የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፍጥረት 28:10-17

ዘፍጥረት 28:10-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ያዕቆብ ቤርሳቤህን ትቶ ወደ ካራን ለመሄድ ተነሣ፤ ፀሐይ በጠለቀች ጊዜ ወደ አንድ ስፍራ መጥቶ ዐረፈ፤ በዚያም አንድ ድንጋይ ተንተርሶ ተኛ፤ በሕልሙም ከመሬት እስከ ሰማይ የሚደርስ መሰላል አየ፤ በመሰላሉም የእግዚአብሔር መላእክት ወደ ላይ ይወጡና ወደ ታች ይወርዱ ነበር። እግዚአብሔርም በአጠገቡ ቆሞ እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአንተና ለትውልድህ እንዲሆን ይህን የተኛህበትን ምድር እሰጥሃለሁ፤ ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ እነርሱ በሁሉ አቅጣጫ ይዞታቸውን ያስፋፋሉ፤ በአንተና በዘርህ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ። አይዞህ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበትም ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህም ምድር በደኅና እመልስሃለሁ፤ የገባሁልህን ቃል ኪዳን ሁሉ እፈጽምልሃለሁ፤ ከቶም አልተውህም።” ያዕቆብም ከእንቅልፉ ነቃና “በእርግጥ እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ አለ፤ እኔ ግን ይህን አላወቅሁም ነበር” አለ። በጣም ፈርቶም ስለ ነበር “ይህ እንዴት የሚያስፈራ ቦታ ነው! ይህ የእግዚአብሔር ቤት መሆን አለበት፤ ወደ ሰማይ የሚያስገባው በር ይህ ነው” አለ።

ዘፍጥረት 28:10-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ያዕ​ቆ​ብም ከአ​ዘ​ቅተ መሐላ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ። ወደ አንድ ስፍ​ራም ደረሰ፤ ፀሐ​ይም ጠልቃ ነበ​ርና በዚያ አደረ፤ ከዚ​ያም ስፍራ ድን​ጋ​ዮች አንድ ድን​ጋይ አነሣ፤ ከራ​ሱም በታች ተን​ተ​ርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ። ሕል​ምም አለመ፤ እነ​ሆም መሰ​ላል በም​ድር ላይ ተተ​ክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነ​ሆም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ይወ​ጡ​በ​ትና ይወ​ር​ዱ​በት ነበር። እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላዩ ቆሞ​በት ነበር፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የአ​ባ​ትህ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ አት​ፍራ፥ ይህ​ችን አንተ የተ​ኛ​ህ​ባ​ትን ምድር ለአ​ን​ተም ለዘ​ር​ህም እሰ​ጣ​ለሁ፤ ዘር​ህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆ​ናል፤ እስከ ባሕ​ርና እስከ አዜብ እስከ መስ​ዕና እስከ ምሥ​ራቅ ይበ​ዛል፤ ይሞ​ላ​ልም፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በአ​ንተ፥ በዘ​ር​ህም ይባ​ረ​ካሉ። እነ​ሆም፥ እኔ ከአ​ንተ ጋር እሄ​ዳ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በ​ትም መን​ገድ ሁሉ እጠ​ብ​ቅ​ሃ​ለሁ፤ ወደ​ዚ​ያ​ችም ምድር እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ፤ የነ​ገ​ር​ሁ​ህን ሁሉ እስ​ካ​ደ​ር​ግ​ልህ ድረስ አል​ተ​ው​ህ​ምና።” ያዕ​ቆ​ብም ከእ​ን​ቅ​ልፉ ተነ​ሥቶ፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ስፍራ አለ፤ እኔ አላ​ወ​ቅ​ሁም ነበር” አለ። ፈራ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህ ስፍራ እን​ዴት ያስ​ፈራ፤ ይህ ስፍራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይ​ደ​ለም፤ ይህ​ችም የሰ​ማይ ደጅ ናት።”

ዘፍጥረት 28:10-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሥቶ ወደ ካራን ሄደ። ወደ አንድ ስፍራ እንደ ደረሰም ፀሓይዋ ጠልቃ ስለ ነበር፣ ዐዳሩን በዚያ አደረገ፤ በአቅራቢያው ከነበሩትም ድንጋዮች አንዱን ተንተርሶ ተኛ። በሕልሙም፣ ጫፉ ሰማይ የሚደርስ መሰላል በምድር ላይ ቆሞ፣ በላዩም የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ አየ። እግዚአብሔርም (ያህዌ) ከጫፉ ላይ ቆሞ እንዲህ አለ፤ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ (ኤሎሂም)፣ የይስሐቅ አምላክ (ኤሎሂም) እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ፤ የተኛህበትን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ። ዘርህ እንደ ምድር አሸዋ ይበዛል፤ በምዕራብና በምሥራቅ፣ በሰሜንና በደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በአንተና በዘርህ አማካይነት ይባረካሉ። እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የሰጠሁህን ተስፋ እስከምፈጽምልህ ድረስ አልተውህም።” ያዕቆብም ከእንቅልፉ ሲነቃ፣ “በእውነት እግዚአብሔር (ያህዌ) በዚህ ስፍራ አለ፤ እኔ ግን ይህን አላወቅሁም ነበር” አለ። እርሱም በፍርሀት፣ “ይህ ስፍራ እንዴት የሚያስፈራ ነው! ይህስ ሌላ ሳይሆን የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ቤት መሆን አለበት፤ የሰማይ ደጅ ነው” አለ።

ዘፍጥረት 28:10-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ። ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሣ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ። ሕልምም አለመ፤ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር። እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር እንዲህም አለ፦ የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፤ ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ። እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ በምትሄድባትም ምድር እመልስሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድርስ አልተውህምና። ያዕቆብም ከእንቅልፋ ተነሥቶ፦ በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ነው እኔ አላወቅሁም ነበር አለ። ፈራ፥ እንዲህም አለ፦ ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም ይህም የሰማይ ደጅ ነው።

ዘፍጥረት 28:10-17 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ። ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ፥ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፥ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሣ፥ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ። ሕልምም አለመ፥ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር። እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ እንዲህም አለ፦ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፥ ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል፥ እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ። እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፥ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።” ያዕቆብም ከእንቅልፉ ተነሥቶ፦ “በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ነው፥ እኔ አላወቅሁም ነበር” አለ። ፈራ፥ እንዲህም አለ፦ “ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ፥ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፥ ይህም የሰማይ ደጅ ነው።”