የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሕዝቅኤል 36:1-7

ሕዝቅኤል 36:1-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ትን​ቢት ተና​ገር፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ በላ​ቸው። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጠላት በእ​ና​ንተ ላይ፦ እሰይ! ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጥፋት፥ ለእኛ ርስት ሆነ​ዋል ብሎ​አ​ልና፤ ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለቀ​ሩት አሕ​ዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ያሉ አሕ​ዛብ አዋ​ር​ደ​ዋ​ች​ኋ​ልና፤ ውጠ​ዋ​ች​ሁ​ማ​ልና፥ እና​ን​ተም የተ​ና​ጋ​ሪ​ዎች ከን​ፈር መተ​ረ​ቻና የአ​ሕ​ዛብ ማላ​ገጫ ሆና​ች​ኋ​ልና፤ ስለ​ዚህ፥ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ሆይ! የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለተ​ራ​ሮ​ችና ለኮ​ረ​ብ​ቶች፥ ለፈ​ሳ​ሾ​ችና ለሸ​ለ​ቆ​ዎች፥ ለም​ድረ በዳ​ዎች፥ ባዶ ለሆ​ኑ​ትና ለፈ​ረ​ሱት፥ በዙ​ሪያ ላሉት ለቀ​ሩት አሕ​ዛብ ምር​ኮና መሣ​ለ​ቂያ ለሆ​ኑት ከተ​ሞች እን​ዲህ ይላል፦ ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያሳ​ድ​ዱ​አ​ትና ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አት ዘንድ በል​ባ​ቸው ሁሉ ደስ​ታና በነ​ፍ​ሳ​ቸው ንቀት ምድ​ሬን ርስት አድ​ር​ገው ለራ​ሳ​ቸው በሰጡ በቀ​ሩት አሕ​ዛ​ብና በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ላይ በቅ​ን​አቴ እሳት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ ስለ እስ​ራ​ኤል ምድር ትን​ቢት ተና​ገር፤ ለተ​ራ​ሮ​ችና ለኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም፥ ለፈ​ሳ​ሾ​ችና ለሸ​ለ​ቆ​ዎ​ችም እን​ዲህ በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የአ​ሕ​ዛ​ብን ስድብ ስለ ተሸ​ከ​ማ​ችሁ በቅ​ን​አ​ቴና በመ​ዓቴ ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ። ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዙ​ሪ​ያ​ችሁ በአሉ አሕ​ዛብ ላይ እኔ እጄን አነ​ሣ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ኀፍ​ረ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ።

ሕዝቅኤል 36:1-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለእስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘የእስራኤል ተራሮች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ጠላት ስለ አንቺ፣ “ዕሠይ! እነዚያ የጥንት ተራሮች የእኛ ርስት ሆነዋል ብሏል።” ’ ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከየአቅጣጫው ከብበው በመውጋት ስላጠቋችሁ፣ ለቀሩት ሕዝቦች ሁሉ ርስት ሆናችሁ፤ ለሕዝብም መሣቂያና መሣለቂያ ሆናችሁ። ስለዚህ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፤ የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኰረብቶች፣ ለሸለቆዎችና ለውሃ መውረጃዎች፣ ለፈራረሱ ባድማዎችና፣ በሌሎቹ በዙሪያችሁ ባሉት ሕዝቦች ተዘርፈውና መዘባበቻ ሆነው መና ለቀሩት ከተሞች እንዲህ ይላል፤ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በሚቃጠል ቅናቴ በቀሩት ሕዝቦች ሁሉና በኤዶም ሁሉ ላይ ተናግሬአለሁ፤ ከልብ በመነጨ ደስታና በንቀት ተሞልተው የግጦሽ መሬቴን ይዘው ይበዘብዙት ዘንድ የራሳቸው ርስት አድርገውታልና።’ ስለዚህ የእስራኤልን ምድር የሚመለከት ትንቢት ተናገር፤ ለተራሮች፣ ለኰረብቶች፣ ለሸለቆዎችና ለውሃ መውረጃዎች እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሕዝቦች ዘለፋ ስለ ተሠቃያችሁ ቍጣ በተሞላ ቅናቴ እናገራለሁ።” ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እጄን አንሥቼ እምላለሁ፤ በዙሪያችሁ ያሉ ሕዝቦች ዘለፋ ይወርድባቸዋል።”

