የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፀአት 33:14-21

ዘፀአት 33:14-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር (ያህዌ) “ሀልዎቴ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ ዕረፍትም እሰጥሃለሁ” ብሎ መለሰ። ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለው፤ “ሀልዎትህ ከእኛ ጋር ካልሄደ ከዚህ አትስደደን። አንተ ከእኛ ጋር ካልሄድህ፣ አንተ በእኔና በሕዝብህ መደሰትህን ሌላው እንዴት ያውቃል? እኔንና ሕዝብህንስ በገጸ ምድር ከሚገኙት ከሌሎቹ ሕዝቦች ሁሉ ልዩ የሚያደርገን ሌላ ምን አለ?” እግዚአብሔርም (ያህዌ) ሙሴን፣ “በአንተ ደስ ስላለኝና በስም ስለማውቅህ፣ የጠየቅኸውን ያንኑ አደርጋለሁ” አለው። ከዚያም ሙሴ “እባክህ፤ ክብርህን አሳየኝ” አለው። እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “መልካምነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ በፊትህም ስሜን እግዚአብሔርን (ያህዌ) ዐውጃለሁ፤ ለምምረው ምሕረት አደርጋለሁ፤ ለምራራለትም ርኅራኄ አደርጋለሁ፤ ነገር ግን፣ ማንም እኔን አይቶ መኖር ስለማይችል፣ ፊቴን ማየት አትችልም።” ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “በአጠገቤ ስፍራ አለ አንተም በዐለት ላይ ትቆማለህ፤

ዘፀአት 33:14-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እኔ በፊ​ትህ እሄ​ዳ​ለሁ፥ አሳ​ር​ፍ​ህ​ማ​ለሁ” አለው። እር​ሱም፥ “አንተ ከእኛ ጋር ካል​ወ​ጣ​ህስ፥ ከዚህ አታ​ው​ጣን። በም​ድ​ርም ከአ​ለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝ​ብህ ተለ​ይ​ተን እን​ከ​ብር ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካል​ሄ​ድህ፥ እኔና ሕዝ​ብህ በአ​ንተ ዘንድ በእ​ው​ነት ሞገስ ማግ​ኘ​ታ​ችን በምን ይታ​ወ​ቃል?” አለው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ይህን ያል​ኸ​ኝን ነገር አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ፤ በፊቴ ሞገ​ስን አግ​ኝ​ተ​ሀ​ልና ከሁሉ ይልቅ ዐው​ቄ​ሃ​ለ​ሁና”አለው። እር​ሱም፥ “ክብ​ር​ህን አሳ​የኝ” አለው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እኔ በክ​ብሬ በፊ​ትህ አል​ፋ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም በፊ​ትህ እጠ​ራ​ለሁ፤ ይቅ​ርም የም​ለ​ውን ይቅር እላ​ለሁ፤ የም​ም​ረ​ው​ንም እም​ራ​ለሁ” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ሰው አይ​ቶኝ አይ​ድ​ን​ምና ፊቴን ማየት አይ​ቻ​ል​ህም” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እነሆ፥ ስፍራ በእኔ ዘንድ አለ፥ በዐ​ለ​ቱም ላይ ትቆ​ማ​ለህ፤

ዘፀአት 33:14-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔርም “እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ ሰላምም እሰጥሃለሁ።” አሳርፍህማለሁ አለው። ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ከእኛ ጋር የማትወጣ ከሆንክ፥ እኛንም ከዚህ ስፍራ አታውጣን፤ ከእኛ ጋር የማትወጣ ከሆነ በሕዝብህም ሆነ በእኔና በሕዝብህ ደስ መሰኘትህን ሰዎች ሁሉ እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ? እኛን በምድር ላይ ካሉት ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የተለየ የሚያደርገን የአንተ ከእኔና ከሕዝብህ ጋር መሆን አይደለምን?” እግዚአብሔርም ሙሴን “እኔ አንተን በሚገባ በትክክል ስለማውቅህና በአንተም ደስ ስለምሰኝ የምትለውን ሁሉ አደርጋለሁ” አለው። ሙሴም እግዚአብሔርን “እባክህን ክብርህን አሳየኝ” አለው። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ደግነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ስሜን በፊትህ ዐውጃለሁ፤ የምምረውን እምራለሁ፤ የምራራለትንም እራራለታለሁ፤ ፊቴን አይቶ ለመኖር የሚችል ሰው ስለሌለ ፊቴን ለማየት አትችልም። ነገር ግን እዚህ በአጠገቤ በአለት ላይ የምትቆምበት ስፍራ አለ።