ዘፍጥረት 18:1-14

ዘፍጥረት 18:1-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በቀ​ት​ርም ጊዜ አብ​ር​ሃም በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ተቀ​ምጦ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ምሬ ዛፍ ሥር ተገ​ለ​ጠ​ለት። ዐይ​ኑ​ንም በአ​ነሣ ጊዜ እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያ​ቸ​ውም ጊዜ ሊቀ​በ​ላ​ቸው ከድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ተነ​ሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድ​ርም ሰገደ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ በፊ​ት​ህስ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ ባሪ​ያ​ህን አት​ለ​ፈው፤ ውኃ እና​ም​ጣ​ላ​ችሁ፤ እግ​ራ​ች​ሁ​ንም እን​ጠ​ባ​ችሁ። ከዛ​ፉም ሥር ዕረፉ፤ እን​ጀ​ራም እና​ም​ጣ​ላ​ች​ሁና ብሉ፤ ከዚ​ያም በባ​ሪ​ያ​ችሁ ዘንድ ከአ​ረ​ፋ​ችሁ በኋላ፥ ወደ ዐሰ​ባ​ች​ሁት ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “እን​ዳ​ልህ እን​ዲሁ አድ​ርግ” አሉት። አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ድን​ኳን ወደ ሚስቱ ወደ ሣራ ፈጥኖ ገባና፥ “ሦስት መስ​ፈ​ሪያ የተ​ሰ​ለቀ ዱቄት ፈጥ​ነሽ ለውሺ፤ እን​ጎ​ቻም አድ​ርጊ” አላት። አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፤ እጅግ የሰ​ባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብ​ላ​ቴ​ናው ሰጠው፤ ያዘ​ጋ​ጅም ዘንድ ተቻ​ኮለ። እር​ጎና መዓር፥ ያን ያዘ​ጋ​ጀ​ው​ንም ጥጃ አመጣ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም አቀ​ረ​በው፤ እር​ሱም ከዛፉ በታች በፊ​ታ​ቸው ቆሞ ያሳ​ል​ፍ​ላ​ቸው ነበር፤ እነ​ር​ሱም በሉ። እር​ሱም፥ “ሚስ​ትህ ሣራ ወዴት ናት?” አለው። እር​ሱም፥ “በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ናት” አለው። እር​ሱም፥ “የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ወደ አንተ ተመ​ልሼ እመ​ጣ​ለሁ፤ ሚስ​ትህ ሣራም ልጅን ታገ​ኛ​ለች” አለ። ሣራም በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ በስ​ተ​ኋ​ላው ቆማ ሳለች ይህን ሰማች። አብ​ር​ሃ​ምና ሣራም በዕ​ድ​ሜ​ያ​ቸው ሸም​ግ​ለው ፈጽ​መው አር​ጅ​ተው ነበር፤ በሴ​ቶች የሚ​ሆ​ነ​ውም ልማድ ከሣራ ተቋ​ርጦ ነበር። ሣራም ለብ​ቻዋ በል​ብዋ እን​ዲህ ስትል ሳቀች፥ “እስከ ዛሬ ገና ነኝን? ጌታ​ዬም ፈጽሞ ሽም​ግ​ሎ​አል።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ሣራን ለብ​ቻዋ በል​ብዋ ምን አሳ​ቃት? እስከ ዛሬ ገና ነኝን? በእ​ው​ነ​ትስ እወ​ል​ዳ​ለ​ሁን? ጌታ​ዬም አር​ጅ​ት​ዋል እነሆ፥ እኔም አር​ጅ​ቻ​ለሁ ብላ​ለ​ችና። በውኑ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሳ​ነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገ​ኛ​ለች።”

