የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሐዋርያት ሥራ 16:25-40

ሐዋርያት ሥራ 16:25-40 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ። የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ “ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ። መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤ ወደ ውጭም አውጥቶ፦ “ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?” ኣላቸው። እነርሱም፦ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ” አሉት። ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው። በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ፤ ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ። በነጋም ጊዜ ገዢዎቹ፦ “እነዚያን ሰዎች ፍታቸው” ብለው ሎሌዎቻቸውን ላኩ። የወኅኒውም ጠባቂ፦ “ትፈቱ ዘንድ ገዢዎቹ ልከዋል፤ እንግዲህ አሁን ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ” ብሎ ይህን ቃል ለጳውሎስ ነገረው። ጳውሎስ ግን፦ “እኛ የሮሜ ሰዎች ስንሆን ያለ ፍርድ በሕዝብ ፊት ደብድበው በወኅኒ ጣሉን፤ አሁንም በስውር ይጥሉናልን? አይሆንም ራሳቸው ግን መጥተው ያውጡን” አላቸው። ሎሌዎቹም ይህን ነገር ለገዢዎች ነገሩ። የሮሜ ሰዎችም እንደ ሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ፤ መጥተውም ማለዱአቸው። ከወኅኒውም ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ፥ ወንድሞችንም ባዩ ጊዜ አጽናኑአቸውና ሄዱ።

ሐዋርያት ሥራ 16:25-40 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እኩለ ሌሊት አካባቢ ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩና እየዘመሩ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ነበር፤ ሌሎቹ እስረኞችም ያዳምጧቸው ነበር። ድንገትም የወህኒ ቤቱን መሠረት የሚያናውጥ ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ፤ ወዲያውም የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፈቱ፤ የሁሉም እስራት ተፈታ። የወህኒ ቤቱ ጠባቂም ከእንቅልፉ ነቅቶ የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፍተው ባየ ጊዜ፣ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ለመግደል ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “እኛ ሁላችን እዚሁ ስላለን፣ በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርስ!” ብሎ ጮኸ። የወህኒ ቤቱ ጠባቂም መብራት ለምኖ ወደ ውስጥ ዘልሎ ገባ፤ እየተንቀጠቀጠም በጳውሎስና በሲላስ እግር ላይ ወደቀ። ይዟቸው ከወጣ በኋላ፣ “ጌቶች ሆይ፤ እድን ዘንድ ምን ላድርግ?” አላቸው። እነርሱም፣ “በጌታ በኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ” አሉት። ከዚያም ለርሱና በቤቱ ላሉት ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ተናገሩ። የወህኒ ቤት ጠባቂውም ሌሊት በዚያ ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን ዐጠበላቸው፤ ወዲያውም እርሱና ቤተ ሰቡ ሁሉ ተጠመቁ። የወህኒ ቤቱ ጠባቂም ወደ ቤቱ ወስዶ ማእድ አቀረበላቸው፤ ከቤተ ሰቡም ሁሉ ጋራ በእግዚአብሔር በማመኑ በደስታ ተሞላ። ሲነጋም፣ ገዦቹ፣ “እነዚያን ሰዎች ፈተህ ልቀቃቸው” ብለው መኰንኖቻቸውን ላኩበት። የወህኒ ቤት ጠባቂውም፣ “ገዦቹ እንድትፈቱ አዝዘዋል፤ ስለዚህ ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ” ብሎ ለጳውሎስ ነገረው። ጳውሎስ ግን፣ “እኛ የሮም ዜጎች ሆነን ሳለን፣ በሕዝብ ፊት ያለ ፍርድ ደብድበው ወደ እስር ቤት ወረወሩን፤ ታዲያ አሁን በስውር ሊያስወጡን ይፈልጋሉ? ይህማ አይሆንም፤ እነርሱ ራሳቸው መጥተው ያስወጡን!” አላቸው። መኰንኖቹም ይህንኑ ቃል ለገዦቹ ነገሯቸው፤ እነርሱም ጳውሎስና ሲላስ የሮም ዜጎች መሆናቸውን ሲሰሙ ደነገጡ፤ እነርሱ ራሳቸውም መጥተው ይቅርታ ጠይቀው ከወህኒ ቤቱ አወጧቸው፤ ከተማውንም ለቅቀው እንዲሄዱ ለመኗቸው። ጳውሎስና ሲላስ ከእስር ቤቱ ከወጡ በኋላ ወደ ልድያ ቤት ሄዱ፤ በዚያም ወንድሞችን አግኝተው አበረታቷችው፤ ከዚያም በኋላ ሄዱ።

