ዘፍጥረት 15:6-19

ዘፍጥረት 15:6-19 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አብ​ራ​ምም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመነ፤ ጽድ​ቅም ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት። “ይህ​ችን ምድር ትወ​ር​ሳት ዘንድ እን​ድ​ሰ​ጥህ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር ያወ​ጣ​ሁህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ” አለው። “አቤቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ እን​ደ​ም​ወ​ር​ሳት በምን አው​ቃ​ለሁ?” አለው። እር​ሱም አለው፥ “የሦ​ስት ዓመት ላም፥ የሦ​ስት ዓመት ፍየ​ልም፥ የሦ​ስት ዓመት በግም፥ ዋኖ​ስም፥ ርግ​ብም አምጣ፤ እኒ​ህ​ንም ሁሉ አም​ጥ​ተህ ከሁ​ለት ከሁ​ለት ቍረ​ጣ​ቸው፤ ወፎ​ችን ግን አት​ቍ​ረ​ጣ​ቸው።” እን​ዲ​ሁም እነ​ዚ​ህን ሁሉ ወሰ​ደ​ለት፤ በየ​ሁ​ለ​ትም ከፈ​ላ​ቸው፤ የተ​ከ​ፈ​ሉ​ት​ንም በየ​ወ​ገኑ ትይዩ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ወፎ​ችን ግን አል​ቈ​ረ​ጣ​ቸ​ውም። አሞ​ራ​ዎ​ችም በተ​ቈ​ረ​ጠው ሥጋ​ቸው ላይ ወረዱ፤ አብ​ራ​ምም በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ተቀ​ምጦ አባ​ረ​ራ​ቸው። ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ በአ​ብ​ራም ድን​ጋጤ መጣ​በት፤ እነ​ሆም፥ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ጽኑዕ ጨለማ መጣ​በት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን አለው፥ “ዘርህ ለእ​ነ​ርሱ ባል​ሆ​ነች ምድር ስደ​ተ​ኞች እን​ዲ​ሆኑ በእ​ር​ግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመ​ታ​ትም ባሪ​ያ​ዎች አድ​ር​ገው ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ ያሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ዋል፤ ያስ​ጨ​ን​ቋ​ቸ​ዋ​ልም። ደግ​ሞም የሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ውን እኔ እፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ። ከዚ​ህም በኋላ ከብዙ ገን​ዘብ ጋር ወደ​ዚህ ይወ​ጣሉ። አንተ ግን ወደ አባ​ቶ​ችህ በሰ​ላም ትሄ​ዳ​ለህ፤ በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ል​ናም ትቀ​በ​ራ​ለህ። በአ​ራ​ተ​ኛው ትው​ልድ ግን ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤ እስከ ዛሬ ድረስ የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ኀጢ​አት አል​ተ​ፈ​ጸ​መ​ምና።” እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ነበ​ል​ባል መጣ፤ የእ​ሳት መብ​ራ​ትና የሚ​ጤስ ምድ​ጃም መጣ፤ በዚ​ያም በተ​ከ​ፈ​ለው መካ​ከል አለፈ። በዚ​ያ​ችም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ተስፋ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ቀኔ​ዎ​ሳ​ው​ያ​ንን፥ ቄኔ​ዜ​ዎ​ሳ​ው​ያ​ንን፥ ቄኔ​ሚ​ሎ​ሳ​ው​ያ​ንን፥

ዘፍጥረት 15:6-19 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አብራም እግዚአብሔርን አመነ፤ እርሱም ጽድቅ አድርጎ ቈጠረለት። ደግሞም እግዚአብሔር፣ “ይህችን ምድር ላወርስህ፣ ከከለዳውያን ምድር፣ ከዑር ያወጣሁህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ” አለው። አብራምም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህችን ምድር እንደምወርሳት በምን ዐውቃለሁ?” አለ። እግዚአብሔርም “እያንዳንዳቸው ሦስት ዓመት የሆናቸው አንዲት ጊደር፣ አንድ ፍየልና አንድ በግ፣ በተጨማሪም አንድ ዋኖስና አንድ ርግብ ዐብረህ አቅርብልኝ” አለው። አብራምም እነዚህን ሁሉ አቀረበለት፤ ቈርጦም ሁለት ቦታ ከከፈላቸው በኋላ፣ እያንዳንዱን ክፍል በሌላው ወገን ትይዩ አስቀመጠ፤ ወፎችን ግን ለሁለት አልከፈላቸውም። አሞሮችም ሥጋውን ለመብላት ወረዱ፤ አብራም ግን አባረራቸው። ፀሓይ ልትገባ ስትል አብራም እንቅልፍ ወሰደው፤ የሚያስፈራም ድቅድቅ ጨለማ መጣበት። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “ዘርህ በባዕድ አገር መጻተኛ እንደሚሆን በርግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመትም በባርነት ተረግጦ ይገዛል። ነገር ግን በባርነት የሚገዛቸውን ሕዝብ እቀጣዋለሁ፤ ከዚያም ብዙ ሀብት ይዘው ይወጣሉ። አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ፤ ዕድሜም ጠግበህ ወደ መቃብር ትወርዳለህ፤ በአራተኛውም ትውልድ ዘርህ ወደዚህ ምድር ይመለሳል፤ የአሞራውያን ኀጢአት ገና ጽዋው አልሞላምና።” ፀሓይ ገብታ ከጨለመ በኋላ የምድጃ ጢስና የሚንበለበል ፋና ታየ፤ በተከፈለውም ሥጋ መካከል ዐለፈ። በዚያ ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ሲል ኪዳን ገባለት፤ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤ የምሰጣቸውም የቄናውያንን፣ የቄኔዛውያንን፣ የቃድሞናውያንን፣

