የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

አሞጽ 5:1-27

አሞጽ 5:1-27 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በእ​ና​ንተ ላይ ለሙሾ የማ​ነ​ሣ​ውን ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ወደ​ቀች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አት​ነ​ሣም፤ በም​ድ​ርዋ ላይ ተጣ​ለች፤ የሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ትም የለም። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “ሺህ ከሚ​ወ​ጡ​ባት ከተማ መቶ ይቀ​ራሉ፤ መቶም ከሚ​ወ​ጡ​ባት ከተማ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ዐሥር ይቀ​ራሉ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “እኔን ፈልጉ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ጌል​ገላ ፈጽሞ ትማ​ረ​ካ​ለ​ችና፥ ቤቴ​ልም እን​ዳ​ል​ነ​በ​ረች ትሆ​ና​ለ​ችና ቤቴ​ልን አት​ፈ​ልጉ፤ ወደ ጌል​ገ​ላም አት​ሂዱ፤ ወደ ቤር​ሳ​ቤ​ህም አት​ለፉ።” በዮ​ሴፍ ቤት እሳት እን​ዳ​ት​ቃ​ጠል፥ እን​ዳ​ት​በ​ላ​ቸ​ውም የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት እሳት የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ላ​ቸው እን​ዳ​ያጡ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈልጉ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ድን በሰ​ማይ ያደ​ር​ጋል፤ ጽድ​ቅ​ንም በም​ድር ላይ ይመ​ሠ​ር​ታል። ሁሉን የሚ​ሠ​ራና የሚ​ያ​ቅ​ናና፥ ብር​ሃ​ኑን ወደ መስዕ የሚ​መ​ል​ሰው፥ ቀኑን እንደ ሌሊት የሚ​ያ​ጨ​ል​መው፥ የባ​ሕ​ሩ​ንም ውኃ ጠርቶ በም​ድር ፊት የሚ​ያ​ፈ​ስ​ሰው ስሙ ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው። በኀ​ያ​ላን ላይ ቅጥ​ቃ​ጤን፥ በአ​ን​ባ​ዎ​ችም ላይ ጕስ​ቍ​ል​ናን ያመ​ጣል። በበሩ የሚ​ገ​ሥ​ጸ​ውን ጠሉ፤ እው​ነ​ት​ንም የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ተጸ​የፉ። ድሃ​ው​ንም ደብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ልና፤ መማ​ለ​ጃ​ንም ከእ​ርሱ ወስ​ዳ​ች​ኋ​ልና፤ ያማሩ ቤቶ​ች​ንም መር​ጣ​ችሁ ሠር​ታ​ች​ኋ​ልና፥ ነገር ግን አት​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ውም፤ ያማሩ የወ​ይን ቦታ​ዎ​ችም ተክ​ላ​ች​ኋል፤ ነገር ግን ወይ​ንን አት​ጠ​ጡም። ጻድ​ቁን የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ ጉቦ​ንም የም​ት​ቀ​በሉ፥ በበ​ሩም የች​ግ​ረ​ኛ​ውን ፍርድ የም​ታ​ጣ​ምሙ እና​ንተ ሆይ! በደ​ላ​ችሁ እን​ዴት እንደ በዛ፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም እን​ዴት እንደ ጸና እኔ ዐው​ቃ​ለ​ሁና። ስለ​ዚህ ዘመኑ ክፉ ነውና በዚያ ዘመን አስ​ተ​ዋይ ዝም ይላል። በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ መል​ካ​ሙን ፈልጉ፤ ክፉ​ው​ንም አይ​ደ​ለም፤ እን​ዲሁ እና​ንተ እንደ ተና​ገ​ራ​ችሁ ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር ይሆ​ናል። ክፉ​ውን ጥሉ፤ መል​ካ​ሙ​ንም ውደዱ፤ በበ​ሩም አደ​ባ​ባይ ፍር​ድን አጽኑ፤ ምና​ል​ባት ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዮ​ሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆ​ናል። ስለ​ዚህ ሁሉን የሚ​ችል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በየ​አ​ደ​ባ​ባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆ​ናል፤ በየ​መ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ላይ ወዮ ወዮ ይባ​ላል፤ ገበ​ሬ​ዎ​ቹም ወደ ልቅሶ፥ አል​ቃ​ሾ​ቹም ወደ ዋይታ ይጠ​ራሉ። በመ​ካ​ከ​ልህ አል​ፋ​ለ​ሁና በጎ​ዳ​ናው ሁሉ ልቅሶ ይሆ​ናል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀን ለም​ት​ፈ​ልጉ ወዮ​ላ​ችሁ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቀን ለምን ትፈ​ል​ጋ​ላ​ችሁ? ጨለማ ነው እንጂ ብር​ሃን አይ​ደ​ለም። ከአ​ን​በሳ ፊት እንደ ሸሸ፥ ድብም እን​ዳ​ገ​ኘው ሰው፥ ወደ ቤትም ገብቶ እጁን በግ​ድ​ግዳ ላይ እን​ዳ​ስ​ደ​ገ​ፈና እባብ እንደ ነደ​ፈው ሰው ይሆ​ናል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ብር​ሃን ሳይ​ሆን ጨለማ አይ​ደ​ለ​ምን? ፀዳል የሌ​ለ​ውም ድቅ​ድቅ ጨለማ አይ​ደ​ለ​ምን? ዓመት በዓ​ላ​ች​ሁን ጠል​ች​ዋ​ለሁ፤ አር​ቄ​ው​ማ​ለሁ፤ መዓዛ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን አላ​ሸ​ትም። የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ና​ች​ሁን ብታ​ቀ​ር​ቡ​ል​ኝም እንኳ አል​ቀ​በ​ለ​ውም፤ የድ​ኅ​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንም አል​መ​ለ​ከ​ትም። የዝ​ማ​ሬ​ህ​ንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፤ የመ​ሰ​ን​ቆ​ህ​ንም ዜማ አላ​ዳ​ም​ጥም። ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድ​ቅም እን​ደ​ማ​ይ​ደ​ርቅ ፈሳሽ ይፍ​ሰስ። “የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በውኑ በም​ድረ በዳ አርባ ዓመት ሙሉ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አቅ​ር​ባ​ች​ሁ​ል​ኛ​ልን? ለራ​ሳ​ች​ሁም የሠ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ውን ምስ​ሎች፥ የሞ​ሎ​ክን ድን​ኳ​ንና የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የሬ​ፋ​ንን ኮከብ አነ​ሣ​ችሁ። ስለ​ዚህ ከደ​ማ​ስቆ ወደ​ዚያ አስ​ማ​ር​ካ​ች​ኋ​ለሁ” ይላል ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የተ​ባለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

አሞጽ 5:1-27 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለ እናንተ የምደረድረውን ይህን የሙሾ ቃል ስሙ፤ “ድንግሊቱ እስራኤል ወደቀች፤ ከእንግዲህም አትነሣም፤ በገዛ ምድሯ ተጣለች፤ የሚያነሣትም የለም።” ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አንድ ሺሕ ብርቱዎችን ለእስራኤል የምታዘምት ከተማ፣ አንድ መቶ ብቻ ይቀሯታል፤ አንድ መቶ ብርቱዎችን የምታዘምተውም፣ ዐሥር ብቻ ይቀሯታል።” እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላል፤ “እኔን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ። ቤቴልን አትፈልጉ፤ ወደ ጌልገላ አትሂዱ፤ ወደ ቤርሳቤህም አትሻገሩ፤ ጌልገላ በርግጥ ትማረካለች፤ ቤቴልም እንዳልነበረች ትሆናለችና።” እግዚአብሔርን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ አለዚያ እንደ እሳት የዮሴፍን ቤት ያወድማል፤ እሳቱም ቤቴልን ይበላል፤ የሚያጠፋውም የለም። እናንተ ፍትሕን ወደ መራርነት የምትለውጡ፣ ጽድቅንም ወደ ምድር የምትጥሉ ወዮላችሁ! ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮንን የሠራ፣ ጨለማውን ወደ ንጋት ብርሃን የሚለውጥ፣ ቀኑን አጨልሞ ሌሊት የሚያደርግ፣ የባሕሩንም ውሃ ጠርቶ፣ በገጸ ምድር ላይ የሚያፈስስ፣ ስሙ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በብርቱው ላይ ድንገተኛ ጥፋትን፣ በተመሸገውም ከተማ ላይ ውድመትን ያመጣል። እናንተ በፍርድ አደባባይ የሚገሥጻችሁን ትጠላላችሁ፤ እውነት የሚናገረውንም ትንቃላችሁ። እናንተ ድኻውን ትረግጣላችሁ፤ እህል እንዲሰጣችሁም ታስገድዱታላችሁ፤ ስለዚህ በተጠረበ ድንጋይ ቤት ብትሠሩም፣ በውስጡ ግን አትኖሩም፤ ባማሩ የወይን ተክል ቦታዎች ወይን ብትተክሉም፣ የወይን ጠጁን ግን አትጠጡም፤ ኀጢአታችሁ ምንኛ ታላቅ እንደ ሆነ፣ በደላችሁም የቱን ያህል እንደ በዛ እኔ ዐውቃለሁና። ጻድቁን ትጨቍናላችሁ፤ ጕቦም ትቀበላላችሁ፤ በፍርድ አደባባይም ከድኻው ፍትሕ ትነጥቃላችሁ። ስለዚህ አስተዋይ ሰው በእንዲህ ያለ ጊዜ ዝም ይላል፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና። በሕይወት ትኖሩ ዘንድ፣ መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፤ ከዚያ በኋላ እንደ ተናገራችሁት፣ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ይሆናል። ክፉውን ጥሉ፤ መልካሙንም ውደዱ፤ በፍርድ አደባባይም ፍትሕን አታጓድሉ፤ ምናልባትም የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር፣ ለዮሴፍ ትሩፍ ይራራ ይሆናል። ስለዚህ ጌታ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በየመንገዱ ሁሉ ወየው ተብሎ ይለቀሳል፤ በአደባባዩም የሥቃይ ጩኸት ይሆናል፤ ገበሬዎች ለልቅሶ፣ አልቃሾችም ለዋይታ ይጠራሉ። በየወይኑ ዕርሻ ሁሉ ወየው ተብሎ ይለቀሳል፤ እኔ በመካከላችሁ ዐልፋለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር። የእግዚአብሔርን ቀን ለምትሹ፣ ለእናንተ ወዮላችሁ! የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትሻላችሁ? ያ ቀን ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም። ይህ ቀን አንድ ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ፣ ድብ እንደሚያጋጥመው፣ ወደ ቤቱም ገብቶ፣ እጁን በግድግዳው ላይ ሲያሳርፍ፣ እባብ እንደሚነድፈው ነው። የእግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ፣ የብርሃን ጸዳል የሌለው ድቅድቅ ጨለማ አይደለምን? “ዓመት በዓላችሁን ተጸይፌአለሁ፤ ጠልቼውማለሁ፤ ጉባኤዎቻችሁ ደስ አያሰኙኝም። የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን ብታቀርቡልኝም፣ እኔ አልቀበለውም፤ ከሠቡ እንስሶቻችሁ የኅብረት መሥዋዕት ብታቀርቡልኝም፣ እኔ አልመለከተውም። የዝማሬህን ጩኸት ከእኔ አርቅ፤ የበገናህንም ዜማ አልሰማም። ነገር ግን ፍትሕ እንደ ወንዝ፣ ጽድቅም እንደማይደርቅ ምንጭ ይፍሰስ። “የእስራኤል ቤት ሆይ፤ አርባ ዓመት በምድረ በዳ፣ መሥዋዕትንና ቍርባንን አቅርባችሁልኝ ነበርን? ይልቁንም ለራሳችሁ የሠራችኋቸውን፣ የንጉሣችሁን የሲኩትን ጣዖታት፣ የኮከብ አምላክ የሆነውን የሪፋን አማልክት አንሥታችሁ ተሸከማችሁ። ስለዚህ ከደማስቆ ማዶ እንድትጋዙ አደርጋለሁ፤” ይላል ስሙ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር የሆነ።

