የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፀአት 3:7-17

ዘፀአት 3:7-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “በግ​ብፅ ያለ​ውን የሕ​ዝ​ቤን መከራ በእ​ው​ነት አየሁ፦ ከአ​ሠ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰማሁ፤ ሥቃ​ያ​ቸ​ው​ንም ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ ከዚ​ያ​ችም ሀገር ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊ​ዪ​ቱና ወደ መል​ካ​ሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ስፍራ አወ​ጣ​ቸው ዘንድ ወረ​ድሁ። አሁ​ንም እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ ደረሰ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ባ​ቸ​ውን ግፍ ደግሞ አየሁ። አሁ​ንም ና፤ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን እል​ክ​ሃ​ለሁ። ሕዝ​ቤን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ታወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።” ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን እሄድ ዘንድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ከግ​ብፅ ምድር አወጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?” አለው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “በእ​ው​ነት እኔ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ እኔም እንደ ላክ​ሁህ ይህ ለአ​ንተ ምል​ክት ይሆ​ን​ሃል፤ ሕዝ​ቡን ከግ​ብፅ በአ​ወ​ጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ” አለው። ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እነሆ፥ እኔ ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች እሄ​ዳ​ለሁ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ ወደ እና​ንተ ላከኝ እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ‘ስሙስ ማን ነው?’ ብለው በጠ​የ​ቁኝ ጊዜ ምን እላ​ቸ​ዋ​ለሁ?” አለው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ ነገ​ረው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “ያለና የሚ​ኖር እኔ ነኝ፤ እን​ዲህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ‘ያለና የሚ​ኖር’ ወደ እና​ንተ ላከኝ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ” አለው። ዳግ​መ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን አለው፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ትላ​ለህ፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እና​ንተ ላከኝ፤ ይህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ስሜ ነው፤ እስከ ልጅ ልጅ ድረ​ስም መታ​ሰ​ቢ​ያዬ ይህ ነው። ሂድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰብ​ስብ፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፦ መጐ​ብ​ኘ​ትን ጐበ​ኘ​ኋ​ችሁ፤ በግ​ብ​ፅም የሚ​ደ​ረ​ግ​ባ​ች​ሁን አየሁ፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦ ከግ​ብፅ መከራ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን ሀገር፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስስ ሀገር አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤

ዘፀአት 3:7-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲህ አለ፣ “በግብፅ አገር የሚኖሩትን የሕዝቤን መከራ አይቻለሁ፤ ከአሠሪዎቻቸው ጭካኔ የተነሣ የሚያሰሙትንም ጩኸት ሰምቻለሁ፤ ሥቃያቸውንም ተረድቼአለሁ። ስለዚህም ከግብፃውያን እጅ ልታደጋቸውና ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ሰፊና ለም ወደሆነችው ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያን፣ ፌርዛውያን፣ ኤዊያውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ላወጣቸው ወርጃለሁ። አሁንም የእስራኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ ደርሷል፤ ግብፃውያን የሚያደርሱባቸውን ግፍ አይቻለሁ። በል እንግዲህ ና፤ ሕዝቤን፣ የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ምድር እንድታወጣቸው ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ”። ሙሴ እግዚአብሔርን (ኤሎሂም)፣ “ወደ ፈርዖን የምሄድና የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ የማወጣ እኔ ማን ነኝ?” አለው። እግዚአብሔርም (ኤሎሂም)፣ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔ የላክሁህ ለመሆኑ ምልክቱ ይህ ነው፤ ሕዝቡን ከግብፅ ካወጣሃቸው በኋላ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) ታመልካላችሁ” አለው። ሙሴም እግዚአብሔርን (ኤሎሂም)፣ “ወደ እስራኤል ልጆች ሄጄ፣ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል’ ስላቸው ‘ስሙ ማን ነው?’ ብለው ቢጠይቁኝ ምን እላቸዋለሁ?” አለው። እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) ሙሴን፣ “እኔ፣ ያለሁና የምኖር ነኝ (ያህዌ)፤ ስለዚህም፣ ‘ያለና የሚኖር ልኮኛል’ ብለህ ንገራቸው” አለው። ደግሞም እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሙሴን፣ “የአባቶቻችሁ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ የሆነው እግዚአብሔር (ያህዌ) ወደ እናንተ ልኮኛል፤ ስሜም ለዘለዓለም ይኸው ነው፤ ወደ ፊት በተከታታይ በሚነሣው ትውልድ ሁሉ የምታሰበው በዚህ ስም ነው ብለህ ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው” አለው። “ሂድና የእስራኤልን አለቆች ሰብስበህ፣ የአባቶቻችሁ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ የሆነው እግዚአብሔር (ያህዌ) ተገለጠልኝና እንዲህ አለኝ፤ ጐብኝቻችኋለሁ፤ በግብፅ የደረሰባችሁንም አይቻለሁ። ስለዚህም በግብፅ ከምትቀበሉት መከራ አውጥቼ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ወደ ከነዓናውያን፣ ወደ ኬጢያውያን፣ ወደ አሞራውያን፣ ወደ ፌርዛውያን፣ ወደ ኤዊያውያንና ኢያቡሳውያን ምድር አገባችኋለሁ ብሏል ብለህ ንገራቸው” አለኝ።

