2 ጴጥሮስ 1:2-17
2 ጴጥሮስ 1:2-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የመለኮቱ ኀይል በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ በተስፋው ቃል ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን። ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥ በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ። እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤ እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፤ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፤ የቀደመውንም ኀጢአቱን መንጻት ረስቶአል። ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና። እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና። ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ምንም ብታውቁ፥ በእናንተም ዘንድ ባለ እውነት ምንም ብትጸኑ፥ ስለ እነዚህ ዘወትር እንዳሳስባችሁ ቸል አልልም። ሁልጊዜም በዚህ አካል ሳለሁ በማሳሰቤ ላነቃችሁ የሚገባኝ ይመስለኛል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ አካሌ መለየቴ ፈጥኖ እንዲሆን አውቃለሁና። ከመውጣቴም በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ። የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኀይልና መምጣት አስታወቅናችሁ። ከገናናው ክብር “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤” የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ምስጋናን ተቀብሎአልና፤
2 ጴጥሮስ 1:2-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔርንና ጌታችን ኢየሱስን በማወቅ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን እርሱን በማወቅ ለሕይወትና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልገንን ሁሉ የመለኮቱ ኀይል ሰጥቶናል። ከክፉ ምኞት የተነሣ በዓለም ካለው ምግባረ ብልሹ ሕይወት አምልጣችሁ፣ ከመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ በእነዚህ ነገሮች አማካይነት እጅግ ታላቅና ክቡር የሆነውን ተስፋ ሰጥቶናል። በዚህም ምክንያት በሙሉ ትጋት በእምነታችሁ ላይ በጎነትን ለመጨመር ጣሩ፤ በበጎነት ላይ ዕውቀትን፣ በዕውቀት ላይ ራስን መግዛት፣ ራስን በመግዛት ላይ መጽናትን፣ በመጽናት ላይ እውነተኛ መንፈሳዊነትን፣ በእውነተኛ መንፈሳዊነት ላይ ወንድማዊ መተሳሰብን፣ በወንድማዊ መተሳሰብ ላይ ፍቅርን ጨምሩ። እነዚህ ባሕርያት ተትረፍርፈው ቢኖሯችሁ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ዳተኞችና ፍሬ ቢሶች ከመሆን ይጠብቋችኋል። እነዚህ ባሕርያት የሌሉት ግን የሩቁን የማያይ ወይም ዕውር ነው፤ ከቀድሞው ኀጢአቱ መንጻቱንም ረስቷል። ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማጽናት ከፊት ይልቅ ትጉ፤ ምክንያቱም እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም። በዚህም ወደ ጌታችንና አዳኛችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋል። ስለዚህ ምንም እንኳ እነዚህን ነገሮች ብታውቋቸውና በያዛችሁት እውነት ብትጸኑም፣ ስለ እነዚህ ነገሮች እናንተን ዘወትር ከማሳሰብ ቸል አልልም። በዚህ ምድራዊ ድንኳን ውስጥ እስካለሁ ድረስ እናንተን መጐትጐት ትክክል ሆኖ ይታየኛል፤ ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ገለጠልኝ ይህን ምድራዊ ድንኳን ቶሎ ጥዬ እንደምሄድ ዐውቃለሁ፤ እነዚህን ነገሮች ከተለየኋችሁም በኋላ ዘወትር ታስቡ ዘንድ እተጋለሁ። ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኀይልና ስለ መምጣቱ የነገርናችሁ የእርሱን ግርማ በዐይናችን አይተን እንጂ፣ በሰዎች ጥበብ የተፈጠረውን ተረት ተከትለን አይደለም፤ ምክንያቱም ከግርማዊው ክብር “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው” የሚል ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርና ሞገስ ተቀብሏል፤
2 ጴጥሮስ 1:2-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን። ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥ በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ። እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤ እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል። ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና። እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና። ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ምንም ብታውቁ በእናንተም ዘንድ ባለ እውነት ምንም ብትጸኑ፥ ስለ እነዚህ ዘወትር እንዳሳስባችሁ ቸል አልልም። ሁልጊዜም በዚህ ማደሪያ ሳለሁ በማሳሰቤ ላነቃችሁ የሚገባኝ ይመስለኛል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ ማደሪያዬ መለየቴ ፈጥኖ እንዲሆን አውቃለሁና። ከመውጣቴም በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ። የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይልና መምጣት አስታወቅናችሁ። ከገናናው ክብር፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ምስጋናን ተቀብሎአልና፤
