የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 15

15
1ከዚህ ነገር በኍላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፤ አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው። 2አብራምም፤ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ ምንን ትሰጠኛለህ? እኔም ያለ ልጅ እሄዳለሁ፤ የቤቴም መጋቢ የደማስቆ ሰው ይህ ኤሊዔዘር ነው አለ። 3አብራምም ለእኔ ዘር አልሰጠኸኝም፤ እነሆም፥ በቤቴ የተወለደ ሰው ይወርስኛል አለ። 4እነሆም፥ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፥ ይህ አይወርስህም፤ ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል። 5ወደ ሜዳም አወጣውና፥ ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቆጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቁጠርን አለው። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው 6አብራምም በእግዚአብሔር አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት። 7ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ እግዚአሔር እኔ ነኝ አለው። 8አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ እንድወርሳት በምን አውቃለሁ? አለ። 9እርሱም፥ የሦስት ዓመት ጊደር፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት በግም ዋኖስም ርግብም ያዝልኝ አለው። 10እነዚህንም ሁሉ ወሰደለት፥ በየሁለትም ከፈላቸው፥ የተከፈለትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው ወፎችን ግን አልከፈለም። 11አሞራዎችም በሥጋው ላይ ወረዱ፥ አብራምም አበረራቸው።
12ፀሐይም በገባች ጊዜ በአብራም ከባድ እንቅልፍ መጣበት፤ እነሆም፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ ወደቀበት፤ 13አብራምንም አለው፤ ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ እወቅ ባሪያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል። 14ደግሞም በባርነት በገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ ከዚያም በኍላ በብዙ ከብት ይወጣሉ። 15አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ በመልካም ሽምግልና ትቀበራለህ። 16በአራተኛው ትውልድ ግን ወደዚህ ይመለሳሉ የአሞራውያን ኃጢአት ገና አልተፈጸመምና። 17ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ። 18በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፤ 19ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤ 20ቄናውያንን፥ ቄኔዛውያንንም፥ ቀድሞንውያንንም፥ ኬጢያውይንንም 21ፌርዛውያንንም፥ ራፋይምንም፥ አሞራውያንንም፥ ከነዓናውያንንም ጌርጌሳውያንንም፥ ኢያቡሳውያንንም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