ኦሪት ዘፍጥረት 12:1-11

ኦሪት ዘፍጥረት 12:1-11 አማ05

እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “አገርህን ትተህ፥ ከዘመዶችህና ከአባትህ ቤተሰብ ተለይተህ፥ እኔ ወደማሳይህ አገር ሂድ፤ ዘርህን አበዛዋለሁ፤ ታላቅ ሕዝብም ይሆናል፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎችም በረከት ትሆናለህ። የሚመርቁህን እመርቃለሁ፤ የሚረግሙህንም እረግማቸዋለሁ፤ በአንተም አማካይነት ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ።” አብራም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ከካራን ወጥቶ ሄደ፤ በዚያን ጊዜ ዕድሜው ሰባ አምስት ዓመት ነበር፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አብራም፥ ሚስቱ ሣራይና የወንድሙ ልጅ ሎጥ፥ በካራን ሳሉ ያገኙትን ሀብትና አገልጋዮቻቸውን ሁሉ ይዘው ወደ ከነዓን ምድር ሄዱ። ከነዓን በደረሱ ጊዜ፥ አብራም በሴኬም ወደሚገኘው ቅዱስ ስፍራ ወደ ሞሬ ዛፍ እስኪደርስ ድረስ ተጓዘ፤ በዚያን ጊዜ ከነዓናውያን በዚያች ምድር ይኖሩ ነበረ። እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና “ለዘርህ የምሰጠው ምድር ይህ ነው” አለው፤ ከዚህ በኋላ አብራም ለተገለጠለት አምላክ በዚያ ቦታ መሠዊያ ሠራ። ቀጥሎም ከቤትኤል በስተምሥራቅ ወዳለው ተራራማ አገር ወጣ፤ ቤትኤልን በስተምዕራብ፥ ዐይን በስተምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፤ በዚያም መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረም ወደ ኔጌብ መጣ። በከነዓን ምድር ራብ ገባ፤ ራብም እየበረታ በመሄዱ አብራም የራቡን ጊዜ ለማሳለፍ በስተደቡብ ርቆ ወደ ግብጽ አገር ሄደ። አብራም ወደ ግብጽ ምድር ለመግባት በተቃረበ ጊዜ ሚስቱን ሣራይን እንዲህ አላት፤ “አንቺ በጣም ቈንጆ ሴት መሆንሽን ዐውቃለሁ፤

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}