ዘፀአት 2:3-4
ዘፀአት 2:3-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ደግሞም ሊሸሽጉት በአልቻሉ ጊዜ እናቱ የደንገል ሣጥን ለእርሱ ወስዳ ዝፍትና ቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም አኖረችበት፤ በወንዝም ዳር ባለ በቄጠማ ውስጥ አስቀመጠችው። እኅቱም ምን እንደሚደርስበት ታውቅ ዘንድ በሩቅ ቆማ ትጐበኘው ነበር።
ያጋሩ
ዘፀአት 2 ያንብቡዘፀአት 2:3-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያ በላይ ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ ግን የደንገል ቅርጫት ወስዳ፣ በዝፍትና በቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም በውስጡ አስተኝታ ቅርጫቱን አባይ ወንዝ ዳር ቄጠማ መካከል አስቀመጠችው። የሕፃኑም እኅት የሚደርስበትን ነገር ለማወቅ ራቅ ብላ ቆማ ታይ ነበር።
ያጋሩ
ዘፀአት 2 ያንብቡዘፀአት 2:3-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ደግሞም ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ፥ የደንገል ሣጥን ለእርሱ ወስዳ ዝፍትና ቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም አኖረችበት፤ በወንዝም ዳር ባለ በቄጠማ ውስጥ አስቀመጠችው። እኅቱም የሚደርስበትን ታውቅ ዘንድ በሩቅ ቆማ ትመለከት ነበር።
ያጋሩ
ዘፀአት 2 ያንብቡ