ኦሪት ዘፍጥረት 18
18
1በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቅምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት። 2ዓይኑንም አነሣና እነሆ ሦስት ስዎች በፊቱ ቆመው አየ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ እንዲህም አለ፥ 3አቤቱ፥ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ 4ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ፥ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ፤ 5ቍራሽ እምጀራም ላምጣላችሁ፥ ልባችሁንም ደግፋ ከዚያም በኍል ትሄዳላችሁ፤ ስለዚህ ወደ ባሪያችሁ መጥታችኍልና። 6አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሣራ ዘንድ ፈጥኖ ገባና፥ ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄር ፈጥነሽ አዘጋጂ፥ ለውሺውም እንጎቻም አድርጊ አላት። 7አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ እጅግ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴንው ስጠው፥ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኮለ። 8እርጎን ወተትም ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ በፊታቸውም አቀረበው፤ እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ነበር እነርሱም በሉ።
9እነርሱም ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? አሉት። እርሱም፥ በድንኳኑ ውስጥ ናት አላቸው። 10እርሱም፥ የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች አለ። ሣራም በድንኳን ደጃፍ በስተ ኍላው ሳለች ይህንን ሰማች። 11አብርሃምና ሣራም በዕድሜአቸው ሸምግለው ፈጽመው አርጅተው ነበር። 12ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች፤ ካረጀሁ በኍላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? ጌታዬም ፈጽሞ ሸምግሎአል። 13እግዚአብሔርም አብርሃምም አለው፤ ካረጀሁ በኍላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን ሳቀች? 14በውኑ ለእግዚአሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንድ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታግኝለች። 15ሣራ፥ ስለ ፈራች፤ አልሳቅሁም ስትል ካደች። እርሱም፤ አይደለም፥ ሳቅሽ እንጂ አላት።
16ሰዎቹም ከዚያ ተንሥተው ወደ ሰዶም አቀኑ፤ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ። 17እግዚአብሔርም አለ፤ እኔ የማደርገውን ከአብርሃም እሰውራለሁን? 18አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናልና፤ የምድር አሕዛብም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉና። 19ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኍላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው። 20እግዚአብሔርም አለ የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቶአልና፥ ኃጢአታቸውም እጅግ ከብዳለችና፥ 21እንግዲህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸትዋ አድርገው እንደ ሆነ ወርጄ አያለሁ፤ እንዲሁም ባይሆን አውቃለሁ።
22ሰዎቹም ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ ወደ ሰዶምም ሄዱ፤ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር 23አብርሃምም ቀረበ አለም፦ በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ታጠፋለህን? 24አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፉለህብ? ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን? 25ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርስ አይፈርድምን? 26እግዚአብሔርም፤ በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ አምስ ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ ስለ እነርሱ እምራለሁ አለ። 27አብርሃምም መለስን አለም፤ እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ እነሆ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፤ 28ከአምሳው ጻድቅን አምስት ቢጎድሉ ከተማይቱን ሁሉ በአምስቱ ምክንያት ታጠፋለህን? ከዚያ አርባ አምስት ባገኝ አላጠፋትም አለ። 29ደግሞም ተናገረው እንዲህም አለ፤ ምናልባት ከዚይ አርባ ቢገኙሳ? እርሱም ለአርባው ስል አላደርገውም አለ። 30እርሱም ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ባገኝ አላጠፋም አለ። 31ደግሞም፤ እነሆ ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፤ ምናልባት ከዚያ ሀያ ቢገኙሳ? አለ። እርሱም፤ ከዚያ ሀያ ቢገኙ ስለ ሀያው አላደርገውም አለ። 32እርሱም፥ እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፤ ምናልባት ከዚያ አሥር አላጠፋትም አለ። 33እግዚአብሔርም ከአብርሃም ጋር ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሄደ አብርሃምም ወደ ስፍራው ተመለሰ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 18: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