ዘፀአት 9:22-23
ዘፀአት 9:22-23 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በግብፅም ሀገር ሁሉ በሰውና በእንስሳም በምድርም ቡቃያ ሁሉ ላይ በረዶ ይሆናል።” ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድና በረዶ ላከ፤ እሳትም ወደ ምድር ወረደ፤ እግዚአብሔርም በግብፅ ሀገር ሁሉ ላይ በረዶ አዘነበ።
Share
ዘፀአት 9 ያንብቡዘፀአት 9:22-23 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “በመላዪቱ የግብፅ ምድር ባሉት ሰዎች፣ በእንስሳት እንዲሁም በምድሪቱ ላይ በሚበቅሉት ነገሮች ሁሉ ላይ በረዶ እንዲወርድ እጅህን ወደ ሰማይ አንሣ” አለው። ሙሴ በትሩን ወደ ሰማይ ባነሣ ጊዜ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነጐድጓድና በረዶ አወረደ፤ መብረቅም በምድሪቱ ላይ ሆነ። እግዚአብሔር (ያህዌ) በግብፅ ምድር በረዶ አዘነበ፤
Share
ዘፀአት 9 ያንብቡዘፀአት 9:22-23 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም ሙሴን፦ “በግብፅ አገር በሰው፥ በእንስሳም፥ በእርሻም ቡቃያ ሁሉ ላይ፥ በግብፅ አገር ሁሉ በረዶ ይሆን ዘንድ እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው። ሙሴም በትሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጎድጓድና በረዶ ላከ፤ እሳትም ወደ ምድር ወረደ፤ እግዚአብሔርም በግብፅ አገር ላይ በረዶ አዘነበ።
Share
ዘፀአት 9 ያንብቡ