ዘፍጥረት 12:1-11

ዘፍጥረት 12:1-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን አለው፥ “ከሀ​ገ​ርህ፥ ከዘ​መ​ዶ​ች​ህም፥ ከአ​ባ​ት​ህም ቤት ተለ​ይ​ተህ ውጣ፤ እኔ ወደ​ማ​ሳ​ይ​ህም ምድር ሂድ። ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ቡሩ​ክም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ባ​ር​ኩ​ህ​ንም እባ​ር​ካ​ለሁ፤ የሚ​ረ​ግ​ሙ​ህ​ንም እረ​ግ​ማ​ለሁ፤ የም​ድር ነገ​ዶ​ችም ሁሉ በአ​ንተ ይባ​ረ​ካሉ።” አብ​ራ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረው ሄደ፤ ሎጥም ከእ​ርሱ ጋር ሄደ፤ አብ​ራ​ምም ከካ​ራን በወጣ ጊዜ ሰባ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ። አብ​ራ​ምም ሚስ​ቱን ሦራ​ንና የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገ​ኙ​ትን ከብት ሁሉና በካ​ራን ያገ​ኙ​አ​ቸ​ውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነ​ዓን ምድር ለመ​ሄድ ወጣ፤ ወደ ከነ​ዓ​ንም ምድር ገቡ። አብ​ራ​ምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚ​ያች ምድር አለፈ፤ የከ​ነ​ዓን ሰዎ​ችም በዚ​ያን ጊዜ በዚ​ያች ምድር ነበሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ራም ተገ​ለ​ጠ​ለ​ትና፥ “ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ” አለው። አብ​ራ​ምም ለእ​ርሱ ለተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ መሠ​ው​ያን ሠራ። ከዚ​ያም በቤ​ቴል ምሥ​ራቅ ወዳ​ለው ተራራ ወጣ፤ በዚ​ያም ቤቴ​ልን ወደ ምዕ​ራብ፥ ጋይን ወደ ምሥ​ራቅ አድ​ርጎ ድን​ኳ​ኑን ተከለ፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ። አብ​ራ​ምም ከዚያ ተነሣ፤ እየ​ተ​ጓ​ዘም ወደ አዜብ ሄደ፤ በዚ​ያም ኖረ። በም​ድ​ርም ራብ ሆነ፤ አብ​ራ​ምም በዚያ በእ​ን​ግ​ድ​ነት ይቀ​መጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በም​ድር ራብ ጠንቶ ነበ​ረና። እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አብ​ራም ወደ ግብፅ ለመ​ግ​ባት በቀ​ረበ ጊዜ ሚስ​ቱን ሦራን እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ መልከ መል​ካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አው​ቃ​ለሁ፤

ዘፍጥረት 12:1-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “ከአገርህ ከወገንህ ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ። “ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፤ ደግሞም እባርክሃለሁ፤ ስምህን ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎች በረከት ትሆናለህ። የሚባርኩህን እባርካለሁ፤ የሚረግሙህን ረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም፣ በአንተ ይባረካሉ።” ስለዚህ አብራም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወጣ፤ ሎጥም ዐብሮት ሄደ። አብራም ከካራን ሲወጣ ዕድሜው 75 ዓመት ነበረ። አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን አስከትሎ በካራን ሳሉ ያፈሩትን ሀብትና የነበራቸውን አገልጋዮች ይዘው በመጓዝ ከነዓን ምድር ገቡ። አብራም ትልቁ የሞሬ ዛፍ እስከሚገኝበት እስከ ሴኬም ድረስ በምድሪቱ ዘልቆ ሄደ። በዚያ ጊዜ ከነዓናውያን በዚሁ ምድር ይኖሩ ነበር። እግዚአብሔርም ለአብራም ተገልጦ፣ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠራ። ከዚያም ተነሥቶ ከቤቴል በስተምሥራቅ ወዳሉት ተራሮች ሄደ፤ ቤቴልን በምዕራብ፣ ጋይን በምሥራቅ አድርጎ ድንኳን ተከለ፣ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ ጸለየ። አብራምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ኔጌብ ሄደ። በዚያም ምድር ጽኑ ራብ ገብቶ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ አብራም ለጥቂት ጊዜ በዚያ ለመኖር ወደ ግብጽ ወረደ። ግብጽ ለመግባት ጥቂት ሲቀረው አብራም ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፤ “መቼም አንቺ ውብ ሴት መሆንሽን ዐውቃለሁ፤

