የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 28

28
1ይስሐቅም ያዕቆብን ጠራው ባረከውም እንዲህ ብሎም አዘዘው፤ 2ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች ሚስትን አታግባ ተነሣና ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል ሂድ ከዚያም ከእናትን ወንድም ከላባ ሴቶች ልጆች ሚስትን አግባ። 3ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን ይባርክህ፥ 4ያፍራህ ያብዛህ፤ ሰደተኛ ሆነህ የተቀመጥህባትን እግዚአብሔርም ለአብርሃም የሰጣትን ምድር ትወርስ ዘንድ የአብርሃም በርከት ለአንተ ይስጥህ ለዘርህም እንዲሁ እንደ አንተ። 5ይስሐቅም ያዕቆብን ሰደደው እርሱም የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም የሚሆን የሶርያዊ ባቱኤል ልጅ ላባ ወዳለበት ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል ሄደ። 6ዔሳውም ይስሐቅ ያዕቆብ እንደ ባረከው ባየ ጊዜ ከዚይም ሚስትም ያገባ ዘንድ ወደ ሁለት ወንዞች መካካል እንደ ሰደደው፥ በባረከውም ጊዜ፦ ከከነዓን ሴቶች ልጆች ሚስትን አታግባ ብሎ እንዳዘዘው፥ 7ያዕቆብም የአባቱንና የእናቱን ቃል ሰምቶ ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል እንደሄደ፥ 8የከነዓናውያንም ሴቶች ልጆች በአባቱ በይስሐቅ ፊት የተጠሉ እንደሆኑ ዔሳ ባየ ጊዜ፥ 9ዔሳው ወደ እስማኤል ሄደ ማዕሌትንም በፊት ካሉት ሚስቶች ጋር ሚስት ትሆነው ዘንድ አገባ እርስዋም የአብርሃም ልጅ የሆነ የእስማኤል ልጅና የነባዮት እኅት ናት።
10ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ። 11ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሣ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ። 12ሕልምም አለመ፤ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር። 13እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር እንዲህም አለ፦ የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፤ 14ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ። 15እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ በምትሄድባትም ምድር እመልስሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድርስ አልተውህምና። 16ያዕቆብም ከእንቅልፋ ተነሥቶ፦ በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ነው እኔ አላወቅሁም ነበር አለ። 17ፈራ፥ እንዲህም አለ፦ ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም ይህም የሰማይ ደጅ ነው።
18ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥ በላዩም ዘይትን አፈሰሰበት። 19ያዕቆብም ይንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው አስቀድሞ ግን የዚያች ከተማ ስም ሎዛ ነበረ። 20ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፦ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ 21የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል፤ 22ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