2 ሳሙኤል 3:22-39

2 ሳሙኤል 3:22-39 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በዚያ ጊዜም የዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖ​ችና ኢዮ​አብ ከዘ​መቻ ታላቅ ምርኮ ይዘው መጡ። አበ​ኔር ግን ዳዊት አሰ​ና​ብ​ቶት በደ​ኅና ሄዶ ነበር እንጂ በኬ​ብ​ሮን አል​ነ​በ​ረም። ኢዮ​አ​ብና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በረ ጭፍራ ሁሉ በመጡ ጊዜ፥ “የኔር ልጅ አበ​ኔር ወደ ንጉሥ መጣ፤ አሰ​ና​በ​ተ​ውም፤ በሰ​ላ​ምም ሄደ” ብለው ሰዎች ለኢ​ዮ​አብ ነገ​ሩት። ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሥ ገብቶ፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ነገር ምን​ድን ነው? እነሆ፥ አበ​ኔር መጥ​ቶ​ልህ ነበር፤ በደ​ኅና እን​ዲ​ሄድ ስለ​ምን አሰ​ና​በ​ት​ኸው? የኔር ልጅ አበ​ኔር ያታ​ል​ልህ ዘንድ፥ መው​ጫ​ህ​ንና መግ​ቢ​ያ​ህ​ንም ያውቅ ዘንድ ፥ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ነገር ሁሉ ያስ​ተ​ውል ዘንድ እንደ መጣ አታ​ው​ቅ​ምን?” አለው። ኢዮ​አ​ብም ከዳ​ዊት በወጣ ጊዜ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ከአ​በ​ኔር በኋላ ላከ፤ ከሴ​ይ​ርም ጕድ​ጓድ መለ​ሱት። ዳዊት ግን ይህን አላ​ወ​ቀም። አበ​ኔ​ርም ወደ ኬብ​ሮን በተ​መ​ለሰ ጊዜ ኢዮ​አብ በበር ውስጥ በቈ​ይታ ይና​ገ​ረው ዘንድ ወደ አጠ​ገቡ ወሰ​ደው፤ በዚ​ያም ለወ​ን​ድሙ ለአ​ሣ​ሄል ደም ተበ​ቅሎ ወገ​ቡን መታው፤ ሞተም። ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ሰማ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ከኔር ልጅ ከአ​በ​ኔር ደም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እኔ ንጹሕ ነኝ፤ መን​ግ​ሥ​ቴም ንጹሕ ነው፤ በኢ​ዮ​አብ ራስ ላይና በአ​ባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይም​ጣ​በት፤ በኢ​ዮ​አ​ብም ቤት ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ወይም ለም​ጻም ወይም አን​ካሳ ወይም በሰ​ይፍ የሚ​ወ​ድቅ ወይም እን​ጀራ የሌ​ለው ሰው አይ​ታጣ።” ኢዮ​አ​ብና ወን​ድሙ አቢ​ሳም በሰ​ልፍ በገ​ባ​ዖን ወን​ድ​ማ​ቸ​ውን አሣ​ሄ​ልን ገድሎ ነበ​ርና አበ​ኔ​ርን ይገ​ድ​ሉት ዘንድ ይጠ​ባ​በቁ ነበር። ዳዊ​ትም ኢዮ​አ​ብ​ንና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብ​ሳ​ች​ሁን ቅደዱ፤ ማቅም ልበሱ፤ በአ​በ​ኔ​ርም ፊት አል​ቅሱ” አላ​ቸው። ንጉ​ሡም ዳዊት ከቃ​ሬ​ዛው በኋላ ሄደ። አበ​ኔ​ር​ንም በኬ​ብ​ሮን ቀበ​ሩት፤ ንጉ​ሡም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ በመ​ቃ​ብሩ አጠ​ገብ አለ​ቀሰ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ለአ​በ​ኔር