የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኤፌሶን 2:1-8

ኤፌሶን 2:1-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እና​ን​ተም በኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ምው​ታን ሆና​ችሁ ነበር። ይኸ​ውም ቀድሞ በዚህ ዓለም ሥር​ዐት፥ አሁን በከ​ሓ​ድ​ያን ልጆች የሚ​በ​ረ​ታ​ታ​ባ​ቸ​ውና፥ በነ​ፋስ አም​ሳል የሚ​ገ​ዛ​ቸው አለቃ እንደ ነበ​ረው ፈቃድ ጸን​ታ​ችሁ የነ​በ​ራ​ች​ሁ​በት ነው። እኛ ሁላ​ችን ቀድሞ እንደ ሥጋ​ችን ምኞት ኖርን፤ የሥ​ጋ​ች​ን​ንም ፈቃ​ድና ያሰ​ብ​ነ​ውን አደ​ረ​ግን፤ እንደ ሌሎች ኃጥ​አ​ንም ሁሉ የጥ​ፋት ልጆች ሆንን። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በም​ሕ​ረቱ ባለ​ጸ​ግ​ነ​ትና በወ​ደ​ደን በፍ​ቅሩ ብዛት፥ በኃ​ጢ​አ​ታ​ችን የሞ​ትን ሳለን በክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወ​ትን ሰጠን፤ በጸ​ጋ​ውም ዳንን። በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም አስ​ነ​ሥቶ በሰ​ማ​ያት ከእ​ርሱ ጋር አኖ​ረን። በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ይቅር ስላ​ለን የጸ​ጋ​ውን ባለ​ጠ​ግ​ነት ብዛት በሚ​መ​ጣው ዓለም ይገ​ልጥ ዘንድ፥ አም​ነን በጸ​ጋው ድነ​ና​ልና፤ ይህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ነው እንጂ የእ​ና​ንተ ሥራ አይ​ደ​ለም።

ኤፌሶን 2:1-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እናንተ በበደላችሁና በኀጢአታችሁ ምክንያት ሙታን ነበራችሁ፤ በዚህም፣ የዓለምን ክፉ መንገድ ተከትላችሁ፣ በአየር ላይ ላሉት መንፈሳውያን ኀይላት ገዥ ለሆነውና አሁንም ለእግዚአብሔር በማይታዘዙት ሰዎች ላይ ለሚሠራው መንፈስ እየታዘዛችሁ ትኖሩ ነበር። እኛ ሁላችን በአንድ ወቅት የሥጋችንን ምኞት እያረካን፣ መንገዱንም እየተከተልን በመካከላቸው እንኖር ነበር፤ እንደ ሌሎቹም የቍጣ ልጆች ነበርን። ነገር ግን በምሕረቱ ባለጠጋ የሆነ እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ፣ በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለ፣ በክርስቶስ ሕያዋን አደረገን፤ የዳናችሁት በጸጋ ነው። እግዚአብሔርም ከክርስቶስ ጋር አስነሣን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን፤ ይኸውም በሚመጣው ዘመን በክርስቶስ ኢየሱስ በቸርነቱ የገለጠልንን ወደር የሌለውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ነው፤ በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤

ኤፌሶን 2:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን። ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም።

ኤፌሶን 2:1-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እናንተ በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ምክንያት በመንፈሳዊ ኑሮአችሁ የሞታችሁ ነበራችሁ፤ በዚያን ጊዜ የዚህን ዓለም ክፉ አካሄድ ትከተሉ ነበር፤ እንዲሁም በአየር ላይ ያሉትን የመናፍስት ኀይሎች ለሚገዛው ትታዘዙ ነበር፤ እርሱ በማይታዘዙት ሰዎች ላይ የሚሠራ ርኩሱ መንፈስ ነው። እኛም ሁላችን ከዚህ በፊት በእነርሱ መካከል የሥጋችንን ፈቃድና የአእምሮአችንን ሐሳብ እየተከተልን በሥጋችን ምኞት እንኖር ነበር፤ እንደ ሌሎቹም በተፈጥሮአችን በእግዚአብሔር ቊጣ ሥር ነበርን። ነገር ግን የእግዚአብሔር ምሕረቱ ብዙ ከመሆኑና ለእኛም ያለው ፍቅር ታላቅ ከመሆኑ የተነሣ በበደላችን የሞትን ብንሆንም እንኳ እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር እንድንኖር አድርጎናል፤ እናንተም የዳናችሁት በጸጋው ነው። እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት ከእርሱው ጋር ከሞት አስነሥቶ በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ይህንንም ያደረገው በኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የገለጠውን ቸርነትና ወደር የሌለውን የጸጋውን ብልጽግና በሚመጡት ዘመናት ሊያሳየን ብሎ ነው። እናንተ የዳናችሁት በእምነት አማካይነት በጸጋው ነው፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ በእናንተ ሥራ የተገኘ አይደለም።

ኤፌሶን 2:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እናንተ በበደላችሁና በኀጢአታችሁ ምክንያት ሙታን ነበራችሁ፤ በዚህም የዚህን ዓለም አኗኗር በመከተል፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው፥ በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ እየታዘዛችሁ ትኖሩ ነበር። በእነዚህም ልጆች መካከል እኛም ሁላችን፥ የሥጋችንንና የህዋሳቶቻችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበር፤ ደግሞም እንደ ሌሎቹ በባሕርያችን የቁጣ ልጆች ነበርን። ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ እኛን ከወደደበት ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ፥ በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለን ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፤ የዳናችሁት በጸጋ ነው። ደግሞም ከክርስቶስ ጋር አስነሣን፤ በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን፤ ይኸውም በሚመጣው ዘመን በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት መለኪያ የሌለውን የጸጋውን ባለጠግነት ሊያሳይ ነው። ጸጋው በእምነት አድኗችኋልና፤ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ የመጣም አይደለም።