አሞጽ 5:1-27 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በእናንተ ላይ ለሙሾ የማነሣውን ይህን ቃል ስሙ። የእስራኤል ድንግል ወደቀች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሣም፥ በምድርዋ ላይ ተጣለች፥ የሚያስነሣትም የለም። ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላልና፦ ሺህ ከሚወጣበት ከተማ መቶ ይቀርላታል፥ መቶም ከሚወጣባት ከተማ ለእስራኤል ቤት አሥር ይቀርላታል። እግዚአብሔርም ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦ እኔን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ፥ ነገር ግን ጌልገላ ፈጽሞ ትማረካለችና፥ ቤቴልም ከንቱ ትሆናለችና ቤቴልን አትፈልጉ፥ ወደ ጌልገላም አትግቡ፥ ወደ ቤርሳቤህም አትለፉ። በዮሴፍ ቤት እሳት እንዳትቃጠል፥ በቤቴል የሚያጠፋትም ሳይኖር እንዳትበላ፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ። ፍርድን ወደ እሬት የምትለውጡ፥ ጽድቅንም በምድር ላይ የምትጥሉ እናንተ ሆይ፥ ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮበብ የፈጠረውን፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጠውን፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልመውን፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸውን፥ አምባውም እንዲፈርስ በብርቱ ላይ የድንገት ጥፋት የሚያመጣውን ፈልጉ፥ ስሙ እግዚአብሔር ነው። በበሩ አደባባይ የሚገሥጸውን ጠሉ፥ እውነትም የሚናገረውን ተጸየፉ። ድሀውንም ደብድባችኋልና፥ የስንዴውንም ቀረጥ ከእርሱ ወስዳችኋልና ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ሠርታችኋል፥ ነገር ግን አትቀመጡባቸውም፥ ያማሩ የወይን ቦታዎች ተክላችኋል፥ ነገር ግን ከወይን ጠጃቸው አትጠጡም። ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችጋረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ፥ በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና። ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና በዚያ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላል። በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፥ እንዲሁም እናንተ እንደ ተናገራችሁ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል። ክፉውን ጥሉ፥ መልካሙንም ውደዱ፥ በበሩም አደባባይ ፍርድን አጽኑ፥ ምናልባት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆናል። ስለዚህ ጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በየአደባባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆናል፥ በየመንገዱም ሁሉ ላይ ወዮ ወዮ ይባላል፥ ገበሬዎቹም ወደ ልቅሶ፥ አልቃሾቹም ወደ ዋይታ ይጠራሉ። በመካከልህ አልፋለሁና በወይኑ ቦታ ሁሉ ልቅሶ ይሆናል፥ ይላል እግዚአብሔር። የእግዚአብሔርን ቀን ለምትፈልጉ ወዮላችሁ! የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትፈልጋላችሁ? ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም። ከአንበሳ ፊት እንደ ሸሸ ድብም እንዳገኘው ሰው፥ ወይም ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ነው። የእግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ አይደለምን? ፀዳል የሌለውም ድቅድቅ ጨለማ አይደለምን? ዓመት በዓላችሁን ጠልቼዋለሁ ተጸይፌውማለሁ፥ የተቀደሰውም ጉባኤአችሁ ደስ አያሰኘኝም። የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቍርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፥ ለምስጋና መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም። የዝማሬህንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፥ የመሰንቆህንም ዜማ አላደምጥም። ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም እንደማይደርቅ ፈሳሽ ይፍሰስ። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በውኑ በምድረ በዳ አርባ ዓመት ሙሉ መሥዋዕትንና ቍርባንን አቅርባችሁልኛልን? ለራሳችሁም የሠራችኋቸውን ምስሎች፥ የሞሎክን ድንኳንና የአምላካችሁን የሬፋን ኮከብ አነሣችሁ። ስለዚህ ከደማስቆ ወደዚያ አስማርካችኋለሁ፥ ይላል ስሙ የሠራዊት አምላክ የተባለ እግዚአብሔር።

አሞጽ 5:1-27 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በእናንተ ላይ እኔ የማወርደውን ይህን ሙሾ አድምጡ፦ እነሆ ድንግሊቱ እስራኤል ወደቀች፤ እንደገናም መነሣት አትችልም የሚያነሣት ረዳት በማጣት በገዛ ምድርዋ የተተወች ብቸኛ ሆነች። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከአንዲት የእስራኤል ከተማ ሺህ ጦረኞች ይዘምታሉ፤ በሕይወት የሚቀሩት ግን አንድ መቶ ብቻ ይሆናሉ፤ ከሌላይቱም ከተማ መቶ ጦረኞች ይዘምታሉ፤ ተመልሰው የሚመጡት ግን ዐሥር ብቻ ይሆናሉ።” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደ እኔ ተመለሱ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ ወደ ቤርሳቤህ አትሂዱ፤ ቤቴል ፈራርሳ እንዳልነበረች ስለምትሆን በጌልገላ የሚኖሩ ሕዝቦችም ስደት ስለ ተፈረደባቸው ወደ ቤቴልም ሆነ ወደ ጌልጌላ አትሂዱ።” ይልቅስ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ አለበለዚያ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ እንደ እሳት ሆኖ ያጋያቸዋል፤ የቤትኤልንም ኗሪዎች እሳት ይበላቸዋል፤ እሳቱን የሚያጠፋላቸውም አይገኝም። እናንተ ፍርድን የምታጣምሙና እውነትን ወደ ሐሰት የምትለውጡ ወዮላችሁ! “ፕሊያዲስ” የተባሉትን ሰባቱን ከዋክብትና “ኦርዮን” ተብለው የሚጠሩትን የከዋክብት ክምችትን የፈጠረ፥ ሌሊቱን ወደ ቀን፥ ቀኑንም ወደ ሌሊት የሚለውጥ፥ የባሕሩን ውሃ አዞ፥ በምድር ላይ እንዲፈስ የሚያደርግ፥ ኀያላንንና ምሽጎቻቸውን የሚደመስስ እርሱ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው። እናንተ በፍርድ አደባባይ የሚገሥጻችሁን ጠላችሁ፤ እውነት የሚናገረውንም ተጸየፋችሁ። ድኾችን ጨቊናችሁ፤ እህላቸውንም አስገብራችሁ፤ ከጥርብ ድንጋይ ቤቶች ሠርታችኋል፤ እናንተ ግን አትኖሩባቸውም፤ የሚያስደስት ወይን ተክላችኋል፤ ነገር ግን ከእርሱ የሚገኘውን የወይን ጠጅ እናንተ አትጠጡም። በደላችሁ ምን ያኽል እንደ በዛና ኃጢአታችሁም ምን ያኽል ከባድ እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ ደጋግ ሰዎችን ታስጨንቃላችሁ፤ ጉቦ እየተቀበላችሁ በየፍርድ አደባባዩ የምስኪኖችን ፍትሕ ታጣምማላችሁ። ስለዚህ ዘመኑ ክፉ ስለ ሆነ አስተዋይ የሆነ ሰው ዝም ይላል። በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን እንጂ ክፉ ነገር አታድርጉ፤ ይህን ብታደርጉ ልክ እናንተ እንደምትሉት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል። ክፉውን ነገር ጥሉ፤ መልካም የሆነውን ነገር ውደዱ፤ በየፍርድ አደባባዩም ፍትሕ እንዳይጓደል አድርጉ፤ ምናልባት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ለተረፉት የእስራኤል ሕዝብ ምሕረት ያደርግላቸው ይሆናል። ስለዚህ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በየመንገዱና በየአደባባዩ ዋይታና ለቅሶ ይሰማል፤ ገበሬዎች እንኳ ለለቅሶ ይጠራሉ፤ ከሙሾ አውጪዎችም ጋር ስለ ሞቱ ሰዎች ያለቅሳሉ፤ በወይን ተክል ቦታዎች ሁሉ ለቅሶ ይሆናል፤ ይህም ሁሉ የሚሆነው እኔ በመካከላችሁ ስለማልፍ ነው፤” ይህንንም የተናገረ እግዚአብሔር ነው። እናንተ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት የምትጠባበቁ ወዮላችሁ! ያ ቀን የጨለማ እንጂ የብርሃን ቀን ስላይደለ ለምን ያንን ቀን ትጠባበቃላችሁ? ያ ቀን አንድ ሰው ከአንበሳ ሸሽቶ ሲሄድ ድብ እንደሚያጋጥመው፥ ወይም አምልጦ ወደ ቤቱ ሲገባ እጁን በግድግዳ ላይ ቢያሳርፍ እባብ እንደሚነድፈው ሁኔታ ይሆንባችኋል። በእግዚአብሔር የፍርድ ቀን ጨለማ እንጂ ብርሃን አይሆንላችሁም፤ ያ ቀን ምንም ብርሃን የማይታይበት ድቅድቅ ጨለማ ይሆንባችኋል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የዓመት በዓሎቻችሁን ሁሉ እጠላለሁ፤ እንቃለሁም፤ የአምልኮ ስብሰባዎቻችሁም አያስደስቱኝም። የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል መባ ብታቀርቡልኝ እንኳ አልቀበላችሁም፤ ለደኅንነት መሥዋዕት ወደምታቀርቡልኝ የሰቡ ፍሪዳዎችም አልመለከትም። የመዝሙራችሁን ጩኸት ከእኔ አርቁ፤ የበገናችሁንም ዜማ መስማት አልፈልግም፤ ይልቅስ ፍትሕ እንደ ወራጅ ውሃ፥ ጽድቅም እንደማያቋርጥ የወንዝ ውሃ ይፍሰስ። “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በውኑ በአርባው ዓመት የምድረ በዳው ጒዞ ጊዜ መሥዋዕትና መባ አቅርባችሁልኛልን? ለራሳችሁ የሠራችኋቸውን ‘ንጉሥ የምትሉትን’ ሳኩት የተባለውን ጣዖታችሁን፥ እንዲሁም ‘ኬዋን’ የተባለውን የኮከብ ጣዖታችሁን ትሸከማላችሁ። ከደማስቆ ወዲያ ርቃችሁ እንድትሰደዱ አደርጋለሁ።” ይህን የተናገርኩ እኔ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነኝ።

አሞጽ 5:1-27 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የእስራኤል ቤት ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ ለሙሾ የማነሣውን ይህን ቃል ስሙ። “የእስራኤል ድንግል ወደቀች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሣም፤ በምድርዋ ላይ ለብቻዋ ተተወች፥ የሚያነሳትም ማንም የለም።” ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላልና፦ “ሺህ ከሚወጣበት ከተማ መቶ ይቀርላታል፥ መቶም ከሚወጣባት ከተማ ለእስራኤል ቤት ዐሥር ይቀርላታል።” ጌታም ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦ “እኔን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ ነገር ግን ጌልገላ ፈጽሞ ትማረካለችና፥ ቤቴልም ከንቱ ትሆናለችና ቤቴልን አትፈልጉ፥ ወደ ጌልገላም አትግቡ፥ ወደ ቤርሳቤህም አትለፉ።” በዮሴፍ ቤት ላይ እንደ እሳት በድንገት እንዳይቀጣጠል፥ በቤቴልም ላይ የሚያጠፋው ሳይኖር እንዳይበላት፥ ጌታን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ። ፍርድን ወደ እሬት የምትለውጡ፥ ጽድቅንም በምድር ላይ የምትጥሉ እናንተ ሆይ! ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮበብ የፈጠረ፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጥ፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልም፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸው እርሱ፥ ስሙ ጌታ ነው። እርሱም ምሽጉ እንዲፈርስ በብርቱ ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣል። በበሩ አደባባይ የሚገሥጸውን ጠሉ፥ እውነትም የሚናገረውን ተጸየፉ። እናንተም ድሀውን ረግጣችኋልና፥ የስንዴውንም ቀረጥ ከእርሱ ወስዳችኋልና፥ ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ሠርታችኋል፥ ነገር ግን አትቀመጡባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታዎች ተክላችኋል፥ ነገር ግን ከወይን ጠጃቸው አትጠጡም። ጻድቁን የምታሠቃዩ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችግረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ! በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና። ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና፥ በእንደዚህ ያለ ዘመን አስተዋይ የሆነ ሰው ዝም ይላል። በሕይወት እንድትኖሩ መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፤ እንዲሁም እናንተ እንደ ተናገራችሁት የሠራዊት አምላክ ጌታ ከእናንተ ጋር ይሆናል። ክፉውን ጥሉ፥ መልካሙንም ውደዱ፥ በበሩም አደባባይ ፍርድን አጽኑ፤ ምናልባት የሠራዊት አምላክ ጌታ ለዮሴፍ ትሩፍ ይራራ ይሆናል። ስለዚህ ጌታ፥ የሠራዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በየአደባባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆናል፤ በየመንገዱም ሁሉ ላይ ‘ወዮ! ወዮ!’ ይላሉ፤ ገበሬዎቹም ወደ ልቅሶ፥ አልቃሾቹም ወደ ዋይታ ይጠራሉ። በመካከልህ አልፋለሁና በወይኑ ቦታ ሁሉ ልቅሶ ይሆናል፥” ይላል ጌታ። የጌታን ቀን ለምትፈልጉ ወዮላችሁ! የጌታን ቀን ለምን ትፈልጋላችሁ? ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም። ከአንበሳ ፊት ሲሸሽ ድብ እንዳገኘው ሰው፥ ወይም ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ነው። የጌታ ቀን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ አይደለምን? ፀዳል የሌለውም ድቅድቅ ጨለማ አይደለምን? “ዓመት በዓላችሁን ጠልቼዋለሁ፤ ተጸይፌዋለሁም፤ የተቀደሰውም ጉባኤአችሁ ደስ አያሰኘኝም። የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቁርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ ለአንድነት መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም። የዝማሬህንም ጩኸት ከእኔ አርቅ፤ የበገናህንም ዜማ አላዳምጥም። ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም እንደማይደርቅ ምንጭ ይፍሰስ።” “የእስራኤል ቤት ሆይ! በውኑ አርባ ዓመት በምድረ በዳ መሥዋዕትንና ቁርባንን አቅርባችሁልኛልን? ለራሳችሁም የሠራችኋቸውን ምስሎቻችሁን፥ የሳኩት የንጉሣችሁን እና የአምላካችሁን የኬዋን ኮከብ ታነሣላችሁ። ስለዚህ ከደማስቆ ባሻገር አስማርኬ አፈልሳችኋለሁ፥” ይላል ጌታ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ የሆነ።