ዘፀአት 3:7-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም አለ፦ “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፤ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ። ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ሰፊይቱና ወደ መልካሚቱ አገር ወደ ከነዓናውያንም ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ። አሁንም እነሆ የእስራኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ ወጣ፤ ግብፃውያንም የሚያደርጉባቸውን ግፍ ደግሞ አየሁ። አሁንም ና! ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ታወጣ ዘንድ ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ።” ሙሴም እግዚአብሔርን፦ “ወደ ፈርዖን የምሄድ የእስራኤልንም ልጆች ከግብፅ የማወጣ እኔ ማን ነኝ?” አለው። እርሱም፦ “በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ነው፤ ሕዝቡን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ ለእግዚአብሔር ትገዛላችሁ፤” አለ። ሙሴም እግዚአብሔርን፦ “እነሆ፥ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ’ ባልሁም ጊዜ፦ ‘ስሙስ ማን ነው?’ ባሉኝ ጊዜ፥ ምን እላቸዋለሁ?” አለው። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ “‘ያለና የሚኖር’ እኔ ነኝ” አለው፤ “እንዲህ ለእስራኤል ልጆች፦ ‘ያለና የሚኖር’ ወደናንተ ላከኝ ትላለህ፤” አለው። እግዚአብሔርም ደግሞ ሙሴን አለው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያቆብም አምላክ እግዚአብሔር ወደናንተ ላከኝ፤’ ይህ ለዘላለሙ ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው። ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ሰብስብ፦ ‘እግዚአብሔር የአባቶቻችሁ አምላክ የአብርሃም የይስሐቅም የያዕቆብም አምላክ፦ መጎብኘትን ጎበኘኋችሁ፤ በግብፅም የሚደረግባችሁን አየሁ፤ ከግብፅም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ፤ አልሁ ብሎ ተገለጠልኝ፤’ በላቸው።