ዘፍጥረት 18:1-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ቀትር ላይ አብርሃም በመምሬ ትልልቅ ዛፎች አቅራቢያ በምትገኘው ድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር ተገለጠለት፤ ቀና ብሎም ሲመለከት፣ ሦስት ሰዎች ቆመው አየ፤ ወዲያውም ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ፣ ፈጥኖ ወደ ሰዎቹ ሄደ፤ ወደ መሬት ዝቅ ብሎም እጅ ነሣ። አብርሃምም እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ፤ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ፣ ባሪያህን ዐልፈህ አትሂድ፤ ጥቂት ውሃ ይምጣላችሁና እግራችሁን ታጠቡ፤ እዚህም ከዛፉ ሥር ዐረፍ በሉ። ወደ እኔ ወደ አገልጋያችሁ ከመጣችሁ፣ እህል ቀምሳችሁ ትበረቱ ዘንድ ምግብ ላቅርብላችሁና ጕዟችሁን ትቀጥላላችሁ።” እነርሱም፣ “መልካም፤ እንዳልኸው አድርግ” አሉት። አብርሃም በፍጥነት ሣራ ወዳለችበት ወደ ድንኳኑ ገብቶ፣ “ቶሎ ብለሽ ሦስት መስፈሪያ ስልቅ ዱቄት አቡኪና ቂጣ ጋግሪ” አላት። ከዚያም ወደ መንጋው በጥድፊያ ሄዶ፣ አንድ ፍርጥም ያለ ሥጋው ገር የሆነ ጥጃ መርጦ ለአገልጋዩ ሰጠው፤ አገልጋዩም ጥጃውን ዐርዶ አዘጋጀው። አብርሃምም ርጎ፣ ወተትና የተዘጋጀውን የጥጃ ሥጋ አቀረበላቸው፤ ሲበሉም ዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ነበር። እነርሱም አብርሃምን፣ “ሚስትህ ሣራ የት አለች?” ብለው ጠየቁት። እርሱም፣ “ድንኳን ውስጥ ናት” አላቸው። እግዚአብሔርም፣ “ጊዜው ሲደርስ በርግጥ በዚህ ጊዜ በሚቀጥለው ዓመት እመለሳለሁ፤ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው። ሣራም በዚህ ጊዜ ከበስተጀርባው ካለው ከድንኳኑ ደጃፍ ሆና ትሰማ ነበር። በዚያ ጊዜ አብርሃምና ሣራ አርጅተው፣ ዕድሜያቸው ገፍቶ ነበር፤ ሣራም ልጅ የመውለጃዋ ዕድሜ ዐልፎ ነበር። ሣራ በልቧ፣ “ካረጀሁና ጌታዬም ከደከመ በኋላ በዚህ ነገር መደሰት ይሆንልኛል?” ብላ ሣቀች። እግዚአብሔርም አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ሣራ፣ ‘ካረጀሁ በኋላ ልጅ እንዴት አድርጌ እወልዳለሁ’ ስትል ለምን ሣቀች? ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? ጊዜው ሲደርስ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅ ይኖራታል።”

ዘፍጥረት 18:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቅምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት። ዓይኑንም አነሣና እነሆ ሦስት ስዎች በፊቱ ቆመው አየ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ እንዲህም አለ፥ አቤቱ፥ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ፥ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ፤ ቍራሽ እምጀራም ላምጣላችሁ፥ ልባችሁንም ደግፋ ከዚያም በኍል ትሄዳላችሁ፤ ስለዚህ ወደ ባሪያችሁ መጥታችኍልና። አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሣራ ዘንድ ፈጥኖ ገባና፥ ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄር ፈጥነሽ አዘጋጂ፥ ለውሺውም እንጎቻም አድርጊ አላት። አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ እጅግ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴንው ስጠው፥ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኮለ። እርጎን ወተትም ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ በፊታቸውም አቀረበው፤ እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ነበር እነርሱም በሉ። እነርሱም ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? አሉት። እርሱም፥ በድንኳኑ ውስጥ ናት አላቸው። እርሱም፥ የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች አለ። ሣራም በድንኳን ደጃፍ በስተ ኍላው ሳለች ይህንን ሰማች። አብርሃምና ሣራም በዕድሜአቸው ሸምግለው ፈጽመው አርጅተው ነበር። ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች፤ ካረጀሁ በኍላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? ጌታዬም ፈጽሞ ሸምግሎአል። እግዚአብሔርም አብርሃምም አለው፤ ካረጀሁ በኍላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን ሳቀች? በውኑ ለእግዚአሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንድ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታግኝለች።