አለ​ቀ​ሱ​ለት። ንጉ​ሡም ለአ​በ​ኔር አለ​ቀ​ሰ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “አበ​ኔር ሰነፍ እን​ደ​ሚ​ሞት ይሞ​ታ​ልን? እጆ​ችህ አል​ታ​ሰ​ሩም፤ እግ​ሮ​ች​ህም በሰ​ን​ሰ​ለት አል​ተ​ያ​ዙም፤ ማንም እንደ ሰነፍ አል​ወ​ሰ​ደ​ህም፤ በዐ​መፃ ልጆ​ችም ፊት ወደ​ቅህ።” ሕዝ​ቡም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው አለ​ቀ​ሱ​ለት። ሕዝ​ቡም ሁሉ ገና ሳይ​መሽ ዳዊ​ትን እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ሊጋ​ብ​ዙት መጡ፤ ዳዊት ግን፥ “ፀሐይ ሳት​ጠ​ልቅ እን​ጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀ​ምስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ያድ​ር​ግ​ብኝ፥ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​ብኝ” ብሎ ማለ። ሕዝ​ቡም ሁሉ ይህን ዐወቁ፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት ንጉሥ ያደ​ረ​ገው ሁሉ ደስ አሰ​ኛ​ቸው። በዚ​ያም ቀን ሕዝቡ ሁሉ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ የኔር ልጅ አበ​ኔ​ርን እን​ዲ​ገ​ድ​ሉት ንጉሡ እን​ዳ​ላ​ዘዘ ዐወቁ። ንጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ዛሬ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ታላቅ መኰ​ንን እንደ ወደቀ አታ​ው​ቁ​ምን? እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እር​ሱም በን​ጉሡ ዘንድ የተ​ሾመ እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? እነ​ዚ​ህም ሰዎች የሦ​ር​ህያ ልጆች በር​ት​ተ​ው​ብ​ኛል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመ​ል​ስ​በት” አላ​ቸው።

2 ሳሙኤል 3:22-39 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የዳዊትና የኢዮአብ ሰዎች በዚያ ጊዜ ብዙ ምርኮ ይዘው ከዘመቻ ተመለሱ። አበኔር ግን ዳዊት በሰላም አሰናብቶት ስለ ሄደ፣ በኬብሮን አልነበረም። ኢዮአብና ዐብሮት የነበረው ሰራዊት ሁሉ እዚያ እንደ ደረሱ፣ የኔር ልጅ አበኔር ወደ ንጉሡ መምጣቱን፣ ንጉሡ እንዳሰናበተውና እርሱም በሰላም እንደ ሄደ፣ ኢዮአብ ሰማ። ስለዚህ ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ገብቶ እንዲህ አለ፤ “ምን ማድረግህ ነው? እነሆ አበኔር መጥቶልህ እንዴት በሰላም እንዲሄድ አሰናበትኸው? የኔርን ልጅ አበኔርን ታውቀዋለህ፤ የመጣው ሊያታልልህ፣ መውጣት መግባትህን ለማወቅና የምታደርገውን ሁሉ ሊሰልል ነው።” ከዚያም ኢዮአብ ከዳዊት ዘንድ ወጣ፤ አበኔርን እንዲያመጡትም መልክተኞች ላከ፤ መልክተኞቹም ከሴይር የውሃ ጕድጓድ አጠገብ መለሱት። ዳዊት ግን ይህን አላወቀም ነበር። አበኔር ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፣ ኢዮአብ በቈይታ የሚያነጋግረው በመምሰል ዞር አድርጎ ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሲል፣ ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው። ዳዊት ይህን ነገር ቈይቶ በሰማ ጊዜ እንዲህ አለ፤ “እኔም ሆንሁ መንግሥቴ ከኔር ልጅ ከአበኔር ደም በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም ንጹሕ ነን፤ ደሙ በኢዮአብ ራስና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይሁን፤ ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ወይም አሠቃቂ የቈዳ በሽታ ያለበት፣ በምርኵዝ የሚሄድ ዐንካሳ፣ ወይም በሰይፍ ተመትቶ የሚወድቅ ወይም የሚበላው ያጣ ራብተኛ ከኢዮአብ ቤት አይታጣ።” አበኔር ገባዖን ላይ በተደረገው ጦርነት የኢዮአብንና የአቢሳን ወንድም አሣሄልን ገድሎት ስለ ነበር፣ እነርሱም አበኔርን ገደሉት። ከዚያም ዳዊት ለኢዮአብና ዐብሮት ለነበረው ሕዝብ ሁሉ፣ “ልብሳችሁን ቀድዳችሁ፣ ማቅ ለብሳችሁ በአበኔር ፊት አልቅሱ” አላቸው፤ ራሱ ንጉሥ ዳዊትም አስከሬኑን አጀበ። ከዚያም አበኔርን በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም በአበኔር መቃብር ላይ ጮኾ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እንደዚሁ አለቀሱ። ንጉሡም ለአበኔር ይህን የሐዘን እንጕርጕሮ ተቀኘ፤ “አበኔር እንደ ሞኝ ሰው ይሙት? እጆችህ አልታሰሩም፤ እግሮችህ በእግር ብረት አልገቡም፤ ሰው በክፉ ሰዎች ፊት እንደሚወድቅ አንተም እንደዚሁ ወደቅህ።” ሕዝቡም ሁሉ እንደ ገና አለቀሱለት። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እህል በሚቀምስበት ሰዓት ወደ ዳዊት መጥተው ምግብ እንዲበላ አጥብቀው ለመኑት። ዳዊት ግን፣ “ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ፣ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ከዚህም የባሰ ያምጣብኝ” ብሎ ማለ። ሕዝቡም ሁሉ ይህንኑ ተመለከቱ፤ ደስም አላቸው፤ በርግጥ ንጉሡ ያደረገው ሁሉ ሕዝቡን ደስ አሠኛቸው። እንዲሁም በዚያ ዕለት ሕዝቡ ሁሉና እስራኤል በሙሉ ንጉሡ በኔር ልጅ በአበኔር ሞት እጁ እንዳልገባበት ዐወቁ። ከዚያም ንጉሡ ለራሱ ሰዎች እንዲህ አለ፤ “በዛሬዪቱ ዕለት በእስራኤል መስፍንና ታላቅ ሰው መውደቁን አላወቃችሁምን? ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፣ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። እግዚአብሔር ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።”

2 ሳሙኤል 3:22-39 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በዚያን ጊዜም የዳዊት ባሪያዎችና ኢዮአብ ከዘምቻ ታላቅ ምርኮ ይዘው መጡ። አበኔር ግን ዳዊት አሰናብቶት በደኅና ሄዶ ነበር እንጂ በኬብሮን አልነበረም። ኢዮአብና ከእርሱም ጋር የነበረ ጭፍራ ሁሉ በመጡ ጊዜ፦ የኔር ልጅ አበኔር ወደ ንጉሥ መጣ፥ አሰናበተውም በደኅናውም ሄደ ብለው ሰዎች ለኢዮአብ ነገሩት። ኢዮአብም ወደ ንጉሥ ገብቶ፦ ምን አደረግህ? እነሆ፥ አበኔር መጥቶልህ ነበር፥ በደኅና እንዲሄድ ስለ ምን አሰናበትኸው? የኔር ልጅ አበኔር ያታልልህ ዘንድ፥ መውጫህንና መግቢያህንም ያውቅ ዘንድ፥ የምታደርገውንም ነገር ሁሉ ያስተውል ዘንድ እንደ መጣ አታውቅምን? አለው። ኢዮአብም ከዳዊት በወጣ ጊዜ መልእክተኞችን ከአበኔር በኋላ ላከ፥ ከሴይርም ጕድጓድም መለሱት። ዳዊት ግን ይህን አላወቀም። አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቆይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፥ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ሆዱን መታው፥ ሞተም። በኋላም ይህ ነገር እንደ ተደረገ በሰማ ጊዜ፦ ከኔር ልጅ ከአበኔር ደም በእግዚአብሔር ዘንድ ለዘላለም እኔ ንጽሕ ነኝ፥ መንግሥቴም ንጽሕ ነው፥ በኢዮአብ ራስ ላይና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይምጣበት፥ በኢዮአብም ቤት ፈሳሽ ነገር ያለበት ወይም ለምጻም ወይም አንካሳ ወይም በሰይፍ የሚወድቅ ወይም እንጀራ የሌለው ሰው አይታጣ አለ። ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳም በሰልፍ በገባዖን ወንድማቸውን አሣሄልን ገድሎ ነበርና አበኔርን ገደሉት። ዳዊትም ኢዮአብንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ሁሉ፦ ልብሳችሁን ቅደዱ፥ ማቅም ልበሱ፥ በአበኔርም ፊት አልቅሱ አላቸው። ንጉሡም ዳዊት ከቃሬዛው በኋላ ሄደ። አበኔርንም በኬብሮን ቀበሩት፥ ንጉሡም ድምፁን ከፍ አድርጎ በአበኔር መቃብር አጠገብ አለቀሰ፥ ሕዝቡም ሁሉ አለቀሱ። ንጉሡም ለአበኔር፦ አበኔር ሰነፍ እንደሚሞት ይሞታልን? እጅህ አልታሰረም፥ እግርህም በሰንሰለት አልተያዘም፥ ሰው በዓመፀኞች ፊት እንደሚወድቅ አንተ እንዲሁ ወደቅህ ብሎ የልቅሶ ቅኔ ተቀኘለት። ሕዝቡም ሁሉ ዋይታ አብዝተው አለቀሱ። ሕዝቡም ሁሉ ገና ሳይመሽ ዳዊትን እንጀራ ይበላ ዘንድ ሊጋብዙት መጡ፥ ዳዊት ግን፦ ፀሐይ ሳትጠልቅ እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፥ ይህንም ይጨምርብኝ ብሎ፥ ማለ። ሕዝቡም ሁሉ ይህን ተመለከቱ፥ ደስ አሰኛቸውም፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት ንጉሥ ያደረገው ሁሉ ደስ አሰኛቸው። በዚያም ቀን ሕዝቡ ሁሉ እስራኤልም ሁሉ የኔር ልጅ የአበኔር ሞት ከንጉሡ ዘንድ እንዳልሆነ አወቁ። ንጉሡም ባሪያዎቹን፦ ዛሬ በእስራኤል ዘንድ መኮንንና ታላቅ ሰው እንደ ወደቀ አታውቁምን? እኔም ዛሬ ምንም ለመንገሥ የተቀባሁ ብሆን ደካማ ነኝ፥ እነዚህም ሰዎች የጽሩያም ልጆች በርትተውብኛል፥ እግዚአብሔር ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት አላቸው።

