የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 33

33
እስ​ራ​ኤል ከሲና ተራራ እንደ ተነሡ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “ሂድ፤ አንተ ከግ​ብፅ ከአ​ወ​ጣ​ኸው ሕዝ​ብህ ጋር ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ለዘ​ራ​ችሁ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ ብዬ ወደ ማል​ሁ​ባት ምድር ውጣ። 2መል​አ​ኬ​ንም ከአ​ንተ ጋር በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ፤ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ያወ​ጣ​ቸ​ዋል። 3ወተ​ትና ማርም ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ምድር አስ​ገ​ባ​ሃ​ለሁ፤ አን​ገተ ደን​ዳና ስለ​ሆኑ ሕዝ​ብህ በመ​ን​ገድ ላይ እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋህ እኔ ከአ​ንተ ጋር አል​ወ​ጣም።” 4ሕዝ​ቡም ይህን ክፉ ወሬ ሰም​ተው ታላቅ ኀዘን አዘኑ፤#ዕብ. “ከእ​ነ​ር​ሱም ማንም ጌጡን አል​ለ​በ​ሰም” የሚል ይጨ​ም​ራል። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እና​ንተ አን​ገተ ደን​ዳና ሕዝብ ናችሁ፤ ሌላ መቅ​ሠ​ፍት እን​ዳ​ላ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁና እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ አሁ​ንም የክ​ብር ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንና ጌጣ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ አውጡ፤ የማ​ደ​ር​ግ​ባ​ች​ሁ​ንም አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ በላ​ቸው” አለው። 6የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከኮ​ሬብ ተራራ ጀም​ረው ልብ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ጌጦ​ቻ​ቸ​ውን አወጡ።
ደብ​ተራ ኦሪት
7ሙሴም ድን​ኳ​ኑን ወስዶ ከሰ​ፈር ውጭ ይተ​ክ​ለው ነበር፤ ከሰ​ፈ​ሩም ራቅ ያደ​ር​ገው ነበር፤ “የም​ስ​ክ​ሩም ድን​ኳን” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የፈ​ለገ ሁሉ ከሰ​ፈር ውጭ ወደ​አ​ለው ወደ ድን​ኳኑ ይወጣ ነበር። 8ሙሴም ከሰ​ፈር ውጭ ወደ​አ​ለው ድን​ኳን በሄደ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ እየ​ጠ​በቀ ይቆም ነበር፤ ሙሴም ወደ ድን​ኳኑ እስ​ኪ​ገባ ድረስ ይመ​ለ​ከ​ቱት ነበር። 9ሙሴም ወደ ድን​ኳኑ በገባ ጊዜ ዐምደ ደመና ይወ​ርድ ነበር፤ በድ​ን​ኳ​ኑም ደጃፍ ይቆም ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ይና​ገ​ረው ነበር። 10ሕዝ​ቡም ሁሉ ዐምደ ደመ​ናው በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ሲቆም ያየው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ተነ​ሥቶ እያ​ን​ዳ​ንዱ በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ይሰ​ግድ ነበር። 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ ሰው ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር እን​ደ​ሚ​ነ​ጋ​ገር ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ይነ​ጋ​ገር ነበር። ሙሴም ወደ ሰፈሩ ይመ​ለስ ነበር፤ ነገር ግን አገ​ል​ጋዩ ብላ​ቴና የነዌ ልጅ ኢያሱ ከድ​ን​ኳኑ አይ​ወ​ጣም ነበር።
ሙሴና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር
12ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እነሆ፥ አንተ፦ ይህን ሕዝብ አውጣ ትለ​ኛ​ለህ፤ ነገር ግን ከእኔ ጋር የም​ት​ል​ከ​ውን አላ​ስ​ታ​ወ​ቅ​ኸ​ኝም። አን​ተም ከሁሉ ይልቅ#ዕብ. “በስ​ምህ” ይላል። ዐወ​ቅ​ሁህ፥ ደግ​ሞም በእኔ ፊት ሞገ​ስን አገ​ኘህ አል​ኸኝ። 13አሁ​ንም በፊ​ትህ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ ዐው​ቅህ ዘንድ በፊ​ት​ህም ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ይህም ትልቅ ሕዝብ ሕዝ​ብህ እንደ ሆነ ዐውቅ ዘንድ ተገ​ለ​ጥ​ልኝ” አለው። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እኔ በፊ​ትህ እሄ​ዳ​ለሁ፥ አሳ​ር​ፍ​ህ​ማ​ለሁ” አለው። 15እር​ሱም፥ “አንተ ከእኛ ጋር ካል​ወ​ጣ​ህስ፥ ከዚህ አታ​ው​ጣን። 16በም​ድ​ርም ከአ​ለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝ​ብህ ተለ​ይ​ተን እን​ከ​ብር ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካል​ሄ​ድህ፥ እኔና ሕዝ​ብህ በአ​ንተ ዘንድ በእ​ው​ነት ሞገስ ማግ​ኘ​ታ​ችን በምን ይታ​ወ​ቃል?” አለው።
17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ይህን ያል​ኸ​ኝን ነገር አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ፤ በፊቴ ሞገ​ስን አግ​ኝ​ተ​ሀ​ልና ከሁሉ ይልቅ ዐው​ቄ​ሃ​ለ​ሁና”#ዕብ. “በስ​ምህ ዐው​ቄ​ሃ​ለሁ” ይላል።አለው። 18እር​ሱም፥ “ክብ​ር​ህን አሳ​የኝ” አለው። 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እኔ በክ​ብሬ በፊ​ትህ አል​ፋ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም በፊ​ትህ እጠ​ራ​ለሁ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በስሜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ራ​ለሁ” ይላል። ይቅ​ርም የም​ለ​ውን ይቅር እላ​ለሁ፤ የም​ም​ረ​ው​ንም እም​ራ​ለሁ” አለ። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ሰው አይ​ቶኝ አይ​ድ​ን​ምና ፊቴን ማየት አይ​ቻ​ል​ህም” አለ። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እነሆ፥ ስፍራ በእኔ ዘንድ አለ፥ በዐ​ለ​ቱም ላይ ትቆ​ማ​ለህ፤ 22ክብ​ሬም በአ​ለፈ ጊዜ በአ​ለቱ ስን​ጥቅ ውስጥ አኖ​ር​ሃ​ለሁ፤ 23እስከ አል​ፍም ድረስ እጄን በላ​ይህ እጋ​ር​ዳ​ለሁ፤ እጄ​ንም ፈቀቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በዚያ ጊዜ ጀር​ባ​ዬን ታያ​ለህ፤ ፊቴ ግን ለአ​ንተ አይ​ታ​ይም።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