ሐዋርያት ሥራ 15:16-18
ሐዋርያት ሥራ 15:16-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከዚህም በኋላ የወደቀችውን የዳዊትን ቤት መልሼ እሠራታለሁ፤ ፍራሽዋንም አድሳለሁ፤ የቀሩት ሰዎችና ስሜም የተጠራባቸው አሕዛብ ሁሉ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ፥ ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር፤ ከጥንት ጀምሮ ሥራው ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ነው።
Share
ሐዋርያት ሥራ 15 ያንብቡሐዋርያት ሥራ 15:16-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ ‘ከዚህ በኋላ እመለሳለሁ፤ የፈረሰውን የዳዊትን ቤት እገነባለሁ። ፍርስራሹን መልሼ አቆማለሁ፤ እንደ ገናም እሠራዋለሁ፤ ይኸውም የቀሩት ሰዎች ጌታን እንዲፈልጉ፣ ስሜን የተሸከሙ አሕዛብም እንዲሹኝ ነው፤ እነዚህን ያደረገ ጌታ እንዲህ ይላል፤’ እነርሱም ከጥንት ጀምሮ የታወቁ ናቸው።
Share
ሐዋርያት ሥራ 15 ያንብቡሐዋርያት ሥራ 15:16-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
‘ከዚህ በኋላ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን ይፈልጉ ዘንድ እመለሳለሁ፥ የወደቀችውንም የዳዊትን ድንኳን እንደ ገና እሠራታለሁ፥ ፍራሽዋንም እንደ ገና እሠራታለሁ እንደ ገናም አቆማታለሁ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ። ከጥንት ጀምሮ ሥራው ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ነው።’
Share
ሐዋርያት ሥራ 15 ያንብቡ