የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 2

2
የሙሴ ልደት
1ከሌዊ ወገን እን​በ​ረም የሚ​ባል አንድ ሰው ነበረ፤ እር​ሱም ከሌዊ ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን አገባ። 2ሴቲ​ቱም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ መል​ካ​ምም እን​ደ​ሆነ በአዩ ጊዜ ሦስት ወር ሸሸ​ጉት። 3ደግ​ሞም ሊሸ​ሽ​ጉት በአ​ል​ቻሉ ጊዜ እናቱ የደ​ን​ገል ሣጥን ለእ​ርሱ ወስዳ ዝፍ​ትና ቅጥ​ራን ለቀ​ለ​ቀ​ችው፤ ሕፃ​ኑ​ንም አኖ​ረ​ች​በት፤ በወ​ን​ዝም ዳር ባለ በቄ​ጠማ ውስጥ አስ​ቀ​መ​ጠ​ችው። 4እኅ​ቱም ምን እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስ​በት ታውቅ ዘንድ በሩቅ ቆማ ትጐ​በ​ኘው ነበር። 5የፈ​ር​ዖ​ንም ሴት ልጅ ልት​ታ​ጠብ ወደ ወንዝ ወረ​ደች፤ ደን​ገ​ጥ​ሮ​ች​ዋም በወ​ንዝ ዳር ይሄዱ ነበር፤ ሣጥ​ኑ​ንም በቄ​ጠማ ውስጥ አየች፤ ደን​ገ​ጥ​ር​ዋ​ንም ልካ አስ​መ​ጣ​ችው። 6ሣጥ​ኑን በከ​ፈ​ተ​ችም ጊዜ ሕፃ​ኑን አየች፤ እነ​ሆም፥ ሕፃኑ በሣ​ጥኑ ውስጥ ያለ​ቅስ ነበር፤ የፈ​ር​ዖ​ንም ልጅ አዘ​ነ​ች​ለት፥ “ይህ ሕፃን ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ልጆች አንዱ ነው” አለች። 7የዚ​ያም ሕፃን እኅት ለፈ​ር​ዖን ልጅ፥ “ሕፃ​ኑን ታጠ​ባ​ልሽ ዘንድ ሄጄ የም​ታ​ጠባ ሴት ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሴቶች ልጥ​ራ​ል​ሽን?” አለ​ቻት። 8የፈ​ር​ዖ​ንም ልጅ፥ “ሂጂና ጥሪ​ልኝ” አለ​ቻት፤ ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም ሄዳ የሕ​ፃ​ኑን እናት ጠራች። 9የፈ​ር​ዖ​ንም ልጅ፥ “ይህን ሕፃን ተን​ከ​ባ​ክ​በሽ አጥ​ቢ​ልኝ፤ ዋጋ​ሽ​ንም እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ” አለ​ቻት። ሴቲ​ቱም ሕፃ​ኑን ወስዳ አጠ​ባ​ችው። 10ሕፃ​ኑም በአ​ደገ ጊዜ ወደ ፈር​ዖን ልጅ ወሰ​ደ​ችው፤ ለእ​ር​ስ​ዋም ልጅ ሆነ​ላት። እኔ ከውኃ አው​ጥ​ቼ​ዋ​ለ​ሁና ስት​ልም ስሙን ሙሴ ብላ ጠራ​ችው ።
ሙሴ ወደ ምድ​ያም እንደ ሸሸ
11ከብዙ ቀን በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ ሙሴ አደገ፤ ወደ ወን​ድ​ሞ​ቹም ወጣ፤ መከ​ራ​ቸ​ው​ንም ተመ​ለ​ከተ፤ የግ​ብ​ፅም ሰው ከወ​ን​ድ​ሞቹ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አን​ዱን ዕብ​ራዊ ሰው ሲመታ አየ። 12ወዲ​ህና ወዲያ ተመ​ለ​ከተ፤ ማን​ንም አላ​የም፤ ግብ​ፃ​ዊ​ው​ንም ገደ​ለው፤ በአ​ሸዋ ውስ​ጥም ቀበ​ረው። 13በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ወጣ፤ ሁለ​ቱም የዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሰዎች ሲጣሉ አየ፤ ሙሴም በዳ​ዩን፥ “ለምን ባል​ን​ጀ​ራ​ህን ትመ​ታ​ዋ​ለህ?” አለው። 