2 ሳሙኤል 3:22-39 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ጥቂት ዘግየት ብሎ ኢዮአብና ሌሎች የዳዊት ወታደሮች ብዙ ምርኮ ካገኙበት ዘመቻ ተመለሱ፤ ይሁን እንጂ አበኔር በዚያን ጊዜ ዳዊት በሰላም አሰናብቶት ሄዶ ስለ ነበር በኬብሮን አልነበረም፤ ኢዮአብና ተከታዮቹ በደረሱም ጊዜ የኔር ልጅ አበኔር ወደ ንጉሥ ዳዊት መጥቶ ንጉሡ አበኔርን በሰላም እንዳሰናበተው ለኢዮአብ ነገሩት። ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ቀርቦ እንዲህ አለው፦ “ይህ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? አበኔር ወደ አንተ መጥቶ ሳለ እንዲሁ እንዲሄድ ያሰናበትከው ስለምንድን ነው? የኔርን ልጅ አበኔርን ታውቀዋለህ፤ እርሱ የመጣው አንተን አታሎ የምትወጣበትንና የምትገባበትን ለማየትና ምን እንደምታደርግ ለመሰለል ነው።” ኢዮአብ ከዳዊት ፊት ወጥቶ ከሄደ በኋላ አበኔርን ያመጡት ዘንድ መልእክተኞች ላከ፤ እነርሱም ከሲራ የውሃ ጒድጓድ አጠገብ መልሰው አመጡለት፤ ዳዊት ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም። አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው። ዳዊትም የአበኔርን መገደል በሰማ ጊዜ እንዲህ አለ፤ “እኔና በንጉሣዊ ግዛቴ ውስጥ ያለው ሕዝብ ስለ አበኔር መገደል ከደሙ ንጹሓን መሆናችንን እግዚአብሔር ያውቃል። ስለዚህም ቅጣቱ በኢዮአብና በቤተሰቡ ላይ ይውረድ! በዘመናት ሁሉ ከቤተሰቡ የአባለ ዘር ወይም የሥጋ ደዌ ያለበት ሰው አይጥፋ! እንዲሁም አካለ ስንኩል የሆነ ሰው፥ በጦር ሜዳ የሚሞት ወይም የሚበላው አጥቶ የሚራብ ሰው አይታጣ!” በዚህ ዐይነት ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳይ ወንድማቸውን ዐሣሄልን በገባዖን በተደረገው ጦርነት ስለ ገደለ አበኔርን ገደሉት። ከዚህ በኋላ ዳዊት በሐዘን ልብሳቸውን ቀደው፥ ማቅ ለብሰው ለአበኔር እንዲያለቅሱ ኢዮአብንና የእርሱ ተከታዮች የሆኑትን ሰዎች አዘዘ፤ በቀብር ሥነ ሥርዓቱም ላይ ንጉሥ ዳዊት ራሱ አስክሬኑን ተከትሎ ሄደ፤ አበኔር በኬብሮን ተቀበረ፤ በመቃብሩም ላይ ንጉሡ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እርሱን በማየት በመረረ ሁኔታ አለቀሱ፤ ዳዊትም ለአበኔር ሐዘኑን በቅኔ ሲገልጥ እንዲህ አለ፦ “አበኔር እንደ ሞኝ ሰው ይሙትን? እጆችህ አልታሰሩም፤ እግሮችህ አልታበቱም፤ ታዲያ፥ በዚህ ሁኔታ ሳለ በወንጀለኞች እጅ እንደሚወድቅ ሰው እንዴት ተገደልክ!” ሕዝቡም ሁሉ ስለ እርሱ እንደገና አለቀሱ። ሰዎችም ቀኑን ሙሉ ዳዊት እህል ይቀምስ ዘንድ ለማግባባት ሞከሩ፤ እርሱ ግን “የዛሬይቱ ጀንበር ሳትጠልቅ እህል ብቀምስ እግዚአብሔር ይቅጣኝ!” ሲል ማለ። ሕዝቡም ሁሉ ይህን ነገር ተመልክተው ደስ አላቸው፤ በእርግጥም ንጉሡ ያደረገው ነገር ሁሉ ሕዝቡን ደስ አሰኛቸው። የዳዊት ሰዎችና መላው የእስራኤል ሕዝብ በአበኔር ሞት ንጉሥ ዳዊት ምንም ያልተባበረ መሆኑን ተገነዘቡ። ንጉሡም ባለሟሎቹ ለሆኑት ባለሥልጣኖች እንዲህ አለ፤ “በዛሬው ቀን በእስራኤል ታላቅ መሪ እንደ ሞተ አታስተውሉምን? ምንም እንኳ እኔ እግዚአብሔር መርጦ የሾመኝ ንጉሥ ብሆን ዛሬ ደካማነት ተሰምቶኛል፤ እነዚህ የጸሩያ ልጆች በእኔ ላይ እጅግ የበረቱ ዐመፀኞች ሆነውብኛል፤ እነዚህን ነፍሰ ገዳዮች እግዚአብሔር ራሱ የሚገባቸውን ቅጣት ይስጣቸው!”

