ዘዳግም 23:1-11

ዘዳግም 23:1-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“ፍሬ ዘሩ የተ​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ አባለ ዘሩም የተ​ቈ​ረጠ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ። ዲቃላ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ፤ “አሞ​ናዊ ወይም ሞዓ​ባዊ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ፤ እስከ ዐሥር ትው​ልድ ድረስ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ። ከግ​ብፅ በወ​ጣ​ችሁ ጊዜ እን​ጀ​ራና ውኃ ይዘው በመ​ን​ገድ ላይ አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ች​ሁ​ምና፥ ከመ​ስ​ጴ​ጦ​ምያ የቢ​ዖ​ርን ልጅ በለ​ዓ​ምን ዋጋ ሰጥ​ተው ይረ​ግ​ማ​ችሁ ዘንድ ተዋ​ው​ለ​ው​ባ​ች​ኋ​ልና። ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በለ​ዓ​ምን ይሰማ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወድ​ዶ​ሃ​ልና ርግ​ማ​ኑን ወደ በረ​ከት ለወ​ጠ​ልህ። በዘ​መ​ንህ ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሰላም እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ቸው አታ​ና​ግ​ራ​ቸው። “ኤዶ​ማ​ዊዉ ወን​ድ​ምህ ነውና አት​ጸ​የ​ፈው፤ ግብ​ፃ​ዊ​ዉ​ንም በሀ​ገሩ ስደ​ተኛ ነበ​ር​ህና አት​ጸ​የ​ፈው። ከእ​ነ​ር​ሱም በሦ​ስ​ተ​ኛው ትው​ልድ የሚ​ወ​ለዱ ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይግቡ። “ጠላ​ቶ​ች​ህን ልት​ወጋ በወ​ጣህ ጊዜ ከክፉ ነገር ሁሉ ሰው​ነ​ት​ህን ጠብቅ። በእ​ና​ንተ ውስጥ ሌሊት በሚ​ሆ​ነው ርኵ​ሰት የረ​ከሰ ሰው ቢኖር፥ ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ይውጣ፤ ወደ ሰፈ​ርም አይ​ግባ። በመ​ሸም ጊዜ ሰው​ነ​ቱን በውኃ ይታ​ጠብ፤ ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ወደ ሰፈር ይመ​ለስ።

ዘዳግም 23:1-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ብልቱ የተቀጠቀጠ ወይም የተቈረጠ ማንኛውም ሰው ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። ዲቃላም ይሁን የዲቃላው ዘር የሆነ ሁሉ፣ እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማንኛውም የርሱ ዘር፣ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳ ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። ምክንያቱም ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በጕዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህል ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም፤ በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖር ልጅ በለዓምን አንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዙት። ይሁን እንጂ አምላክህ እግዚአብሔር በለዓምን አልሰማውም፤ አምላክህ እግዚአብሔር ስለሚወድድህ ርግማኑን በረከት አደረገልህ። በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ሰላምን ለእነርሱ አትመኝ። ወንድምህ ስለ ሆነ ኤዶማዊውን አትጸየፈው፤ መጻተኛ ሆነህ በአገሩ ኖረሃልና ግብጻዊውን አትጥላው። ለእነርሱ የተወለዱላቸው የሦስተኛው ትውልድ ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ መግባት ይችላሉ። ጠላትህን ለመውጋት ወጥተህ በሰፈርህ ጊዜ፣ ከማናቸውም ርኩሰት ራስህን ጠብቅ። ከመካከላችሁ ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከሰ ሰው ቢኖር፣ ከሰፈር ወጥቶ እዚያው ይቈይ። እየመሸ ሲመጣ ግን ገላውን ይታጠብ፤ ፀሓይ ስትጠልቅም ወደ ሰፈሩ ይመለስ።