ዘፍጥረት 15:6-19 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

አብራምም በእግዚአብሔር አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት። ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ እግዚአሔር እኔ ነኝ አለው። አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ እንድወርሳት በምን አውቃለሁ? አለ። እርሱም፥ የሦስት ዓመት ጊደር፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት በግም ዋኖስም ርግብም ያዝልኝ አለው። እነዚህንም ሁሉ ወሰደለት፥ በየሁለትም ከፈላቸው፥ የተከፈለትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው ወፎችን ግን አልከፈለም። አሞራዎችም በሥጋው ላይ ወረዱ፥ አብራምም አበረራቸው። ፀሐይም በገባች ጊዜ በአብራም ከባድ እንቅልፍ መጣበት፤ እነሆም፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ ወደቀበት፤ አብራምንም አለው፤ ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ እወቅ ባሪያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል። ደግሞም በባርነት በገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ ከዚያም በኍላ በብዙ ከብት ይወጣሉ። አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ በመልካም ሽምግልና ትቀበራለህ። በአራተኛው ትውልድ ግን ወደዚህ ይመለሳሉ የአሞራውያን ኃጢአት ገና አልተፈጸመምና። ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ። በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፤ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤

ዘፍጥረት 15:6-19 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

አብራም በእግዚአብሔር አመነ፤ እምነቱም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት። ደግሞም እግዚአብሔር አብራምን “ይህችን አገር በውርስ ለአንተ እንድሰጥህ ዑር ከምትባለው ከከለዳውያን ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ” አለው። አብራም ግን “ጌታ አምላክ ሆይ፥ ይህች ምድር የእኔ እንደምትሆን እንዴት ለማወቅ እችላለሁ?” ሲል ጠየቀ። እግዚአብሔርም “ሦስት፥ ሦስት ዓመት የሆናቸው አንድ ጊደር፥ አንድ ፍየልና፥ አንድ በግ፥ እንዲሁም ዋኖስና ርግብ አምጣልኝ” አለው። አብራምም እነዚህን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር አምጥቶ እያንዳንዱን እየቈረጠ በሁለት ከፈለው፤ የተከፈሉትንም ትይዩ አድርጎ በሁለት መስመር አስቀመጣቸው። ወፎቹን ግን ቈርጦ አልከፈላቸውም። አሞራዎች የተቈራረጠውን ሥጋ ለመብላት ሲመጡ አብራም አባረራቸው። የፀሐይ መጥለቂያ ሰዓት እየተቃረበ ሲሄድ አብራምን ከባድ እንቅልፍ ያዘው፤ እነሆ፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ መጣበት። እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፦ “የልጅ ልጆችህ በባዕድ አገር ስደተኞች እንደሚሆኑ ዕወቅ፤ እዚያም በባርነትና በጭቈና ለአራት መቶ ዓመት ያስጨንቁአቸዋል፤ በባርነት የሚገዛቸውን ሕዝብ እቀጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ ብዙ ሀብት ይዘው ከዚያ አገር ይወጣሉ። አንተ ግን ብዙ ዘመን ኖረህ በሰላም ትሞታለህ፤ በሰላምም ትቀበራለህ። የልጅ ልጆችህ ወደዚህ ተመልሰው የሚመጡት በአራተኛው ትውልድ ነው፤ እስከዚያ የሚቈዩበትም ምክንያት የአሞራውያን ኃጢአት ገና ስላልተፈጸመ ነው።” ፀሐይ ጠልቃ በጨለመ ጊዜ የምድጃ እሳት ጢስና ነበልባል ታየ፤ በተቈራረጠውም ሥጋ መካከል አለፈ። በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤ እንዲሁም የቄናውያንን፥ የቀኒዛውያንን፥ የቃድሞናውያንን፥

ዘፍጥረት 15:6-19 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አብራምም በእግዚአብሔር አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት። ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ እግዚአሔር እኔ ነኝ አለው። አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንድወርሳት በምን አውቃለሁ? አለ። እርሱም፦ የሦስት ዓመት ጊደር፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም ያዝልኝ አለው። እነዚህንም ሁሉ ወሰደለት፥ በየሁለትም ከፈላቸው፥ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፥ ወፎችን ግን አልከፈለም። አሞራዎችም በሥጋው ላይ ወረዱ፥ አብራምም አበረራቸው። ፀሐይም በገባች ጊዜ በአብራም ከባድ እንቅልፍ መጣበት፥ እነሆም፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ ወደቀበት፥ አብራምንም አለው፦ “ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንደሚሆኑ በእርግጥ እወቅ፥ ባርያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል። ደግሞም በባርነት በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ፥ ከዚያም በኋላ በብዙ ከብት ይወጣሉ። አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ፥ በመልካም ሽምግልና ትቀበራለህ። በአራተኛው ትውልድ ግን ወደዚህ ይመለሳሉ፥ የአሞራውያን ኃጢአት ገና አልተፈጸመምና።” ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ፥ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ። በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፥ ቄናውያንን ቄኔዛውያንንም

ዘፍጥረት 15:6-19

ዘፍጥረት 15:6-19 NASV