የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፀአት 6:13-30

ዘፀአት 6:13-30 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚህ ሁኔታ እግዚአብሔር ስለ እስራኤላውያንና ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ለሙሴና ለአሮን ነገራቸው፤ እስራኤላውያንንም ከግብጽ እንዲያወጡ አዘዛቸው። የየቤተ ሰቡ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፣ ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮን፣ ከርሚ። እነዚህ የሮቤል ነገድ ናቸው። የስምዖን ወንዶች ልጆች፣ ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሐርና የከነዓናዊቱም ልጅ ሳኡል ነበሩ። እነዚህ የስምዖን ነገድ አባቶች ናቸው። በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ወንዶች ልጆች ስሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጌርሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው። ሌዊ መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ። የጌርሶን ወንዶች ልጆች በትውልዳቸው ሎቤኒና ሰሜኢ ነበሩ። የቀዓት ወንዶች ልጆች እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮንና ዑዝኤል ነበሩ፤ ቀዓት መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ኖረ። የሜራሪ ወንዶች ልጆች ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ። በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ነገዶች እነዚህ ናቸው። እንበረም የአጎቱን እናት ዮካብድን አገባ፤ እርሷም አሮንና ሙሴን ወለደችለት። እንበረም መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ። የይስዓር ወንዶች ልጆች፣ ቆሬ፣ ናፌግና ዝክሪ ነበሩ። የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፣ ሚሳኤል፣ ኤልዳፋንና ሥትሪ ነበሩ። አሮንም የአሚናዳብን ልጅ፣ የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፤ እርሷም ናዳብንና አብዩድን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት። የቆሬ ወንዶች ልጆች፣ አሴር፣ ሕልቃናና አብያሳፍ ነበሩ፤ እነዚህ የቆሬ ነገድ ጐሣ ናቸው። የአሮን ልጅ አልዓዛር ከፉትኤል ሴት ልጆች አንዷን አገባ፤ እርሷም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደየነገዳቸው የሌዋውያን ጐሣዎች አለቆች ነበሩ። እግዚአብሔር “እስራኤላውያንን በየሰራዊታቸው ከግብጽ አውጡ” ብሎ የነገራቸው አሮንንና ሙሴን ነበር። ስለ እስራኤላውያን ከግብጽ መውጣት፣ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ያናገሩትም እነዚሁ ሙሴና አሮን ነበሩ። እግዚአብሔር ሙሴን በግብጽ በተናገረው ጊዜ፣ እንዲህ አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ የነገርሁህን ሁሉ ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖን ንገረው።” ሙሴ ግን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ፈርዖን ምን ብሎ ይሰማኛል? አንደበቴ ኰልታፋ ነው።”

ዘፀአት 6:13-30 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን “እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር መርታችሁ እንድታወጡ እኔ ያዘዝኳችሁ መሆኔን ለእስራኤላውያንና ለግብጽ ንጉሥ ንገሩ” ብሎ አዘዛቸው። የያዕቆብ በኲር ልጅ ሮቤል፥ ሐኖክ፥ ፋሉ፥ ሔጽሮንና ካርሚ የሚባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሮቤል ነገድ አባቶች ናቸው። ስምዖን ከከነዓናዊት ሴት የተወለደውን ሻኡልን ጨምሮ ይሙኤል፥ ያሚን፥ ኦሃድ ያኪንና፥ ጾሓር የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የስምዖን ነገድ አባቶች ናቸው። ሌዊ ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሌዊ ነገድ አባቶች ናቸው፤ ሌዊ በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነበር። ጌርሾን፥ ሊብኒና ሺምዒ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ብዙ ዘሮች ነበሩአቸው። ቀዓት፥ ዓምራም፥ ይጽሐር፥ ኬብሮንና ዑዚኤል የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ቀዓት በሕይወት የኖረበት ዘመን 133 ዓመት ነው። መራሪ ማሕሊና ሙሺ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህና ዘሮቻቸው ሁሉ የሌዊ ወገኖች ናቸው። ዓምራም ዮኬቤድ የተባለችውን የአባቱን እኅት አገባ፤ እርስዋም አሮንንና ሙሴን ወለደችለት። ዓምራም በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነው። ይጽሐር ቆሬ፥ ኔፌግና ዚክሪ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ዑዚኤልም ሚሻኤል፥ ኤልጻፋንና ሲትሪ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት። አሮን የነአሶን እኅት የሆነችውን የዓሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ፤ እርስዋም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ወንዶች ልጆች ወለደችለት። ቆሬ አሲር፥ ኤልቃናና አቢያሳፍ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም ለቆሬ ዘሮች ሁሉ የነገድ አባቶች ነበሩ። የአሮን ልጅ አልዓዛር የፑቲኤልን ልጅ አገባ፤ እርስዋም ፊኒሐስን ወለደችለት፤ እነዚህ ሁሉ የሌዊ የነገድ አባቶችና አለቆች ነበሩ። ከነዚህ መካከል እግዚአብሔር ሙሴና አሮን “የእስራኤልን ሕዝብ በየነገዳቸው ከግብጽ ምድር መርታችሁ አውጡ” ብሎ ያዘዛቸው ነው። “የእስራኤልን ሕዝብ ልቀቅ” ብለው ከግብጽ ንጉሥ ጋር የተነጋገሩ እነርሱ ናቸው። እግዚአብሔር ሙሴን በግብጽ ምድር በተናገረው ጊዜ፤ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ እኔ የምነግርህን ሁሉ ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖን ንገር” አለው። ሙሴ ግን “እኔ ኰልታፋ ነኝ፤ ታዲያ፥ ንጉሡ እንዴት ሊሰማኝ ይችላል?” ሲል መለሰ።

ዘፀአት 6:13-30 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ተና​ገ​ራ​ቸው፤ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ እን​ዲ​ያ​ወ​ጣ​ቸው ይነ​ግ​ሩት ዘንድ አዘ​ዛ​ቸው። የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤት አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው። የእ​ስ​ራ​ኤል የበ​ኵር ልጅ የሮ​ቤል ልጆች ሄኖኅ፥ ፍሉስ፥ አስ​ሮን፥ ከርሚ፤ እነ​ዚህ የሮ​ቤል ትው​ልድ ናቸው። የስ​ም​ዖ​ንም ልጆች፤ ይሙ​ኤል፥ ያሚን፥ አኡድ፥ ያኪን፥ ሱሐር፥ የፊ​ኒ​ቃ​ዊ​ቱም ልጅ ሳኡል፤ እነ​ዚህ የስ​ም​ዖን ትው​ልድ ናቸው። እነ​ዚ​ህም እንደ ወገ​ኖ​ቻ​ቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ናቸው፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌ​ዊም የሕ​ይ​ወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው። የጌ​ድ​ሶ​ንም ልጆች በየ​አ​ባ​ታ​ቸው ወገን ሎቤኒ፥ ሰሜኢ ናቸው። የቀ​ዓ​ትም ልጆች እን​በ​ረም፥ ይስ​ዓር፥ ኬብ​ሮን፥ ዑዝ​ኤል ናቸው፤ የቀ​ዓ​ትም የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነው። የሜ​ራሪ ልጆች ሞሖሊ፥ ሐሙሲ ናቸው። እነ​ዚ​ህም እንደ ትው​ል​ዳ​ቸው የሌዊ ትው​ልድ ናቸው። እን​በ​ረ​ምም የአ​ባ​ቱን ወን​ድም ልጅ ዮካ​ብ​ድን አገባ፤ አሮ​ን​ንና ሙሴን፥ እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ማር​ያ​ምን ወለ​ደ​ች​ለት፤ የእ​ን​በ​ረ​ምም የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው። የይ​ስ​ዓ​ርም ልጆች ቆሬ፥ ናፌግ፥ ዝክሪ ናቸው። የዑ​ዝ​ኤ​ልም ልጆች ሚሳ​ኤል፥ ኤል​ሳ​ፋን፥ ሴትሪ ናቸው። አሮ​ንም የአ​ሚ​ና​ዳ​ብን ልጅ የነ​አ​ሶ​ንን እኅት ኤል​ሳ​ቤ​ጥን አገባ። እር​ስ​ዋም ናዳ​ብ​ንና አብ​ዩ​ድን፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን ወለ​ደ​ች​ለት። የቆሬ ልጆች አሴር፥ ሕል​ቃና፥ አብ​ያ​ሳፍ ናቸው፤ እነ​ዚህ የቆሬ ልጆች ትው​ልድ ናቸው። የአ​ሮ​ንም ልጅ አል​ዓ​ዛር ከፋ​ት​ኤል ልጆች ሚስ​ትን አገባ፤ እር​ስ​ዋም ፊን​ሐ​ስን ወለ​ደ​ች​ለት። እነ​ዚ​ህም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው የሌ​ዋ​ው​ያን አባ​ቶች አለ​ቆች ናቸው። እነ​ዚህ አሮ​ንና ሙሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ከግ​ብፅ ምድር ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አውጡ” ያላ​ቸው ናቸው። እነ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ያወጡ ዘንድ ከግ​ብፅ ንጉሥ ከፈ​ር​ዖን ጋር የተ​ነ​ጋ​ገሩ ናቸው፤ እነ​ዚ​ህም ሙሴና አሮን ናቸው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብፅ ሀገር ሙሴን በተ​ና​ገ​ረው ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እኔ የም​ነ​ግ​ር​ህን ሁሉ ለግ​ብፅ ንጉሥ ለፈ​ር​ዖን ንገር” ብሎ ተና​ገ​ረው። ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት፥ “እነሆ፥ እኔ አን​ደ​በተ ርቱዕ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እን​ዴ​ትስ ፈር​ዖን ይሰ​ማ​ኛል?” አለ።

ዘፀአት 6:13-30 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚህ ሁኔታ እግዚአብሔር ስለ እስራኤላውያንና ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ለሙሴና ለአሮን ነገራቸው፤ እስራኤላውያንንም ከግብጽ እንዲያወጡ አዘዛቸው። የየቤተ ሰቡ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፣ ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮን፣ ከርሚ። እነዚህ የሮቤል ነገድ ናቸው። የስምዖን ወንዶች ልጆች፣ ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሐርና የከነዓናዊቱም ልጅ ሳኡል ነበሩ። እነዚህ የስምዖን ነገድ አባቶች ናቸው። በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ወንዶች ልጆች ስሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጌርሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው። ሌዊ መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ። የጌርሶን ወንዶች ልጆች በትውልዳቸው ሎቤኒና ሰሜኢ ነበሩ። የቀዓት ወንዶች ልጆች እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮንና ዑዝኤል ነበሩ፤ ቀዓት መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ኖረ። የሜራሪ ወንዶች ልጆች ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ። በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ነገዶች እነዚህ ናቸው። እንበረም የአጎቱን እናት ዮካብድን አገባ፤ እርሷም አሮንና ሙሴን ወለደችለት። እንበረም መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ። የይስዓር ወንዶች ልጆች፣ ቆሬ፣ ናፌግና ዝክሪ ነበሩ። የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፣ ሚሳኤል፣ ኤልዳፋንና ሥትሪ ነበሩ። አሮንም የአሚናዳብን ልጅ፣ የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፤ እርሷም ናዳብንና አብዩድን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት። የቆሬ ወንዶች ልጆች፣ አሴር፣ ሕልቃናና አብያሳፍ ነበሩ፤ እነዚህ የቆሬ ነገድ ጐሣ ናቸው። የአሮን ልጅ አልዓዛር ከፉትኤል ሴት ልጆች አንዷን አገባ፤ እርሷም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደየነገዳቸው የሌዋውያን ጐሣዎች አለቆች ነበሩ። እግዚአብሔር “እስራኤላውያንን በየሰራዊታቸው ከግብጽ አውጡ” ብሎ የነገራቸው አሮንንና ሙሴን ነበር። ስለ እስራኤላውያን ከግብጽ መውጣት፣ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ያናገሩትም እነዚሁ ሙሴና አሮን ነበሩ። እግዚአብሔር ሙሴን በግብጽ በተናገረው ጊዜ፣ እንዲህ አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ የነገርሁህን ሁሉ ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖን ንገረው።” ሙሴ ግን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ፈርዖን ምን ብሎ ይሰማኛል? አንደበቴ ኰልታፋ ነው።”

