የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

አስቴር 2:15-18

አስቴር 2:15-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በዚህ ዐይነት አስቴር ወደ ንጉሡ ፊት የምትቀርብበት ጊዜ ደረሰ፤ ይህችም አስቴር የአቢኀይል ልጅ፥ እንደ ልጁ አድርጎ ያሳደጋት የመርዶክዮስ የአጐት ልጅ የነበረችውና ባያት ሁሉ ዘንድ ሞገስን ያገኘች ነበረች፤ እርስዋም ወደ ንጉሡ ፊት የመቅረብ ተራዋ በደረሰ ጊዜ የለበሰችው፥ የምርጥ ሴቶች መኖሪያ ቤት ኀላፊ የነበረው ጃንደረባው ሄጋይ እንድትለብስ የመከራትን እንጂ እርስዋ የጠየቀችውን ልብስ አልነበረም። ስለዚህም አርጤክስስ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ቴቤት ተብሎ በሚጠራው በዐሥረኛው ወር አስቴር ወደ ቤተ መንግሥቱ ተወሰደች። ንጉሡም ከሌሎቹ ልጃገረዶች ሁሉ አስበልጦ ወደዳት፤ ከሌሎቹም ሁሉ ይበልጥ በፊቱ ሞገስንና መወደድን አገኘች፤ እርሱም መንግሥታዊውን ዘውድ አንሥቶ በራስዋ ላይ ደፋላትና በአስጢን ቦታ አነገሣት። ከዚህም በኋላ ንጉሡ ስለ አስቴር ክብር ታላቅ ግብዣ አዘጋጅቶ ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለሥልጣኖችና አስተዳዳሪዎች ሁሉ ጠራ፤ በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት በሚገኙት አገሮች ሁሉ የደስታ በዓል እንዲደረግ ዐወጀ፤ ለጋስነት የተሞላበት ንጉሣዊ ስጦታም አደረገ።