ዘፀአት 3:7-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን ጭንቀት አይቻለሁ፤ በአስጨናቂዎቻቸው ምክንያት የሚጮኹትን ጩኸት ሰምቼአለሁ፤ ጭንቀታቸውንም ዐውቃለሁ። እነርሱንም ከግብጻውያን እጅ ለማዳን ወርጃለሁ፤ ከግብጽም አውጥቼ አሁን ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ የሚኖሩባትን፥ በማርና በወተት የበለጸገችውን ሰፊና ለም የሆነችውን ምድር እሰጣቸዋለሁ። እነሆ፥ የሕዝቤ የእስራኤል ጩኸት ወደ እኔ ደርሶአል፤ ግብጻውያን በእነርሱ ላይ የሚያደርሱባቸውን የግፍ ጭቈና ተመልክቻለሁ፤ ስለዚህ አሁን ሕዝቤን ከግብጽ ምድር ታወጣ ዘንድ ወደ ግብጽ ንጉሥ እልክሃለሁ።” ሙሴ ግን እግዚአብሔርን “ወደ ፈርዖን ሄጄ የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ለማውጣት እኔ ማን ነኝ?” አለ። እግዚአብሔርም መልሶ “አይዞህ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔ እንደ ላክኹህም ምልክት የሚሆንህ ይህ ነው፤ ሕዝቤን ከግብጽ በምታወጣበት ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እኔን ታመልኩኛላችሁ” አለው። ሙሴም “እኔ ወደ እስራኤል ሕዝብ ሄጄ ‘የቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል’ በምላቸው ጊዜ እነርሱ ‘ስሙ ማን ነው?’ ብለው ቢጠይቁኝ ምን እመልስላቸዋለሁ?” አለ። እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እኔ ‘ያለሁና የምኖር ነኝ፤’ ስለዚህም ‘እኔ ነኝ’ ወደ እናንተ ልኮኛል” በላቸው፤ እግዚአብሔርም እንደገና ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ የአባቶቻችሁ የአብርሃም፥ የይስሐቅ፥ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛል፤ ይህ የዘለዓለም ስሜ ነው፤ በዚህም ስም ከትውልድ እስከ ትውልድ እታወቃለሁ። እንግዲህ ሂድና የእስራኤልን ሕዝብ አለቆች ሁሉ በአንድነት ሰብስብ፤ የቀድሞ አባቶቻቸው የአብርሃም የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እኔ እግዚአብሔር የተገለጥኩልህ መሆኔንም ንገራቸው፤ ወደ እነርሱ ወርጄ ግብጻውያን በእነርሱ ላይ ያደረሱባቸውን ግፍና ጭቈና መመልከቴን ንገራቸው። በግፍ ጭቈና ከሚሠቃዩባት ከግብጽ ምድር አውጥቼ እነሆ ዛሬ፥ ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን የሚኖሩባትን፥ በማርና በወተት የበለጸገች ሰፊና ለም የሆነች ምድር ልሰጣቸው ቃል ገብቻለሁ።

ዘፀአት 3:7-17 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታም አለ፦ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ በአስገባሪዎቻቸውም ምክንያት የሚጮሁትን ጩኸት ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ። ከግብፃውያን እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወደ መልካምና ሰፊ አገር፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ከነዓናውያን፥ ሒቲያውያን፥ ኤሞራውያን፥ ፌርዛውያን፥ ሒዊያውያን፥ የቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ። አሁን ደግሞ የእስራኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ መጣ፤ ግብፃውያን የሚያደርጉባቸውን ግፍ ደግሞ አየሁ። ስለዚህ ሂድ፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ እንድታወጣ ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ።” ሙሴም እግዚአብሔርን፦ “ወደ ፈርዖን የምሄድና የእስራኤልንም ልጆች ከግብጽ የማወጣ እኔ ማን ነኝ?” አለው። እርሱም፦ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ይሆናል፤ ሕዝቡን ከግብጽ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታገለግላላችሁ” አለ። ሙሴም እግዚአብሔርን፦ “እኔ ወደ እስራኤል ልጆች ሄጄ፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ’ ባልሁ ጊዜ፦ ‘ስሙ ማን ነው?’ ቢሉኝ፥ ምን እላቸዋለሁ?” አለው። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ “የምኖር እኔ ነኝ” አለው፤ ስለዚህ ለእስራኤል ልጆች፦ “‘የምኖር’ ወደ እናንተ ላከኝ በላቸው” አለው። እግዚአብሔርም ደግሞ ሙሴን አለው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ፦ ‘ጌታ የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ፤’ ይህ ለዘለዓለሙ ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።” ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ትሰበስባለህ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ “ጌታ የአባቶቻችሁ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ፥ የያዕቆብም ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ ‘ጎበኘኋችሁ፥ በግብጽም የሚደረግባችሁን አየሁ፤ ከግብጽም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ።’