የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፍጥረት 22:1-10

ዘፍጥረት 22:1-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሮች በኋላ እን​ዲህ ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ር​ሃ​ምን ፈተ​ነው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም ሆይ፥” እር​ሱም፥ “እነሆ፥ አለሁ” አለ። “የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን አንድ ልጅ​ህን ይስ​ሐ​ቅን ይዘህ ወደ ከፍ​ተ​ኛው ተራራ ሂድ፤ እኔም በም​ነ​ግ​ርህ በአ​ንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ ሠዋው” አለው። አብ​ር​ሃ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ሁለ​ቱ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹ​ንና ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ሰነ​ጠቀ፤ ተነ​ሥ​ቶም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ቦታ ሄደ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ደረሰ። አብ​ር​ሃ​ምም ዐይ​ኑን አነ​ሣና ቦታ​ውን ከሩቅ አየ። አብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ​ዎ​ቹን አላ​ቸው፥ “አህ​ያ​ውን ይዛ​ችሁ በዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደ​ዚያ ተራራ ሄደን እን​ሰ​ግ​ዳ​ለን፤ ሰግ​ደ​ንም ወደ እና​ንተ እን​መ​ለ​ሳ​ለን።” አብ​ር​ሃ​ምም የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ዕን​ጨት አን​ሥቶ ለልጁ ለይ​ስ​ሐቅ አሸ​ከ​መው፤ እር​ሱም እሳ​ቱ​ንና ቢላ​ዋ​ዉን በእጁ ያዘ፤ ሁለ​ቱም አብ​ረው ሄዱ። ይስ​ሐ​ቅም አባ​ቱን አብ​ር​ሃ​ምን ተና​ገ​ረው፥ “አባቴ ሆይ፥” አለ፤ እር​ሱም፥ “ልጄ፥ ምን​ድን ነው?” አለው። “እሳ​ቱና ዕን​ጨቱ ይኸው አለ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕቱ በግ ግን ወዴት አለ?” አለው። አብ​ር​ሃ​ምም፥ “ልጄ ሆይ፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን በግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ጋ​ጃል” አለው፤ ሁለ​ቱም አብ​ረው ሄዱ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለ​ውም ወደ​ዚያ ቦታ ደረሱ፤ አብ​ር​ሃ​ምም በዚያ መሠ​ዊ​ያ​ዉን ሠራ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ረበ​ረበ፤ ልጁን ይስ​ሐ​ቅ​ንም አስሮ በመ​ሠ​ዊ​ያዉ በዕ​ን​ጨቱ ላይ በልቡ አስ​ተ​ኛው። አብ​ር​ሃ​ምም እጁን ዘረጋ፤ ልጁ​ንም ያርድ ዘንድ ቢላዋ አነሣ።

ዘፍጥረት 22:1-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) አብርሃምን ፈተነው፤ “አብርሃም!” አለው። እርሱም “አቤቱ አለሁ” አለ። እግዚአብሔርም (ኤሎሂም)፣ “የምትወድደውን አንዱን ልጅህን፣ ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እኔ በማመለክትህ በአንዱ ተራራ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው። በማግስቱም ጧት አብርሃም ማልዶ ተነሣ፤ አህያውን ጭኖ፣ ሁለት አገልጋዮቹንና ልጁን ይስሐቅን ይዞ፣ ለመሥዋዕት የሚበቃውን ዕንጨት ከቈረጠ በኋላ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጕዞውን ጀመረ፤ በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ቦታውን ከሩቅ ተመለከተ፤ አገልጋዮቹንም “እናንተ አህያውን ይዛችሁ እዚህ ቈዩን፤ እኔና ልጄ ግን ወደዚያ ሄደን ለእግዚአብሔር ሰግደን እንመለሳለን” አላቸው። አብርሃም ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን ዕንጨት ወስዶ፣ ልጁን ይስሐቅን አሸከመው፤ እሳቱንና ቢላዋውንም ራሱ ያዘ። ሁለቱም አብረው ሄዱ። ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን፣ “አባቴ ሆይ” አለው። አብርሃምም፣ “እነሆኝ፤ አለሁ ልጄ” አለው። ይስሐቅም፣ “እሳቱና ዕንጨቱ ይኸው፤ ነገር ግን የሚቃጠለው መሥዋዕት የት አለ?” ብሎ ጠየቀ። አብርሃምም፣ “ልጄ ሆይ፤ ለሚቃጠለው መሥዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል (ኤሎሂም ይሬህሎ)” አለው። ሁለቱም አብረው ጕዟቸውን ቀጠሉ። እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወደ አመለከተው ቦታ እንደ ደረሱ፣ አብርሃም መሠዊያ ሠራ፤ በላዩም ላይ ዕንጨት ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያው ዕንጨት ላይ አጋደመው። ከዚያም ልጁን ለማረድ እጁን ዘርግቶ ቢላዋውን አነሣ።

