ሕዝቅኤል 33:7-9
ሕዝቅኤል 33:7-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“የሰው ልጅ ሆይ፤ አንተን ለእስራኤል ቤት ጕበኛ አድርጌሃለሁ፤ ስለዚህ የምናገረውን ቃል ስማ፤ ማስጠንቀቂያዬንም ስጣቸው። ኀጢአተኛውን፣ ‘አንተ ክፉ ሰው፤ በርግጥ ትሞታለህ’ ባልሁት ጊዜ፣ ከመንገዱ እንዲመለስ ባታደርገው፣ ያ ክፉ ሰው በኀጢአቱ ይሞታል፤ አንተን ግን ስለ ደሙ እጠይቅሃለሁ። ነገር ግን ክፉውን ሰው ከመንገዱ እንዲመለስ አስጠንቅቀኸው ከመንገዱ ባይመለስ፣ እርሱ ስለ ኀጢአቱ ይሞታል፤ አንተ ግን ራስህን አድነሃል።
ሕዝቅኤል 33:7-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእስራኤል ቤት ጕበኛ አድርጌሃለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ፤ ከእኔም ዘንድ አስጠንቅቃቸው። ኀጢአተኛውን፦ ኀጢአተኛ ሆይ! በርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ፥ ኀጢአተኛውን ከክፉ መንገዱ ታስጠነቅቅ ዘንድ ባትናገር፥ ያ ኀጢአተኛ በኀጢአቱ ይሞታል፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ። ነገር ግን ከመንገዱ ይመለስ ዘንድ ኀጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው፥ እርሱም ከመንገዱ ባይመለስ፥ በኀጢአቱ ይሞታል፤ አንተ ግን ነፍስህን ታድናለህ።
ሕዝቅኤል 33:7-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“የሰው ልጅ ሆይ፤ አንተን ለእስራኤል ቤት ጕበኛ አድርጌሃለሁ፤ ስለዚህ የምናገረውን ቃል ስማ፤ ማስጠንቀቂያዬንም ስጣቸው። ኀጢአተኛውን፣ ‘አንተ ክፉ ሰው፤ በርግጥ ትሞታለህ’ ባልሁት ጊዜ፣ ከመንገዱ እንዲመለስ ባታደርገው፣ ያ ክፉ ሰው በኀጢአቱ ይሞታል፤ አንተን ግን ስለ ደሙ እጠይቅሃለሁ። ነገር ግን ክፉውን ሰው ከመንገዱ እንዲመለስ አስጠንቅቀኸው ከመንገዱ ባይመለስ፣ እርሱ ስለ ኀጢአቱ ይሞታል፤ አንተ ግን ራስህን አድነሃል።
ሕዝቅኤል 33:7-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ቤት ጕበኛ አድርጌሃለሁ፥ ከአፌ ቃሌን ስማ ከእኔም ዘንድ አስጠንቅቃቸው። ኃጢአተኛውን፦ ኃጢአተኛ ሆይ፥ በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ፥ ኃጢአተኛውን ከመንገዱ ታስጠነቅቅ ዘንድ ባትናገር ያ ኃጢአተኛ በኃጢአቱ ይሞታል፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ። ነገር ግን ከመንገዱ ይመለስ ዘንድ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው እርሱም ከመንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።
ሕዝቅኤል 33:7-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“አሁንም የሰው ልጅ ሆይ! እነሆ፥ እኔ አንተን ለእስራኤል ሕዝብ ጠባቂ አድርጌሃለሁ፤ እኔ የምሰጥህን ማስጠንቀቂያ ሁሉ ለእነርሱ ማስተላለፍ አለብህ፤ ኃጢአተኛውን ሰው ‘ኃጢአተኛ ሆይ! በእርግጥ ትሞታለህ’ በምለው ጊዜ አንተ ከክፉ ሥራው እንዲመለስ ባታስጠነቅቀው፥ ያ ሰው ኃጢአተኛ እንደ ሆነ በኃጢአቱ ይሞታል፤ ስለ እርሱም ሞት አንተን ራስህን በኀላፊነት ተጠያቂ አደርግሃለሁ። ኃጢአተኛውን ሰው ከክፉ ሥራው እንዲመለስ ካስጠነቀቅኸው በኋላ፥ ከክፉ ሥራው ሳይመለስ በኃጢአቱ ጸንቶ ቢሞት ግን፥ አንተ ራስህን ከኀላፊነት ነጻ ታደርጋለህ።”
ሕዝቅኤል 33:7-9 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ቤት ዘበኛ አድርጌሃለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ ከእኔም ዘንድ አስጠንቅቃቸው። ኃጢአተኛውን ሰው፦ ኃጢአተኛ ሆይ፥ በእርግጥ ትሞታለህ በምለው ጊዜ፥ ኃጢአተኛውን ከመንገዱ ባታስጠነቅቀው ያ ኃጢአተኛ ሰው በኃጢአቱ ይሞታል፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ። ነገር ግን ከመንገዱ እንዲመለስ ኃጢአተኛውን ሰው ብታስጠነቅቀው እርሱም ከመንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።