ዘፀአት 24:13-15
ዘፀአት 24:13-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሙሴም ከኢያሱ ጋር ተነሣ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራም ወጡ። ሽማግሌዎችንም፥ “ወደ እናንተ እስክንመለስ ድረስ በዚህ ቈዩን፤ ግርግር አትበሉ፤ አሮንና ሆርም እነሆ፥ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ ነገረተኛም ቢኖር ወደ እነርሱ ይሂድ” አላቸው። ሙሴም ከኢያሱ ጋር ወደ ተራራ ወጣ፤ ደመናውም ተራራውን ሸፈነው።
Share
ዘፀአት 24 ያንብቡዘፀአት 24:13-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም ሙሴ ከረዳቱ ከኢያሱ ጋር አብሮ ሄደ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ተራራ ወጣ። እርሱም ሽማግሌዎችን “ወደ እናንተ እስክንመለስ ድረስ በዚህ ቈዩ፤ አሮንና ሖር ከእናንተ ጋር ናቸው፤ ክርክር ያለው ሰው ቢኖር ወደ እነርሱ ይሂድ።” አላቸው። ሙሴ ወደ ተራራ ሲወጣ ደመናው ተራራውን ሸፈነ፤
Share
ዘፀአት 24 ያንብቡዘፀአት 24:13-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሙሴና ሎሌው ኢያሱ ተነሡ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወጣ። ሽማግሌዎችንም፦ ወደ እናንተ እስክንመለስ ድረስ በዚህ ቆዩን፤ አሮንና ሖርም እነሆ ከእናንተ ጋር ናቸው፥ ነገረተኛም ቢኖር ወደ እነርሱ ይምጣ አላቸው። ሙሴም ወደ ተራራ ወጣ፥ ደመናውም ተራራውን ሸፈነው።
Share
ዘፀአት 24 ያንብቡ