ሐዋርያት ሥራ 16:38-40
ሐዋርያት ሥራ 16:38-40 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
መኰንኖቹም ይህንኑ ቃል ለገዦቹ ነገሯቸው፤ እነርሱም ጳውሎስና ሲላስ የሮም ዜጎች መሆናቸውን ሲሰሙ ደነገጡ፤ እነርሱ ራሳቸውም መጥተው ይቅርታ ጠይቀው ከወህኒ ቤቱ አወጧቸው፤ ከተማውንም ለቅቀው እንዲሄዱ ለመኗቸው። ጳውሎስና ሲላስ ከእስር ቤቱ ከወጡ በኋላ ወደ ልድያ ቤት ሄዱ፤ በዚያም ወንድሞችን አግኝተው አበረታቷችው፤ ከዚያም በኋላ ሄዱ።
ሐዋርያት ሥራ 16:38-40 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ፖሊሶቹ ይህን ነገር ለባለሥልጣኖቹ ነገሩ፤ ባለሥልጣኖቹም ጳውሎስና ሲላስ የሮም ዜጋዎች መሆናቸውን ባወቁ ጊዜ ፈሩ። ስለዚህ መጥተው ይቅርታ ጠየቁአቸውና ከወህኒ ቤት አስወጡአቸው፤ ከከተማውም እንዲሄዱ ለመኑአቸው። ጳውሎስና ሲላስም ከወህኒ ቤት ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ፤ እዚያም ወንድሞችን አግኝተው፥ አጽናኑአቸውና ከተማውን ለቀው ሄዱ።
ሐዋርያት ሥራ 16:38-40 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ብላቴኖቻቸውም ሄደው ይህንን ነገር ለገዢዎቹ ነገሩአቸው፤ የሮም ሰዎች መሆናቸውንም ሰምተው ደነገጡ። መጥተውም ከከተማቸው እንዲወጡ ማለዱአቸው። ከወኅኒ ቤቱም ከወጡ በኋላ ወደ ልድያ ቤት ገብተው ወንድሞችን አገኙ፤ አጽናንተዋቸውም ሔዱ።
ሐዋርያት ሥራ 16:38-40 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
መኰንኖቹም ይህንኑ ቃል ለገዦቹ ነገሯቸው፤ እነርሱም ጳውሎስና ሲላስ የሮም ዜጎች መሆናቸውን ሲሰሙ ደነገጡ፤ እነርሱ ራሳቸውም መጥተው ይቅርታ ጠይቀው ከወህኒ ቤቱ አወጧቸው፤ ከተማውንም ለቅቀው እንዲሄዱ ለመኗቸው። ጳውሎስና ሲላስ ከእስር ቤቱ ከወጡ በኋላ ወደ ልድያ ቤት ሄዱ፤ በዚያም ወንድሞችን አግኝተው አበረታቷችው፤ ከዚያም በኋላ ሄዱ።
ሐዋርያት ሥራ 16:38-40 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሎሌዎቹም ይህን ነገር ለገዢዎች ነገሩ። የሮሜ ሰዎችም እንደ ሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ፤ መጥተውም ማለዱአቸው። ከወኅኒውም ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ፥ ወንድሞችንም ባዩ ጊዜ አጽናኑአቸውና ሄዱ።