ዘፍጥረት 12:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም አብራምን አለው፤ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ። አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ፤ አብራምም ከካራን በወጣ ጊዜ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበረ። አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፤ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ። አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ሞሬ የአድባር ዛፍ ድረስ በምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በምድሩ ነበሩ። እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፤ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ። ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ የእግዚአብሔር ስም ጠራ። አብራምም ከዚያ ተነሣ፥ እየተጓዘም ወደ አዜብ ሄደ። በምድርም ራብ ሆነ አብራንምም በዚያ በእንግድነት ይቀመጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፥ በምድር ራብ ጸንቶ ነበርና። ወደ ግብፅም ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፤ አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ፤

ዘፍጥረት 12:1-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “አገርህን ትተህ፥ ከዘመዶችህና ከአባትህ ቤተሰብ ተለይተህ፥ እኔ ወደማሳይህ አገር ሂድ፤ ዘርህን አበዛዋለሁ፤ ታላቅ ሕዝብም ይሆናል፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎችም በረከት ትሆናለህ። የሚመርቁህን እመርቃለሁ፤ የሚረግሙህንም እረግማቸዋለሁ፤ በአንተም አማካይነት ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ።” አብራም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ከካራን ወጥቶ ሄደ፤ በዚያን ጊዜ ዕድሜው ሰባ አምስት ዓመት ነበር፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አብራም፥ ሚስቱ ሣራይና የወንድሙ ልጅ ሎጥ፥ በካራን ሳሉ ያገኙትን ሀብትና አገልጋዮቻቸውን ሁሉ ይዘው ወደ ከነዓን ምድር ሄዱ። ከነዓን በደረሱ ጊዜ፥ አብራም በሴኬም ወደሚገኘው ቅዱስ ስፍራ ወደ ሞሬ ዛፍ እስኪደርስ ድረስ ተጓዘ፤ በዚያን ጊዜ ከነዓናውያን በዚያች ምድር ይኖሩ ነበረ። እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና “ለዘርህ የምሰጠው ምድር ይህ ነው” አለው፤ ከዚህ በኋላ አብራም ለተገለጠለት አምላክ በዚያ ቦታ መሠዊያ ሠራ። ቀጥሎም ከቤትኤል በስተምሥራቅ ወዳለው ተራራማ አገር ወጣ፤ ቤትኤልን በስተምዕራብ፥ ዐይን በስተምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፤ በዚያም መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረም ወደ ኔጌብ መጣ። በከነዓን ምድር ራብ ገባ፤ ራብም እየበረታ በመሄዱ አብራም የራቡን ጊዜ ለማሳለፍ በስተደቡብ ርቆ ወደ ግብጽ አገር ሄደ። አብራም ወደ ግብጽ ምድር ለመግባት በተቃረበ ጊዜ ሚስቱን ሣራይን እንዲህ አላት፤ “አንቺ በጣም ቈንጆ ሴት መሆንሽን ዐውቃለሁ፤

ዘፍጥረት 12:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፥ ለበረከትም ትሆናለህ፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፥ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ። አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ፥ ሎጥም ከእርሱ ጋር ሄደ፥ አብራምም ከካራን በወጣ ጊዜ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበረ። አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፥ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ። አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ሞሬ የባሉጥ ዛፍ ድረስ በምድር አለፈ፥ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በምድሩ ነበሩ። እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ። ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፥ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ። አብራምም ከዚያ ተነሣ፥ እየተጓዘም ወደ አዜብ ሄደ። በምድርም ራብ ሆነ፥ አብራምም በዚያ በእንግድነት ይቀመጥ ዘንድ ወደ ግብጽ ወረደ፥ በምድር ራብ ጸንቶ ነበርና። ወደ ግብጽም ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሣራን እንዲህ አላት፦ አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ፥