2 ሳሙኤል 3:22-39 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በዚያን ጊዜም የዳዊት አገልጋዮችና ኢዮአብ ብዙ ምርኮ ይዘው ከዘመቻ ተመለሱ። አበኔር ግን ዳዊት በሰላም አሰናብቶት ስለ ሄደ፥ በኬብሮን አልነበረም። ኢዮአብና አብሮት የነበረው ሠራዊት ሁሉ እዚያ እንደ ደረሱ፥ “የኔር ልጅ አበኔር ወደ ንጉሡ መጣ፥ አሰናበተውም እርሱም በሰላም ሄደ” ብለው ለኢዮአብ ነገሩት። ከዚያም ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ገብቶ እንዲህ አለ፤ “ምንድነው ያደረግከው? እነሆ አበኔር መጥቶልህ፥ በሰላም እንዲሄድ ያሰናበትኸው ለምንድነው? የኔርን ልጅ አበኔርን ታውቀዋለህ፤ የመጣው ሊያታልልህ፥ መውጫና መግቢያህን ሊያውቅብህና፥ የምታደርገውን ሁሉ ሊሰልልህ ነው።” ከዚያም ኢዮአብ ከዳዊት ፊት እንደ ወጣ፤ ወደ አበኔር መልክተኞች ላከ፤ መልክተኞቹም ከሲራ የውሃ ጉድጓድ አጠገብ መለሱት። ዳዊት ግን ይህን አላወቀም ነበር። አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፥ ኢዮአብ ለብቻው የሚያነጋግረው በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው። ዳዊት ይህን ነገር ቆይቶ በሰማ ጊዜ እንዲህ አለ፤ “እኔም ሆንሁ መንግሥቴ ከኔር ልጅ ከአበኔር ደም በጌታ ፊት ለዘለዓለም ንጹሕ ነን፤ ደሙ በኢዮአብ ራስና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይሁን፤ ከኢዮአብ ቤት ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ወይም የሥጋ ደዌ ያለበት፥ በምርኲዝ የሚሄድ አንካሳ፥ ወይም በሰይፍ ተመቶ የሚሞት ወይም የሚበላው ያጣ ራብተኛ አይታጣ።” አበኔር ገባዖን ላይ በተደረገው ጦርነት የኢዮአብንና የአቢሳን ወንድም አሣሄልን ገድሎት ስለ ነበር፥ እነርሱም አበኔርን ገደሉት። ከዚያም ዳዊት ለኢዮአብና አብሮት ለነበረው ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብሳችሁን ቀዳችሁና ማቅ ለብሳችሁ በአበኔር ፊት አልቅሱ” አላቸው፤ ንጉሡም ዳዊት ከቃሬዛው በኋላ ሄደ። አበኔርንም በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም ጮኾ በአበኔር መቃብር ላይ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እንደዚሁ አለቀሱ። ንጉሡም ለአበኔር ይህን የኀዘን እንጉርጉሮ ተቀኘ፤ “አበኔር እንደ ተራ ሰው ይሙት? እግሮችህ በእግር ብረት አልገቡም፤ ሰው በክፉ ሰዎች ፊት እንደሚወድቅ አንተም እንደዚሁ ወደቅህ።” ሕዝቡም ሁሉ እንደገና አለቀሱለት። ከዚያም ሕዝቡም ሁሉ ገና ሳይመሽ ዳዊትን እንጀራ እንዲበላ አጥብቀው ለመኑት። ዳዊት ግን፥ “ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ያድርግብኝ ከዚያም የባሰ ያምጣብኝ” ብሎ ማለ። ሕዝቡም ሁሉ ይህንኑ ተመልክተው ደስ አላቸው፤ በእርግጥ ንጉሡ ያደረገው ሁሉ ሕዝቡን ደስ አሰኛቸው። በዚያን ዕለት ሕዝቡ ሁሉና እስራኤል በሙሉ ንጉሡ በኔር ልጅ በአበኔር ሞት እጁ እንዳልነበረበት ዐወቁ። ከዚያም ንጉሡ ለአገልጋዮቹ እንዲህ አለ፤ “በዛሬዪቱ ዕለት በእስራኤል መስፍንና ታላቅ ሰው መውደቁን አላወቃችሁምን? ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፥ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። ጌታ ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።”