ዘፀአት 6:13-30 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን ተናገራቸው፤ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖንም የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ እንዲያወጣቸው ይነግሩት ዘንድ አዘዛቸው። የአባታቸውም ቤት አለቆች እነዚህ ናቸው። የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፦ ሄኖኅ፥ ፈሉስ፥ አስሮን፥ ከርሚ፤ እነዚህ የሮቤል ወገኖች ናቸው። የስምዖንም ልጆች፦ ይሙኤል፥ ያሚን፥ ኦሃድ፥ ያኪን፥ ዶሐር፥ የከነዓናዊቱም ልጅ ሳኡል፤ እነዚህ የስምዖን ወገኖች ናቸው። እነዚህም እንደ ወገኖቻቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌዊም የሕይወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው። የጌድሶንም ልጆች እንደ ወገኖቻቸው ሎቤኒ፥ ሰሜኢ ናቸው። የቀዓትም ልጆች እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል ናቸው፤ የቀዓትም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነው። የሜራሪ ልጆች ሞሖሊ፥ ሙሲ ናቸው። እነዚህ እንደ ትውልዳቸው የሌዊ ወገኖች ናቸው። እንበረምም የአጎቱን ልጅ ዮካብድን አገባ፤ አሮንንና ሙሴንም ወለደችለት፤ የእንበረምም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው። የይስዓር ልጆች ቆሬ፥ ናፌግ፥ ዝክሪ ናቸው። የዑዝኤል ልጆች ሚሳኤል፥ ኤልዳፋን፥ ሥትሪ ናቸው። አሮንም የአሚናዳብን የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፤ እርስዋም ዮናዳብንና አብድን አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት። የቆሬ ልጆች አሴር፥ ሕልቃና፥ አብያሳፍ ናቸው፤ እነዚህ የቆሬ ልጆች ወገኖች ናቸው። የአሮንም ልጅ አልዓዛር ከፉትኤል ልጆች ሚስት አገባ፤ እርስዋም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደ ወገኖቻቸው የሌዋውያን አባቶች አለቆች ናቸው። እነዚህ አሮንና ሙሴ እግዚአብሔር፦ ከግብፅ ምድር በየሠራዊቶቻቸው የእስራኤልን ልጆች አውጡ” ያላቸው ናቸው። እነዚህ የእስራኤልን ልጆች “ከግብፅ ያወጡ ዘንድ ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን ጋር የተነጋገሩ ናቸው፤ እነዚህ ሙሴና አሮን ናቸው። እግዚአብሔርም በግብፅ አገር ሙሴን በተናገረው ቀን እንዲህ ሆነ፤ እግዚአብሔር ሙሴን፦ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ እኔ የምነግርህን ሁሉ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገር፤” ብሎ ተናገረው። ሙሴም በእግዚአብሔር ፊት፦ “እነሆ እኔ ከንፈረ ቈላፍ ነኝ፤ እንዴትስ ፈርዖን ይሰማኛል?” አለ።

ዘፀአት 6:13-30 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን “እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር መርታችሁ እንድታወጡ እኔ ያዘዝኳችሁ መሆኔን ለእስራኤላውያንና ለግብጽ ንጉሥ ንገሩ” ብሎ አዘዛቸው። የያዕቆብ በኲር ልጅ ሮቤል፥ ሐኖክ፥ ፋሉ፥ ሔጽሮንና ካርሚ የሚባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሮቤል ነገድ አባቶች ናቸው። ስምዖን ከከነዓናዊት ሴት የተወለደውን ሻኡልን ጨምሮ ይሙኤል፥ ያሚን፥ ኦሃድ ያኪንና፥ ጾሓር የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የስምዖን ነገድ አባቶች ናቸው። ሌዊ ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሌዊ ነገድ አባቶች ናቸው፤ ሌዊ በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነበር። ጌርሾን፥ ሊብኒና ሺምዒ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ብዙ ዘሮች ነበሩአቸው። ቀዓት፥ ዓምራም፥ ይጽሐር፥ ኬብሮንና ዑዚኤል የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ቀዓት በሕይወት የኖረበት ዘመን 133 ዓመት ነው። መራሪ ማሕሊና ሙሺ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህና ዘሮቻቸው ሁሉ የሌዊ ወገኖች ናቸው። ዓምራም ዮኬቤድ የተባለችውን የአባቱን እኅት አገባ፤ እርስዋም አሮንንና ሙሴን ወለደችለት። ዓምራም በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነው። ይጽሐር ቆሬ፥ ኔፌግና ዚክሪ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ዑዚኤልም ሚሻኤል፥ ኤልጻፋንና ሲትሪ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት። አሮን የነአሶን እኅት የሆነችውን የዓሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ፤ እርስዋም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ወንዶች ልጆች ወለደችለት። ቆሬ አሲር፥ ኤልቃናና አቢያሳፍ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም ለቆሬ ዘሮች ሁሉ የነገድ አባቶች ነበሩ። የአሮን ልጅ አልዓዛር የፑቲኤልን ልጅ አገባ፤ እርስዋም ፊኒሐስን ወለደችለት፤ እነዚህ ሁሉ የሌዊ የነገድ አባቶችና አለቆች ነበሩ። ከነዚህ መካከል እግዚአብሔር ሙሴና አሮን “የእስራኤልን ሕዝብ በየነገዳቸው ከግብጽ ምድር መርታችሁ አውጡ” ብሎ ያዘዛቸው ነው። “የእስራኤልን ሕዝብ ልቀቅ” ብለው ከግብጽ ንጉሥ ጋር የተነጋገሩ እነርሱ ናቸው። እግዚአብሔር ሙሴን በግብጽ ምድር በተናገረው ጊዜ፤ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ እኔ የምነግርህን ሁሉ ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖን ንገር” አለው። ሙሴ ግን “እኔ ኰልታፋ ነኝ፤ ታዲያ፥ ንጉሡ እንዴት ሊሰማኝ ይችላል?” ሲል መለሰ።

ዘፀአት 6:13-30 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታም ሙሴንና አሮንን ተናገራቸው፥ የእስራኤልን ልጆችንና የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ እንዲያወጣቸው እንዲነግሩት አዘዛቸው። የአባቶቻቸው ቤት አለቆች እነዚህ ናቸው። የእስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል ልጆች ሐኖክ፥ ፋሉ፥ ሔፅሮንና ካርሚ፤ እነዚህ የሮቤል ወገኖች ናቸው። የስምዖንም ልጆች ይሙኤል፥ ያሚን፥ ኦሃድ፥ ያኪን፥ ጾሐር፥ የከነዓናዊቱም ልጅ ሻኡል፤ እነዚህ የስምዖን ወገኖች ናቸው። እነዚህ የሌዊ ልጆች ስሞች እንደ ትውልዳቸው ጌርሾን፥ ቀሃት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌዊም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው። የጌርሾንም ልጆች እንደ ወገኖቻቸው ሊብኒና፥ ሽምኢ ናቸው። የቀሃትም ልጆች ዓምራም፥ ይፅሃር፥ ሔብሮን፥ ዑዚኤል ናቸው፤ የቀሃትም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነው። የሜራሪ ልጆች ማሕሊ፥ ሙሺ ናቸው። እነዚህ እንደ ትውልዳቸው የሌዊ ወገኖች ናቸው። ዓምራምም የአባቱን እኅት ዮካቤድን አገባ፥ አሮንንና ሙሴንም ወለደችለት፤ የዓምራምም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው። የይፅሃር ልጆች ቆራሕ፥ ኔፌግ፥ ዚክሪ ናቸው። የዑዚኤል ልጆች ሚሻኤል፥ ኤልጻፋን፥ ሢትሪ ናቸው። አሮንም የዓሚናዳብን ልጅ የናሕሾንን እኅት ኤሊሼባን አገባ፥ እርሷም ናዳብ፥ አቢሁ፥ ኤልዓዛርንና ኢታማርን ወለደችለት። የቆራሕ ልጆች አሲር፥ ኤልቃናና፥ አቢያሳፍ ናቸው፤ እነዚህ የቆራሓውያን ወገኖች ናቸው። የአሮንም ልጅ ኤልዓዛር ከፑቲኤል ልጆች አንዷን ሚስት አገባ፥ እርሷም ፒንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደ ወገኖቻቸው የሌዋውያን አባቶች አለቆች ናቸው። እነዚህ አሮንና ሙሴ ጌታ፦ “የእስራኤልን ልጆች በየነገዳቸው ከግብጽ ምድር አውጡ” ያላቸው ናቸው። እነዚህ ከግብጽ ንጉሥ ከፈርዖን ጋር የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ስለማውጣት የተነጋገሩ ናቸው፤ እነዚህም ሙሴና አሮን ናቸው። ጌታ በግብጽ አገር ሙሴን በተናገረው ቀን፥ እርሱም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ ጌታ ነኝ፤ ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖን እኔ የምነግርህን ሁሉ ንገረው።” ሙሴም በጌታ ፊት፦ “እነሆ እኔ ከንፈሬ ያልተገረዘ ነኝ፤ እንዴትስ ፈርዖን ይሰማኛል?” አለ።