ዘፀአት 25:30-33
ዘፀአት 25:30-33 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በገበታም ላይ ኅብስተ ገጹን ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ። “መቅረዝንም ከጥሩ ወርቅ አድርግ፤ የመቅረዙም እግሩና ቅርንጫፎቹ የተቀጠቀጠ ሥራ ይሁን፤ ጽዋዎቹም፥ ጕብጕቦቹም፥ አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት። በስተጐኑ ስድስት ቅርንጫፎች ይውጡለት፤ ሦስት የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስትም የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ ወገን ይውጡ። በአንደኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕብና አበባ፥ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፤ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕብና አበባ፥ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፤ እንዲሁም ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስት ቅርንጫፎች አድርግ።
ዘፀአት 25:30-33 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በማንኛውም ጊዜ በፊቴ እንዲሆን በገጸ ኅብስቱ በዚህ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጥ። “ከንጹሕ ወርቅ መቅረዝ ሥራ፤ መቆሚያና ዘንግ አብጅለት፤ ጽዋ መሰል አበባዎች፣ እንቡጦችና የፈነዱ አበባዎች ከመቅረዙ ጋራ ወጥ ሆነው ይሠሩ። ከመቅረዙ ግራና ቀኝ ጐን ጋራ የተያያዙ፣ በአንዱ በኩል ሦስት በሌላው በኩል ሦስት በድምሩ ስድስት ቅርንጫፎች ይኑሩት። ከመቅረዙ ጋራ የተያያዙት ስድስቱ ቅርንጫፎች እያንዳንዳቸው እንቡጥና ቀንበጥ ያሏቸው የለውዝ አበባ ቅርጽ ያሏቸው ሦስት ጽዋ መሰል አበባዎች ጋራ ያኑሯቸው።
ዘፀአት 25:30-33 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በገበታም ላይ የገጽ ኅብስት ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ። መቅረዝንም ከጥሩ ወርቅ አድርግ፤ መቅረዙ ከእግሩና ከአገዳው ጋር በተቀጠቀጠ ሥራ ይደረግ፤ ጽዋዎቹም ጕብጕቦቹም አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት። በስተጎኑ ስድስት ቅርንጫፎች ይውጡለት፤ ሦስት የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስትም የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ ወገን ይውጡ። በአንደኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕብና አበባ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕብና አበባ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፤ እንዲሁም ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አድርግ።
ዘፀአት 25:30-33 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ጠረጴዛውም በታቦቱ ፊት ለፊት ይቀመጥ፤ ለእኔ የሚቀርበው የተቀደሰ ኅብስት ዘወትር በጠረጴዛው ላይ መኖር አለበት። “ከንጹሕም ወርቅ መቅረዝ ሥራ፤ የመቅረዙን መሠረትና ዘንግ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፤ ለጌጥ የሚሠሩት የአበባዎች ወርድ እንቡጦችና ቀንበጦች ጨምሮ ከእርሱ ጋር አንድ ሆነው ይሠሩ። በስተጐኑ ስድስት ቅርንጫፎች አውጣለት፤ ይኸውም ሦስቱ በአንድ ጐን ሲሆኑ፥ ሦስቱ ደግሞ በሌላ ጐን ይሁኑ። ስድስቱም ቅርንጫፎች እያንዳንዳቸው እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስል ሦስት የአበባ ወርድ ጌጥ ይኑራቸው።
ዘፀአት 25:30-33 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በገበታው ላይ ኅብስተ ገጹን ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ። “ከንጹሕ ወርቅ መቅረዝ ሥራ፤ መቅረዙ የተቀጠቀጠ ሥራ ይሁን፤ እግሩና ከአገዳው ጋር ጽዋዎቹም ጉብጉቦቹም አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት። በስተጎኑ ስድስት ቅርንጫፎች ይውጡለት፤ ሦስት የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስት የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ ወገን ይውጡ። በአንደኛው ቅርንጫፍ እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች አድርግ፤ እንዲሁም ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አድርግ።