ዘፍጥረት 33:1-3
ዘፍጥረት 33:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ያዕቆብም ዐይኑን አነሣ፤ እነሆም፥ ዔሳውን ሲመጣ አየው፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆቹንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለቱም ዕቁባቶቹ አደረጋቸው፤ ዕቁባቶቹንና ልጆቻቸውንም በፊት አደረገ፤ ልያንና ልጆችዋን በኋላ፥ ራሔልንና ዮሴፍንም ከሁሉ በኋላ አደረገ። እርሱም በፊታቸው አለፈ፤ ወደ ወንድሙ ወደ ዔሳውም እስኪደርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ።
ዘፍጥረት 33:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ያዕቆብ አሻግሮ ተመለከተ፤ እነሆ ዔሳው አራት መቶ ሰዎች አስከትሎ እየመጣ ነበር። ስለዚህ ልጆቹን ለልያ፣ ለራሔልና ለሁለቱ አገልጋዮች አከፋፈላቸው። ከዚያም ሁለቱን አገልጋዮች ከነልጆቻቸው አስቀደመ፤ ልያንና ልጆቿንም አስከተለ፤ ራሔልንና ዮሴፍን ግን ከሁሉ ኋላ እንዲሆኑ አደረገ። እርሱ ራሱም ቀድሟቸው ሄደ፤ ወንድሙም ዘንድ እስኪደርስ ድረስ ሰባት ጊዜ ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ።
ዘፍጥረት 33:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ያዕቆብም ዓይኑን አነሣ እነሆም ዔሳውን ሲመጣ አየው ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆቹንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለቱም ባሪያዎች አደረጋቸው፤ ባሪያዎችንና ልጆቻቸውንም በፊት አደረገ ልያንና ልጆችዋንም በኋለኛው ስፍራ ራሔልንና ዮሴፍንም ከሁሉ በኍላ አደረገ። እርሱም በፊታቸው አለፈ ወደ ወንድሙም እስኪደርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ።
ዘፍጥረት 33:1-3 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ያዕቆብ ቀና ብሎ ሲመለከት፥ ዔሳው አራት መቶ ሰዎችን አስከትሎ ሲመጣ አየ፤ ያዕቆብም ልጆቹን ከልያ፥ ከራሔልና ከሁለቱ ሴቶች አገልጋዮቹ ጋር ከፋፈላቸው። በመጀመሪያ ሁለቱን ሴቶች አገልጋዮቹንና ልጆቻቸውን አስቀደመ፤ ቀጥሎ ልያንና ልጆችዋን አስከተለ፤ በመጨረሻም ራሔልንና ዮሴፍን ከሁሉ በኋላ አደረገ። ያዕቆብ ከሁሉ ቀድሞ ተጓዘ፤ ወደ ወንድሙ ወደ ዔሳው ሲቀርብ ወደ መሬት በመጐንበስ ሰባት ጊዜ እጅ ነሣ፤
ዘፍጥረት 33:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ያዕቆብም ዓይኑን አነሣ ተመለከተም፥ እነሆም ዔሳው እየመጣ ነበር፥ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ። ልጆቹንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለቱም አገልጋዮች አደረጋቸው። ሴት አገልጋዮቹንና ልጆቻቸውንም ከፊት አደረገ፥ ልያንና ልጆችዋንም አስከተለ፥ ከዚያም ራሔልንና ዮሴፍን ከሁሉ በኋላ አደረገ። እርሱም ከፊታቸው ቀደመ፥ ወደ ወንድሙም እስኪደርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ።