1
ኦሪት ዘፀአት 2:24-25
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እግዚአብሔርም ጩኸታቸውን ሰማ፤ እግዚአብሔርም ከአብርሃምና ከይስሐቅ፥ ከያዕቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን ዐሰበ። እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች ጐበኛቸው፤ ታወቀላቸውም።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ኦሪት ዘፀአት 2:23
ከዚያም ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ልጆች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፤ ጮኹም፤ ስለ ባርነታቸውም ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።
3
ኦሪት ዘፀአት 2:10
ሕፃኑም በአደገ ጊዜ ወደ ፈርዖን ልጅ ወሰደችው፤ ለእርስዋም ልጅ ሆነላት። እኔ ከውኃ አውጥቼዋለሁና ስትልም ስሙን ሙሴ ብላ ጠራችው ።
4
ኦሪት ዘፀአት 2:9
የፈርዖንም ልጅ፥ “ይህን ሕፃን ተንከባክበሽ አጥቢልኝ፤ ዋጋሽንም እሰጥሻለሁ” አለቻት። ሴቲቱም ሕፃኑን ወስዳ አጠባችው።
5
ኦሪት ዘፀአት 2:5
የፈርዖንም ሴት ልጅ ልትታጠብ ወደ ወንዝ ወረደች፤ ደንገጥሮችዋም በወንዝ ዳር ይሄዱ ነበር፤ ሣጥኑንም በቄጠማ ውስጥ አየች፤ ደንገጥርዋንም ልካ አስመጣችው።
6
ኦሪት ዘፀአት 2:11-12
ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ አደገ፤ ወደ ወንድሞቹም ወጣ፤ መከራቸውንም ተመለከተ፤ የግብፅም ሰው ከወንድሞቹ ከእስራኤል ልጆች አንዱን ዕብራዊ ሰው ሲመታ አየ። ወዲህና ወዲያ ተመለከተ፤ ማንንም አላየም፤ ግብፃዊውንም ገደለው፤ በአሸዋ ውስጥም ቀበረው።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች