ዘፍጥረት 13:1-4
ዘፍጥረት 13:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አብራምም ከግብፅ ወጣ፤ እርሱና ሚስቱ፥ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ፥ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ። አብራምም በከብት፥ በብርና በወርቅ እጅግ በለጸገ። ከአዜብ ባደረገው በጕዞውም ወደ ቤቴል ሄደ፤ ያም ስፍራ አስቀድሞ በቤቴልና በጋይ መካከል ድንኳን ተክሎበት የነበረው ነው፤ ስፍራውም አስቀድሞ መሠውያ የሠራበት ነው፤ በዚያም አብራም የእግዚአብሔርን ስም ጠራ።
ዘፍጥረት 13:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አብራም ሚስቱንና ንብረቱን ሁሉ ይዞ ከግብፅ ወደ ኔጌብ ሄደ፤ ሎጥም አብሮት ነበረ። አብራም በከብት፣ በብርና በወርቅ እጅግ በልጽጎ ነበር። አብራም ከኔጌብ ተነሥቶ እስከ ቤቴል ተጓዘ፤ ቀድሞ በቤቴልና በጋይ መካከል ድንኳኑን ከተከለበት፣ ለመጀመሪያ ጊዜም መሠዊያ ካቆመበት ስፍራ ደረሰ፤ በዚያም የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ስም ጠራ።
ዘፍጥረት 13:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አብራምም ከግብፅ ወጣ እርሱና ሚስቱ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ። አብራምም በከብት በብርና በወርቅ እጅግ በለጠገ። ከአዜብ ባደረገው በጉዞውም ወደ ቤቴል በኩል ሄደ ያም ስፍራ አስቀድሞ በቤቴልና በጋይ መካከል ድንኳን ተክሎበት የነበረው ነው፤ ያም ስፍራ አስቀድሞ መሠውይ የሠራበት ነው በዚያም አብራም የእግዚአብሔርን ስም ጠራ።
ዘፍጥረት 13:1-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አብራም ሚስቱንና ያለውን ሀብት ሁሉ ይዞ ከግብጽ ወደ ኔጌብ ሄደ፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አብራም ብዙ እንስሶች፥ ብዙ ብርና ወርቅ ያለው ሀብታም ሰው ነበረ። ከኔጌብ ተነሥቶም ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር ወደ ቤትኤል አመራ፤ በቤትኤልና በዐይ መካከል ወዳለውም ስፍራ ደረሰ፤ ይህም ስፍራ ከዚህ በፊት ድንኳን ተክሎ የሰፈረበትና፥ መሠዊያም ሠርቶበት የነበረው ነው፤ እዚያም አብርሃም እግዚአብሔርን አመለከ።