ሕዝቅኤል 36:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናግረህ፦ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ በል። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠላት በእናንተ ላይ፦ እሰይ፥ የጥንት ከፍታዎች ለእኛ ርስት ሆነዋል ብሎአልና ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ ባድማ አድርገዋችኋልና፥ ውጠዋችሁማልና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የሕዝብ ማላገጫ ሆናችኋልና ስለዚህ፥ እናንተ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለፈሳሾችና ለሸለቆች ለምድረ በዳዎች ባዶ ለሆኑትም በዙሪያ ላሉት ለቀሩት አሕዛብ ምርኮና መሳቂያ ለሆኑት ከተሞች እንዲህ ይላል፥ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ፥ ስለዚህ ስለ እስራኤል ምድር ትንቢት ተናገር፥ ለተራሮችና ለኮረብቶችም ለፈሳሾችና ለሸለቆችም እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የአሕዛብን ስድብ ስለ ተሸከማችሁ በቅንዓቴና በመዓቴ ተናግሬአለሁ፥ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ ስድባቸውን በእርግጥ ይሸከማሉ ብዬ ምያለሁ።

ሕዝቅኤል 36:1-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ለእስራኤል ተራራዎች ትንቢት ተናገር፤ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምለውን ያዳምጡ ዘንድ ንገራቸው፤ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ጠላቶች ‘እነሆ፥ እነዚያ የጥንት ተራራዎች የእኛ ሆነዋል!’ በማለት መጓደድ ጀምረዋል። “ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ብለህ ለእስራኤል ተራራዎች ትንቢት ተናገር አለኝ፦ የባዕድ አገር ሕዝቦች በሁሉም አቅጣጫ ምድራችሁን ስላፈራረሱትና በእርግጥም ባድማ ስላደረጉት አገራችሁ ለሌሎች ሕዝቦች ንብረት ሆነ። እናንተም የሰዎች መሳቂያና መሳለቂያ ሆናችኋል። ስለዚህ እናንተ የእስራኤል ተራራዎች የልዑል እግዚአብሔርን ቃል አድምጡ፦ ለተራሮችና ለኰረብቶች፥ ለወራጅ ውሃዎችና ለሸለቆዎች፥ ባድማና ወና ሆነው ለተለቀቁትና በአካባቢው ላሉ ሕዝቦች ሁሉ የዘረፋ ምንጮችና የመሳለቂያ ርእስ ለሆኑት ከተሞች ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በኀይለኛ ቅናቴ በሌሎች ሕዝቦች ላይና በመላዋ ኤዶም ላይ እናገራለሁ፤ እነርሱ ደስታን በተመላ ስሜትና በፍጹም ንቀት መሰማሪያዋን ለመውረር ምድሬን ርስታቸው አደረጉት፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር። “ስለ እስራኤል ምድር ትንቢት ተናገር፥ ለሕዝቡም እንዲህ በላቸው፦ በተራሮቻችሁ፥ በኰረብቶቻችሁ፥ በወራጅ ውሃዎቻችሁና በሸለቆዎቻችሁ ላይ ሕዝቦች ባደረሱት ውርደት ምክንያት እኔ በኀይለኛ የቊጣ ቅናቴ እናገራለሁ ይላል ልዑል እግዚአብሔር። በእናንተ ዙሪያ የሚገኙ የጐረቤት አገሮች ሁሉ እንደሚዋረዱ፥ እኔ ልዑል እግዚአብሔር በፍጹም እምላለሁ።

ሕዝቅኤል 36:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናገር፥ እንዲህም በላቸው፦ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታን ቃል ስሙ። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠላት በእናንተ ላይ፦ “እሰይ! የጥንት ከፍታዎች ለእኛ ርስት ሆነዋል” ብሏልና፥ ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰላጠፉአችሁ፥ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ ባድማ አድርገዋችኋልና፥ ውጠዋችኋልምና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የሕዝብ ማላገጫ ሆናችኋልና ስለዚህ፥ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ። ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለውሃ መውረጃዎችና ለሸለቆዎች፥ ለፈራረሱ ቦታዎችና ባዶ ለሆኑትም በዙሪያ ላሉት ለቀሩት ሕዝቦች ምርኮና መሳቂያ ለሆኑት ከተሞች እንዲህ ይላል፥ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ፤ ስለዚህ ስለ እስራኤል ምድር ትንቢት ተናገር፥ ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለውሃ መውረጃዎችና ለሸለቆች እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በቅንዓቴና በመዓቴ ተናግሬአለሁ የሕዝቦችን ስድብ ተሸከማችሁአልና፤ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዙሪያችሁ ያሉ ሕዝቦች በእርግጥ ስድባቸውን ይሸከማሉ ብዬ እጄን አንስቻለሁ።