ሐዋርያት ሥራ 16:25-40 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በመ​ን​ፈቀ ሌሊ​ትም ጳው​ሎ​ስና ሲላስ ጸለዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በዜማ አመ​ሰ​ገ​ኑት፤ እስ​ረ​ኞ​ቹም ይሰ​ሙ​አ​ቸው ነበር። ድን​ገ​ትም ታላቅ ንው​ጽ​ው​ጽታ ሆነ፤ የወ​ህኒ ቤቱ መሠ​ረ​ትም ተና​ወጠ፤ በሮ​ችም ሁሉ ያን​ጊዜ ተከ​ፈቱ፤ የሁ​ሉም እግር ብረ​ቶ​ቻ​ቸው እየ​ወ​ለቁ ወደቁ። የወ​ህኒ ቤቱ ጠባ​ቂም ከእ​ን​ቅ​ልፉ በነቃ ጊዜ በሮች ሁሉ ተከ​ፍ​ተው አየ፤ ሰይ​ፉ​ንም መዝዞ ራሱን ሊገ​ድል ወደደ፤ እስ​ረ​ኞቹ ያመ​ለ​ጡት መስ​ሎት ነበ​ርና። ጳው​ሎ​ስም፥ “በራ​ስህ ክፉ ነገር አታ​ድ​ርግ፤ ሁላ​ች​ንም ከዚህ አለን” ብሎ በታ​ላቅ ቃል ጮኸ። መብ​ራት አም​ጥ​ቶም እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ ወደ ውስጥ ሄደና ለጳ​ው​ሎ​ስና ለሲ​ላስ ወድቆ ሰገደ። ወደ ውጭም አው​ጥቶ “ጌቶች፥ እድን ዘንድ ምን ላድ​ርግ?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እመን፤ አን​ተና ቤተ ሰብ​ህም ሁሉ ትድ​ና​ላ​ችሁ” አሉት። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ለእ​ር​ሱና በቤቱ ላሉት ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው። ወዲ​ያ​ው​ኑም በሌ​ሊት ወስዶ ቍስ​ላ​ቸ​ውን አጠ​በ​ላ​ቸው፤ እር​ሱም በዚ​ያው ጊዜ ከቤተ ሰቡ ሁሉ ጋር ተጠ​መቀ። ወደ ቤቱም አግ​ብቶ ማዕድ አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ በጌ​ታ​ችን ስለ አመ​ነም እርሱ ከቤተ ሰቡ ጋር ደስ አለው። በነጋ ጊዜም፥ ገዢ​ዎቹ፥ “እነ​ዚ​ያን ሰዎች ፈት​ታ​ችሁ ልቀ​ቋ​ቸው” ብለው ብላ​ቴ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ላኩ። የወ​ህኒ ቤቱ ጠባ​ቂም በሰማ ጊዜ ሄዶ ገዢ​ዎቹ “ይፈቱ” ብለው እንደ ላኩ ይህን ነገር ለጳ​ው​ሎ​ስና ለሲ​ላስ ነገ​ራ​ቸው፤ “አሁ​ንም ውጡና በሰ​ላም ሂዱ” አላ​ቸው። ጳው​ሎስ ግን፥ “እኛ የሮም ሰዎች ስን​ሆን፥ ያለ ፍርድ በአ​ደ​ባ​ባይ ገረ​ፉን፤ አሰ​ሩ​ንም፤ አሁ​ንም በስ​ውር ሊያ​ወ​ጡን ይሻሉ፤ አይ​ሆ​ንም፥ ራሳ​ቸው መጥ​ተው ያው​ጡን” አላ​ቸው። ብላ​ቴ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ሄደው ይህ​ንን ነገር ለገ​ዢ​ዎቹ ነገ​ሩ​አ​ቸው፤ የሮም ሰዎች መሆ​ና​ቸ​ው​ንም ሰም​ተው ደነ​ገጡ። መጥ​ተ​ውም ከከ​ተ​ማ​ቸው እን​ዲ​ወጡ ማለ​ዱ​አ​ቸው። ከወ​ኅኒ ቤቱም ከወጡ በኋላ ወደ ልድያ ቤት ገብ​ተው ወን​ድ​ሞ​ችን አገኙ፤ አጽ​ና​ን​ተ​ዋ​ቸ​ውም ሔዱ።

ሐዋርያት ሥራ 16:25-40 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እኩለ ሌሊት አካባቢ ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩና እየዘመሩ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ነበር፤ ሌሎቹ እስረኞችም ያዳምጧቸው ነበር። ድንገትም የወህኒ ቤቱን መሠረት የሚያናውጥ ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ፤ ወዲያውም የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፈቱ፤ የሁሉም እስራት ተፈታ። የወህኒ ቤቱ ጠባቂም ከእንቅልፉ ነቅቶ የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፍተው ባየ ጊዜ፣ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ለመግደል ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “እኛ ሁላችን እዚሁ ስላለን፣ በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርስ!” ብሎ ጮኸ። የወህኒ ቤቱ ጠባቂም መብራት ለምኖ ወደ ውስጥ ዘልሎ ገባ፤ እየተንቀጠቀጠም በጳውሎስና በሲላስ እግር ላይ ወደቀ። ይዟቸው ከወጣ በኋላ፣ “ጌቶች ሆይ፤ እድን ዘንድ ምን ላድርግ?” አላቸው። እነርሱም፣ “በጌታ በኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ” አሉት። ከዚያም ለርሱና በቤቱ ላሉት ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ተናገሩ። የወህኒ ቤት ጠባቂውም ሌሊት በዚያ ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን ዐጠበላቸው፤ ወዲያውም እርሱና ቤተ ሰቡ ሁሉ ተጠመቁ። የወህኒ ቤቱ ጠባቂም ወደ ቤቱ ወስዶ ማእድ አቀረበላቸው፤ ከቤተ ሰቡም ሁሉ ጋራ በእግዚአብሔር በማመኑ በደስታ ተሞላ። ሲነጋም፣ ገዦቹ፣ “እነዚያን ሰዎች ፈተህ ልቀቃቸው” ብለው መኰንኖቻቸውን ላኩበት። የወህኒ ቤት ጠባቂውም፣ “ገዦቹ እንድትፈቱ አዝዘዋል፤ ስለዚህ ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ” ብሎ ለጳውሎስ ነገረው። ጳውሎስ ግን፣ “እኛ የሮም ዜጎች ሆነን ሳለን፣ በሕዝብ ፊት ያለ ፍርድ ደብድበው ወደ እስር ቤት ወረወሩን፤ ታዲያ አሁን በስውር ሊያስወጡን ይፈልጋሉ? ይህማ አይሆንም፤ እነርሱ ራሳቸው መጥተው ያስወጡን!” አላቸው። መኰንኖቹም ይህንኑ ቃል ለገዦቹ ነገሯቸው፤ እነርሱም ጳውሎስና ሲላስ የሮም ዜጎች መሆናቸውን ሲሰሙ ደነገጡ፤ እነርሱ ራሳቸውም መጥተው ይቅርታ ጠይቀው ከወህኒ ቤቱ አወጧቸው፤ ከተማውንም ለቅቀው እንዲሄዱ ለመኗቸው። ጳውሎስና ሲላስ ከእስር ቤቱ ከወጡ በኋላ ወደ ልድያ ቤት ሄዱ፤ በዚያም ወንድሞችን አግኝተው አበረታቷችው፤ ከዚያም በኋላ ሄዱ።

ሐዋርያት ሥራ 16:25-40 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ። የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ “ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ። መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤ ወደ ውጭም አውጥቶ፦ “ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?” ኣላቸው። እነርሱም፦ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ” አሉት። ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው። በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ፤ ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ። በነጋም ጊዜ ገዢዎቹ፦ “እነዚያን ሰዎች ፍታቸው” ብለው ሎሌዎቻቸውን ላኩ። የወኅኒውም ጠባቂ፦ “ትፈቱ ዘንድ ገዢዎቹ ልከዋል፤ እንግዲህ አሁን ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ” ብሎ ይህን ቃል ለጳውሎስ ነገረው። ጳውሎስ ግን፦ “እኛ የሮሜ ሰዎች ስንሆን ያለ ፍርድ በሕዝብ ፊት ደብድበው በወኅኒ ጣሉን፤ አሁንም በስውር ይጥሉናልን? አይሆንም ራሳቸው ግን መጥተው ያውጡን” አላቸው። ሎሌዎቹም ይህን ነገር ለገዢዎች ነገሩ። የሮሜ ሰዎችም እንደ ሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ፤ መጥተውም ማለዱአቸው። ከወኅኒውም ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ፥ ወንድሞችንም ባዩ ጊዜ አጽናኑአቸውና ሄዱ።