14ወን​ድ​ሙን የሚ​በ​ድ​ለው ያም ሰው፥ “በእኛ ላይ አን​ተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደ​ረ​ገህ? ወይስ ግብ​ፃ​ዊ​ውን ትና​ንት እንደ ገደ​ል​ኸው ልት​ገ​ድ​ለኝ ትሻ​ለ​ህን?” አለው። ሙሴም፥ “በእ​ው​ነት ይህ ነገር ታው​ቆ​አ​ልን?” ብሎ ፈራ። 15ፈር​ዖ​ንም ይህን ነገር ሰማ፤ ሙሴ​ንም ሊገ​ድ​ለው ፈለገ። ሙሴ ግን ከፈ​ር​ዖን ፊት ኰበ​ለለ፤ በም​ድ​ያ​ምም ምድር ተቀ​መጠ፤ ወደ ምድ​ያም ምድር በደ​ረሰ ጊዜም በው​ኃው ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ዐረፈ።
16ለም​ድ​ያ​ምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ው​ንም የዮ​ቶ​ርን በጎች ይጠ​ብቁ ነበር፤ እነ​ር​ሱም መጥ​ተው ውኃ ቀዱ፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ው​ንም የዮ​ቶ​ርን በጎች ሊያ​ጠጡ የው​ኃ​ዉን ገንዳ ሞሉ። 17እረ​ኞ​ችም መጥ​ተው ገፉ​አ​ቸው፤ ሙሴ ግን ተነ​ሥቶ አዳ​ና​ቸው፤ እየ​ቀ​ዳም በጎ​ቻ​ቸ​ዉን አጠ​ጣ​ላ​ቸው። 18ወደ አባ​ታ​ቸ​ውም ወደ ራጉ​ኤል መጡ እር​ሱም፥ “ዛሬስ እን​ዴት ፈጥ​ና​ችሁ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው። 19እነ​ር​ሱም፥ “አንድ የግ​ብፅ ሰው ከእ​ረ​ኞች እጅ አዳ​ነን፤ ደግ​ሞም ቀዳ​ልን፤ በጎ​ቻ​ች​ን​ንም አጠ​ጣ​ልን” አሉት። 20ልጆ​ቹ​ንም፥ “ሰው​ዬው ወዴት ነው? ለም​ንስ ያን ሰው ተዋ​ች​ሁት? ጥሩት፤ እን​ጀ​ራም ይብላ” አላ​ቸው። 21ሙሴም ከዚያ ሰው ጋር ሊቀ​መጥ ወደደ፤ ልጁ​ንም ሲፓ​ራን ለሙሴ ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው። 22ያችም ሴት ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ ሙሴም፥ “በሌላ ምድር መጻ​ተኛ ነኝ” ሲል ስሙን ጌር​ሳም ብሎ ጠራው። ዳግ​መ​ኛም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ኤል​ኤ​ዜር አለው፤ የአ​ባቴ ፈጣሪ ረዳቴ ነው ሲል።#“ዳግ​መ​ኛም ፀነ​ሰች ፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች ፤ ስሙ​ንም ኤል​ኤ​ዜር አለው ፤ የአ​ባቴ ፈጣሪ ረዳቴ ነው ሲል” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም።
23ከዚ​ያም ከብዙ ቀን በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የግ​ብፅ ንጉሥ ሞተ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከባ​ር​ነት የተ​ነሣ አለ​ቀሱ፤ ጮኹም፤ ስለ ባር​ነ​ታ​ቸ​ውም ጩኸ​ታ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወጣ። 24እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ብ​ር​ሃ​ምና ከይ​ስ​ሐቅ፥ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ጋር ያደ​ረ​ገ​ውን ቃል ኪዳን ዐሰበ። 25እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ጐበ​ኛ​ቸው፤ ታወ​ቀ​ላ​ቸ​ውም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