ዘዳግም 23:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ቍላው የተቀጠቀጠ ብልቱም የተቈረጠ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። ዲቃላ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ፤ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ እንጀራና ውኃ ይዘው በመንገድ ላይ አልተቀበሉአችሁምና፥ በመስጴጦምያ ካለው ከፋቱራ የቢዖርን ልጅ በለዓምን ዋጋ ሰጥተው ይረግምህ ዘንድ አምጥተውብሃልና አሞራዊና ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ፤ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ለዘላለም ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር በለዓምን ይሰማ ዘንድ አልወደደም፤ አምላክህም እግዚአብሔር ወድዶሃልና እርግማኑን በረከት አደረገልህ። በዘመንህ ሁሉ ለዘላለም ሰላምና ልማት ለእነርሱ አትሻ። ኤዶማዊ ወንድምህ ነውና አትጸየፈው፤ ግብፃዊውንም በአገሩ ስደተኛ ነበርህና አትጸየፈው። ከእነርሱም በሦስተኛው ትውልድ የሚወለዱ ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ይግቡ። ጠላቶችህን ልትወጋ በወጣህ ጊዜ ከክፉ ነገር ሁሉ ሰውነትህን ጠብቅ። በእናንተ መካከል ሌሊት በሚሆነው ርኩሰት የረከስ ሰው ቢኖር፥ ከሰፈር ወደ ውጭ ይውጣ፥ ወደ ሰፈርም አይግባ። በመሸም ጊዜ በውኃ ይታጠብ፤ ፀሐይም በገባ ጊዜ ወደ ሰፈር ይመለስ።

ዘዳግም 23:1-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“የተኰላሸ ወይም የተሰለበ ሰው የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ አባል አይሁን። “ከጋብቻ ውጪ ዲቃላ ሆኖ የተወለደና የእርሱም ዘር ሆኖ የተወለደ ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳ ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ ገብቶ አይቈጠር። “ዐሞናዊም ሆነ ሞአባዊ ወይም የእነርሱ ዘር የሆነ ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳ የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ አባል አይሁን። እናንተ ከግብጽ ምድር ወጥታችሁ በጒዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እነርሱ እህልና ውሃ አንሰጥም ብለው ከልክለዋችሁ እንደ ነበር አይዘነጋም፤ ከዚሁም ጋር በመስጴጦምያ ፐቶር ተብላ በምትጠራው ከተማ ይኖር የነበረ የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲረግማችሁ ቀጥረውት ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክህ እርሱን ማዳመጥ አልፈለገም፤ ይልቁንም እግዚአብሔር አንተን ስለሚወድህ መርገሙን ወደ በረከት ለወጠው። እግዚአብሔር እናንተን ይወዳችኋል። በምትኖርበት ዘመን ሁሉ እነዚህ ሕዝቦች ባለጸጎች ሆነው በሰላም እንዲኖሩ አትርዳቸው። “ኤዶማውያን ዘመዶችህ ስለ ሆኑ አትጸየፋቸው፤ በግብጽ ምድር ስደተኛ ሆነህ ስለ ኖርክ ግብጻውያንን አትጸየፋቸው። የእነርሱም ከሦስተኛው ትውልድ በኋላ ዘሮቻቸው የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ አባሎች ይሁኑ። “በጦርነት ጊዜ በጦር ሰፈር ውስጥ ስትገኙ፥ ርኩስ ነገርን ሁሉ አስወግዱ። አንድ ሰው ሌሊት በሕልሙ ከአባለ ዘሩ የፈሰሰ እርጥበት በሰውነቱ ላይ ቢገኝ ከሰፈር ወጥቶ በዚያው ይቈይ። ወደ ማታም ጊዜ ገላውን ይታጠብ፤ ጀንበር ስትጠልቅም ወደ ሰፈር ይመለስ።

ዘዳግም 23:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“የተኰላሸ ወይም ብልቱም የተሰለበ ሰው ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ። “ከጋብቻ ውጪ የተወለደ ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ፤ እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ። “አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማናቸውም የእርሱ ዘር፥ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳን ቢሆን ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ። ምክንያቱም ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በጉዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህል ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም፤ በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምም አንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዝተውት ነበር። ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር በለዓምን መስማት አልፈለገም፥ ጌታ እግዚአብሔር ወድዶሃልና እርግማኑን በረከት አደረገልህ። በዘመንህ ሁሉ ለዘለዓለም ሰላምና ልማት ለእነርሱ አትሻ። “ኤዶማዊ ወንድምህ ነውና አትጸየፈው፥ ግብፃዊውንም በአገሩ ስደተኛ ነበርህና አትጸየፈው። ከእነርሱም በሦስተኛው ትውልድ የሚወለዱ ልጆች ወደ ጌታ ጉባኤ ይግቡ።” “ጠላቶችህን ልትወጋ በወጣህ ጊዜ ከክፉ ነገር ሁሉ ሰውነትህን ጠብቅ። ከእናንተ መካከል ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከሰ ሰው ቢኖር ከሰፈር ወደ ውጭ ይውጣ፥ እዚያው ይቆይ። በመሸም ጊዜ በውኃ ይታጠብ፥ ፀሐይም በገባ ጊዜ ወደ ሰፈር ይመለስ።