ዘፍጥረት 18:1-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በመምሬ የወርካ ዛፎች አጠገብ እግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለት፤ የተገለጠለትም በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ከዕለታት አንድ ቀን በቀትር ጊዜ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ነበር፤ ቀና ብሎም ሲመለከት ሦስት ሰዎች እዚያ ቆመው አየ፤ እንዳያቸውም ወዲያውኑ ሊያነጋግራቸው ወደ እነርሱ ሮጠ፤ ግንባሩም መሬት እስኪነካ ዝቅ ብሎ በመስገድ እጅ ነሣ፤ እንዲህም አለ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ፥ አልፈኸኝ እንዳትሄድ እለምንሃለሁ፤ እግራችሁን የምትታጠቡበት ውሃ እስካመጣላችሁ ድረስ በዚህ ዛፍ ጥላ ሥር ዐረፍ በሉ፤ ወደ እኔ ወደ አገልጋያችሁ በመምጣታችሁ ደስ ብሎኛል፤ ስለዚህ ለጒዞአችሁ ብርታት የሚሰጣችሁን ጥቂት ምግብ አምጥቼ እንዳስተናግዳችሁ ፍቀዱልኝ።” እነርሱም “መልካም ነው፤ እንዳልከው አድርግ” አሉት። አብርሃም ወደ ድንኳኑ ሮጦ ሄደና ሣራን “ቶሎ ብለሽ ሦስት መስፈሪያ ዱቄት ውሰጂና አቡክተሽ እንጀራ ጋግሪ” አላት። ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ መንጋው ሄደና ለግላጋውንና መልካሙን ጥጃ መርጦ ለአገልጋዩ ሰጠው፤ አገልጋዩም በፍጥነት ዐርዶ አወራርዶ አዘጋጀው፤ አብርሃም እርጎ፥ ወተትና ሥጋ ይዞ ሄደና ምግቡን ለእንግዶቹ አቀረበላቸው፤ እነርሱ ምግቡን በሚበሉበት ጊዜ አብርሃም ከዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ያስተናግዳቸው ነበር። እነርሱም “ሚስትህ ሣራ የት አለች?” አሉት። እርሱም “እዚያ ድንኳኑ ውስጥ ነች” አላቸው። ከሦስቱም እንግዶች አንዱ አብርሃምን “የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው። እርሱም ይህን በሚናገርበት ጊዜ ሣራ በስተኋላው በድንኳኑ ደጃፍ ቆማ ታዳምጥ ነበር፤ አብርሃምና ሣራ በዕድሜአቸው መግፋት አርጅተው ነበር፤ የሣራም፥ ልጅ የመውለጃ ዕድሜዋ አልፎ ነበር። ስለዚህ ሣራ “እኔ አሁን እንዲህ ካረጀሁ በኋላ ጌታዬ አብርሃምም ካረጀ በኋላ እንዲህ ያለ ደስታ ሊኖረኝ ይችላልን?” ብላ በማሰብ ሳቀች። እግዚአብሔርም አብርሃምን “ሣራ ‘እንደዚህ ካረጀሁ በኋላ ልጅ መውለድ እችላለሁን’ በማለት ስለምን ሳቀች? ከቶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? እንደ ነገርኩህ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው።

ዘፍጥረት 18:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የባሉጥ ዛፎች አጠገብ ተገለጠለት። ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፥ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፥ እንዲህም አለ፦ “አቤቱ፥ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፥ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ፥ እግራችሁን ታጠቡ፥ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ፥ ቁራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፥ ልባችሁንም ደግፋ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ፥ ስለዚህ ወደ ባርያችሁ መጥታችኋልና።” እነርሱም፦ “እንዳልህ አድርግ” አሉት። አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሣራ ዘንድ ፈጥኖ ገባና፦ “ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፥ ለውሺውም፥ እንጎቻም አድርጊ” አላት። አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፥ እጅግ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴናው ሰጠው፥ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኰለ። እርጎና ወተት፥ ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፥ በፊታቸውም አቀረበው፥ እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ነበር፥ እነርሱም በሉ። እነርሱም፦ “ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት?” አሉት። እርሱም፦ “በድንኳኑ ውስጥ ናት” አላቸው። እርሱም፦ “የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ፥ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች” አለ። ሣራም በድንኳን ደጃፍ በስተ ኋላው ሳለች ይህንን ሰማች። አብርሃምና ሣራም በዕድሜአቸው ሸምግለው ፈጽመው አርጅተው ነበር፥ በሴቶች የሚሆነውም ልማድ ከሣራ ተቋርጦ ነበር። ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች፦ “ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? ጌታዬም ፈጽሞ ሸምግሎአል።” እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ “ካረጀሁ በኋላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን ሳቀች? በውኑ ለጌታ የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፥ ሣራም ልጅን ታገኛለች።”