ዘፀአት 29:38-39
ዘፀአት 29:38-39 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“በመሠዊያውም ላይ የምታቀርበው ይህ ነው፤ በቀን በቀን ዘወትር በመሠዊያው ላይ ሁለት ንጹሓን የዓመት ጠቦቶች ታቀርባለህ። አንዱን ጠቦት በነግህ፥ ሁለተኛውንም ጠቦት በሠርክ መሥዋዕት አድርገህ ታቀርበዋለህ።
Share
ዘፀአት 29 ያንብቡዘፀአት 29:38-39 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“በየዕለቱ ያለ ማቋረጥ በመሠዊያው ላይ የምታቀርበው ይህ ነው፤ ዓመት የሞላቸው ሁለት የበግ ጠቦቶች፤ አንዱን በማለዳ፣ ሌላውን በምሽት አቅርብ።
Share
ዘፀአት 29 ያንብቡዘፀአት 29:38-39 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በመሠዊያውም ላይ የምታቀርበው ይህ ነው፤ በቀን በቀን ዘወትር ሁለት የዓመት ጠቦቶች ታቀርባለህ። አንዱን ጠቦት በማለዳ ቍርባን አድርገህ ታቀርበዋለህ፤ ሁለተኛውንም ጠቦት በማታ ቍርባን አድርገህ ታቀርበዋለህ።
Share
ዘፀአት 29 ያንብቡ