2 ጢሞቴዎስ 2:3-10

2 ጢሞቴዎስ 2:3-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

አንተም የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ወታደር በመሆን ከእኔ ጋር መከራን ተቀበል። በወታደርነት የሚያገለግል ሰው የጦር አዛዡን ለማስደሰት ዝግጁ መሆን አለበት እንጂ ወታደራዊ ባልሆነ ጉዳይ ላይ አይውልም። እንዲሁም በሩጫ የሚወዳደር ሰው በደንቡ መሠረት ካልተወዳደረ የአሸናፊነት የድል አክሊልን ሽልማት አያገኝም። በሥራ የሚደክም ገበሬ ከሥራው ከሚገኘው ፍሬ የመጀመሪያውን ማግኘት ይገባዋል። ጌታ በሁሉ ነገር ማስተዋልን ስለሚሰጥህ እኔ የምለውን ልብ ብለህ አስብ። ከሞት የተነሣውንና የዳዊት ዘር የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስታውስ፤ እኔም የማበሥረው ወንጌል ይኸው ነው። በዚህም ወንጌል ምክንያት እንደ ወንጀለኛ በሰንሰለት ታስሬ መከራ እቀበላለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም። ስለዚህ እነርሱም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚገኘውን መዳንና ዘለዓለማዊ ክብርን እንዲያገኙ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሰዎች ስል ሁሉን ነገር እታገሣለሁ።