2 ጴጥሮስ 1:2-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔርንና ጌታችንን ኢየሱስን በማወቅ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። በክብሩና በደግነቱ የጠራንን እርሱን በማወቃችን መለኮታዊ ኀይሉ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለማምለክ የሚያስፈልገንን ሁሉ ሰጥቶናል። በክብሩና በቸርነቱ ክቡር ዋጋ ያለውንና እጅግ ታላቅ የሆነውን ተስፋውን አግኝተናል፤ በእነዚህም አማካይነት እናንተ በክፉ ምኞት ምክንያት በዚህ ዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች ሆናችኋል። በዚህ ምክንያት የሚከተሉት ነገሮች እንዲጨመሩላችሁ ትጉ፦ በእምነት ላይ ደግነትን፥ በደግነት ላይ ዕውቀትን፥ በዕውቀት ላይ ራስ መቈጣጠርን፥ በራስ መቈጣጠር ላይ በትዕግሥት መጽናትን፥ በትዕግሥት በመጽናት ላይ እግዚአብሔርን ማምለክን፥ እግዚአብሔርን በማምለክ ላይ የወንድማማችነት መዋደድን፥ በወንድማማችነት መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ። እነዚህ ነገሮች በብዛት ቢኖሩአችሁ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማወቅ የማትጠቅሙ ፍሬቢሶች እንዳትሆኑ ይጠብቁአችኋል። እነዚህ ነገሮች የሌሉት ግን የሩቁን ነገር ማየት የማይችል ዕውር ነው፤ ካለፉት ኃጢአቶቹም መንጻቱን ረስቶአል። ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማረጋገጥ በይበልጥ የምትጓጉ ሁኑ፤ ይህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም። በዚህ ዐይነት ዘለዓለማዊት ወደሆነችው ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት ለመግባት ሙሉ መብት ይሰጣችኋል። እነዚህን ነገሮች ብታውቁአቸውና በያዛችሁት እውነት ጸንታችሁ ብትኖሩም እንኳ እነርሱን ለእናንተ ከማሳሰብ ቸል አልልም። በዚህ ሕይወት እስካለሁበት ጊዜ ድረስ እናንተን ዘወትር ማነቃቃት ትክክል መስሎ ይታየኛል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ገለጠልኝ በቶሎ ከዚህ ዓለም በሞት እንደምለይ ዐውቃለሁ። እኔ አሁን የምተጋው በሞት ከተለየኋችሁ በኋላ እንኳ እነዚህን ነገሮች ዘወትር ማስታወስ እንድትችሉ ነው። ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኀይልና ስለ ዳግመኛ መምጣቱም በነገርናችሁ ጊዜ ራሳችን ግርማውን በዐይናችን አይተን የምንመሰክር እንጂ በሰው ተንኰል የታቀደውን ተረት ተከትለን አይደለም። “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው!” የሚል ድምፅ ከታላቁ ክብር በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ገናናነትን ተቀብሎአል።
2 ጴጥሮስ 1:2-17 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። በመለኮቱ ኃይል በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ሰጠን። በእነዚህም አማካኝነት፥ ከክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ፥ በተስፋው ቃል ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ፥ በክብርና በበጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን። በዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ ሠናይነትን ጨምሩ፥ በሠናይነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችነት መዋደድ፥ በወንድማማችነትም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ። እነዚህ ነገሮች ቢኖሩአችሁና ቢበዙላችሁ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ በተመለከተ ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጓችኋልና፤ እነዚህ ነገሮች የሌሉት ግን የሩቁን ነገር ማየት የማይችል ዕውር ነው፤ ከቀደመው ኀጢአቱም መንጻቱን ረስቷአል። ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁንና መመረጣችሁን እንድታጸኑ፥ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ ይህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም። በዚህ መልክ፥ ወደ ዘለዓለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋል። ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ምንም ብታውቁና፥ በእናንተም ዘንድ ባለ እውነት ጸንታችሁ ብትኖሩም፥ ስለ እነዚህ ዘወትር ከማሳሰብ ቸል አልልም። በዚህ ሕይወት እስካለሁበት ጊዜ ድረስ እናንተን ዘወትር ማነቃቃት ትክክል መስሎ ይታየኛል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቴ ፈጥኖ እንደሚሆን አውቃለሁና፤ ከመለየቴም በኋላ እነዚህን ነገሮች፥ በየትኛውም ጊዜ ማሰብ ትችሉ ዘንድ፥ በብርቱ እተጋለሁ። ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይልና መምጣቱም በነገርናችሁ ጊዜ፥ ራሳችን ግርማውን በዐይናችን አይተን የምንመሰክር እንጂ፥ በሰው ብልጠት የታቀደውን ተረት ተከትለን አይደለም። ከግርማዊው ክብር “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው!” የሚል ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ገናናነትን ተቀብሏል።