ሐዋርያት ሥራ 16:25-40 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ወደ እኩለ ሌሊት ገደማ ጳውሎስና ሲላስ በጸሎትና በመዝሙር እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ሌሎችም እስረኞች ያዳምጡአቸው ነበር። በድንገት የወህኒ ቤቱ መሠረት እስኪናጋ ድረስ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ በሮቹም ሁሉ በአንድ ጊዜ ተከፈቱ፤ የእያንዳንዱም እስረኛ ሰንሰለት ተፈታ። ጠባቂው ከእንቅልፉ ነቅቶ የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፍተው ባየ ጊዜ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ሊገድል ሰይፉን መዘዘ። ነገር ግን ጳውሎስ፥ “ሁላችንም እዚህ ነን! ስለዚህ በራስህ ላይ ጒዳት አታድርስ!” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በዚህ ጊዜ ጠባቂው መብራት አስመጥቶ እየሮጠ ወደ ውስጥ ገባ፤ እየተንቀጠቀጠም በጳውሎስና በሲላስ እግር ሥር በግንባሩ ተደፋ። ወደ ውጪም አወጣቸውና “ጌቶቼ ሆይ! ለመዳን ምን ማድረግ ይገባኛል?” አላቸው። እነርሱም “በጌታ በኢየሱስ እመን፤ ትድናለህ፤ ቤተሰቦችህም ይድናሉ” አሉት። የጌታንም ቃል ለእርሱና በእርሱ ቤት ላሉትም ሁሉ ተናገሩ። በዚያኑ ሰዓት በሌሊት የወህኒ ቤቱ ጠባቂ ወሰዳቸውና ቊስላቸውን አጠበላቸው፤ ወዲያውኑ እርሱና ቤተሰቡ በሙሉ ተጠመቁ። ከዚህ በኋላ ጳውሎስንና ሲላስን ወደ ቤቱ ወስዶ ምግብ አቀረበላቸው፤ በእግዚአብሔር ስላመነም ከቤተ ሰቡ ሁሉ ጋር ደስ አለው። በነጋም ጊዜ ባለሥልጣኖቹ “እነዚያ ሰዎች ይለቀቁ” ብለው ፖሊሶችን ላኩ። የወህኒ ቤት ጠባቂውም “እናንተ እንድትለቀቁ ባለሥልጣኖቹ ሰው ልከዋልና እንግዲህ ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ” ሲል ለጳውሎስ ነገረው። ጳውሎስ ግን “እኛ የሮም ዜጋዎች ስንሆን ያለ ፍርድ በአደባባይ ገርፈው ወደ ወህኒ አስገብተውናል። አሁን ደግሞ ከወህኒ ቤት በስውር እንድንወጣ ያደርጋሉን? አይሆንም! እነርሱ ራሳቸው መጥተው ያስወጡን!” ሲል መለሰ። ፖሊሶቹ ይህን ነገር ለባለሥልጣኖቹ ነገሩ፤ ባለሥልጣኖቹም ጳውሎስና ሲላስ የሮም ዜጋዎች መሆናቸውን ባወቁ ጊዜ ፈሩ። ስለዚህ መጥተው ይቅርታ ጠየቁአቸውና ከወህኒ ቤት አስወጡአቸው፤ ከከተማውም እንዲሄዱ ለመኑአቸው። ጳውሎስና ሲላስም ከወህኒ ቤት ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ፤ እዚያም ወንድሞችን አግኝተው፥ አጽናኑአቸውና ከተማውን ለቀው ሄዱ።

ሐዋርያት ሥራ 16:25-40 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፤ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ፤ የሁሉም እስራት ተፈታ። የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ “ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ፤” ብሎ ጮኸ። መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፤ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤ ወደ ውጭም አውጥቶ “ጌቶች ሆይ! እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?” ኣላቸው። እነርሱም “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፤ አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ፤” አሉት። ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው። በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቁስላቸውን አጠበላቸው፤ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ፤ ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው፤ በእግዚአብሔርም ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ። በነጋም ጊዜ ገዢዎቹ “እነዚያን ሰዎች ፍታቸው፤” ብለው ሎሌዎቻቸውን ላኩ። የወኅኒውም ጠባቂ “ትፈቱ ዘንድ ገዢዎቹ ልከዋል፤ እንግዲህ አሁን ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ፤” ብሎ ይህን ቃል ለጳውሎስ ነገረው። ጳውሎስ ግን “እኛ የሮሜ ሰዎች ስንሆን ያለ ፍርድ በሕዝብ ፊት ደብድበው በወኅኒ ጣሉን፤ አሁንም በስውር ይጥሉናልን? አይሆንም፤ ራሳቸው ግን መጥተው ያውጡን፤” አላቸው። ሎሌዎቹም ይህን ነገር ለገዢዎች ነገሩ፤ የሮሜ ሰዎችም እንደ ሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ። መጥተውም ማለዱአቸው፤ አውጥተውም ከከተማ ይወጡ ዘንድ ለመኑአቸው። ከወኅኒውም ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ፤ ወንድሞችንም ባዩ ጊዜ አጽናኑአቸውና ሄዱ።