የሐዋርያት ሥራ 16:38-40

የሐዋርያት ሥራ 16:38-40 መቅካእኤ

ሎሌዎቹም ይህን ነገር ለገዢዎች ነገሩ፤ የሮሜ ሰዎችም እንደ ሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ። መጥተውም ማለዱአቸው፤ አውጥተውም ከከተማ ይወጡ ዘንድ ለመኑአቸው። ከወኅኒውም ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ፤ ወንድሞችንም ባዩ ጊዜ አጽናኑአቸውና ሄዱ።