ዕዝራ 4:3
ዕዝራ 4:3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ዘሩባቤልና ኢያሱም፥ የቀሩትም የእስራኤል አባቶች ቤቶች አለቆች፥ “የአምላካችንን ቤት መሥራት ለእኛና ለእናንተ አይደለም፤ እኛ ራሳችን ግን የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዳዘዘን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ቤት እንሠራለን” አሉአቸው።
Share
ዕዝራ 4 ያንብቡዕዝራ 4:3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ዘሩባቤል፣ ኢያሱና ሌሎቹ የእስራኤል ቤተ ሰቦች አለቆች ግን፣ “ለአምላካችን ቤተ መቅደስ እንድትሠሩ ከእኛ ጋር የሚያገናኛችሁ ምንም ነገር የለም። የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ ባዘዘን መሠረት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የምንሠራው እኛ ብቻ ነን” ሲሉ መለሱላቸው።
Share
ዕዝራ 4 ያንብቡዕዝራ 4:3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ዘሩባቤልና ኢያሱም የቀሩትም የእስራኤል አባቶች ቤቶች አለቆች “የአምላካችንን ቤት መሥራት ለእኛና ለእናንተ አይደለም፤ እኛ ለብቻችን ግን የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዳዘዘን ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤት እንሠራለን” አሉአቸው።
Share
ዕዝራ 4 ያንብቡ