የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ሕዝቅኤል 36:1-7

ትንቢተ ሕዝቅኤል 36:1-7 መቅካእኤ

አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናገር፥ እንዲህም በላቸው፦ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታን ቃል ስሙ። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠላት በእናንተ ላይ፦ “እሰይ! የጥንት ከፍታዎች ለእኛ ርስት ሆነዋል” ብሏልና፥ ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰላጠፉአችሁ፥ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ ባድማ አድርገዋችኋልና፥ ውጠዋችኋልምና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የሕዝብ ማላገጫ ሆናችኋልና ስለዚህ፥ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ። ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለውሃ መውረጃዎችና ለሸለቆዎች፥ ለፈራረሱ ቦታዎችና ባዶ ለሆኑትም በዙሪያ ላሉት ለቀሩት ሕዝቦች ምርኮና መሳቂያ ለሆኑት ከተሞች እንዲህ ይላል፥ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ፤ ስለዚህ ስለ እስራኤል ምድር ትንቢት ተናገር፥ ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለውሃ መውረጃዎችና ለሸለቆች እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በቅንዓቴና በመዓቴ ተናግሬአለሁ የሕዝቦችን ስድብ ተሸከማችሁአልና፤ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዙሪያችሁ ያሉ ሕዝቦች በእርግጥ ስድባቸውን ይሸከማሉ ብዬ እጄን አንስቻለሁ።