ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 33:7-9

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 33:7-9 አማ2000

“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጕበኛ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቃ​ቸው። ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን፦ ኀጢ​አ​ተኛ ሆይ! በር​ግጥ ትሞ​ታ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ከክፉ መን​ገዱ ታስ​ጠ​ነ​ቅቅ ዘንድ ባት​ና​ገር፥ ያ ኀጢ​አ​ተኛ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ ደሙን ግን ከእ​ጅህ እፈ​ል​ጋ​ለሁ። ነገር ግን ከመ​ን​ገዱ ይመ​ለስ ዘንድ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ብታ​ስ​ጠ​ነ​ቅ​ቀው፥ እር​ሱም ከመ​ን​ገዱ ባይ​መ​ለስ፥ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ አንተ ግን ነፍ​ስ​ህን ታድ​ና​ለህ።