ዘፍጥረት 22:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከእነዚም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብረሃምን ፈተነው፥ እንዲህም አለው፦ አብረሃም ሆይ። አብረሃምም፦ እንሆ፥ አለሁ አለ። የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሕቅን ይዘህ ወደ ሞሪያም ምድር ሂድ፤ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መስዋዕት አድርገህ ሠዋው አለ። አብረሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፥ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሕቅን ከእርሱ ጋር ወሰደ፥ እንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ፤ ተነስቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ። በሦስተኛውም ቀን አብርሃም ዓይኑን አነሣና ቦታውን ከሩቅ አየ። አብርሃምም ሎሌዎቹን አላቸው፦ አህያውን ይዛችሁ ከዚህ ቆዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን እንሰግዳለን፥ ወደ እናንተም እንመለሳለን። አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ፥ ሁለቱም አብረው ሄዱ። ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን ተናገረው፦ አባቴ ሆይ አለ። እርሱም፦ እነሆኝ ልጄ አለው። እሳቱና እንጨቱ ይኸው አለ፤ የመስዋዓቱ በግ ግን ወዴት ነው? አለ። አብርሃምም፦ ልጄ ሆይ፥ የመስዋዕቱን በግ እግዚአብሐር ያዘጋጃል አለው፤ ሁለቱም አብረው ሄዱ። እግዚአብሔር ወዳለውም ቦታ ደረሱ፤ አብርሃምም በዚያ መሰዊያውን ሰራ፥ እንጨትንም ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሰዊያው በእንጨቱ ላይ አጋደመው። አብርሃምም እጁን ዘረጋ፥ ልጁንም ያርድ ዘንድ ቢላዋ አነሣ።

ዘፍጥረት 22:1-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እግዚአብሔርም “አብርሃም!” ብሎ ጠራው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” ብሎ መለሰ። እግዚአብሔርም “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እዚያ በማሳይህ አንድ ኮረብታ ላይ እርሱን መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ” አለው። አብርሃም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕቱ የሚሆን እንጨት ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅንና ሁለት አገልጋዮችን ይዞ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጒዞ ጀመረ። በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት ቦታውን በሩቅ አየ። ከዚህ በኋላ አብርሃም አገልጋዮቹን “እናንተ ከአህያው ጋር እዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን ለእግዚአብሔር ከሰገድን በኋላ እንመለሳለን” አላቸው። አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱ ግን ቢለዋውንና እሳቱን ያዘ፤ ሁለቱም አብረው ሲሄዱ ሳለ፥ ይስሐቅ አብርሃምን “አባባ!” አለው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁ ልጄ!” አለው። ይስሐቅም “እነሆ፥ እሳትና እንጨት ይዘናል፤ ታዲያ ለመሥዋዕት የሚሆነው በግ የት አለ?” በማለት አብርሃምን ጠየቀው። አብርሃምም “ልጄ ሆይ፥ ለመሥዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር ለራሱ ያዘጋጃል” አለው፤ ሁለቱም አብረው መንገዳቸውን ቀጠሉ። እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሠዊያ ሠርቶ እንጨቱን በላዩ ላይ ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ ከእንጨቱ በላይ በመሠዊያው ላይ አጋደመው። ልጁን ለማረድ ቢላዋ አንሥቶ እጁን ዘረጋ፤

ዘፍጥረት 22:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፥ “አብርሃም!” ብሎ ጠራው፤ አብርሃምም፥ “እነሆ፥ አለሁኝ!” ብሎ መለሰ። እግዚአብሔርም፥ “የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሕቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፥ እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋልኝ” አለው። በማግስቱም ጠዋት አብርሃም በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕት የሚሆን ዕንጨትን ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፥ ከእርሱም ጋር ሁለቱን አገልጋዮቹን እና ልጁን ይስሕቅን ይዞ፥ እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ተነሥቶ ጉዞ ጀመረ። በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት ቦታውን በሩቅ አየ። ከዚህ በኋላ አብርሃምም አገልጋዮቹን፥ “አህያውን ይዛችሁ በዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ተራራ ሄደን እንሰግዳለን፤ ሰግደንም ወደ እናንተ እንመለሳለን” አላቸው። አብርሃምም የመሥዋዕቱን ማቃጠያ እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፥ እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ፥ ከዚያም ሁለቱ አብረው ሄዱ። ይስሐቅ አብርሃምን “አባቴ ሆይ!” አለው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁ ልጄ!” አለው። ይስሐቅም “እነሆ፥ እሳትና እንጨት ይዘናል፤ ነገር ግን ለመሥዋዕት የሚሆነው በግ የት አለ?” በማለት ጠየቀው። አብርሃምም “ልጄ ሆይ፥ ለመሥዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር ራሱ ያዘጋጃል” አለው፤ ከዚያም ሁለቱ አብረው ሄዱ። እግዚአብሔር ወዳለውም ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሠዊያ ሠራና እንጨቱን በላዩ ላይ ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያው ላይ፥ ከእንጨቱ በላይ አጋደመው። እጁንም ዘርግቶ፥ ልጁን ለማረድ አብርሃም ቢላዋ አነሣ።