የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2 ነገሥት 4:8-17

2 ነገሥት 4:8-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከዚ​ህም በኋላ አንድ ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ኤል​ሳዕ ወደ ሱማን አለፈ፤ በዚ​ያም ታላቅ ሴት ነበ​ረች፤ እን​ጀ​ራም ይበላ ዘንድ አቆ​መ​ችው፤ በዚ​ያም ባለፈ ቍጥር እን​ጀራ ሊበላ ወደ​ዚያ ይገባ ነበር። ሴት​ዮ​ዋም ለባ​ልዋ፥ “ይህ በእኛ ዘንድ ሁል​ጊዜ የሚ​ያ​ል​ፈው ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆነ አው​ቃ​ለሁ። ትንሽ ቤት በሰ​ገ​ነቱ ላይ እን​ሥራ፤ በዚ​ያም አል​ጋና ጠረ​ጴዛ፥ ወን​በ​ርና መቅ​ረዝ እና​ኑ​ር​ለት፤ ወደ እኛም ሲመጣ ወደ​ዚያ ይግባ” አለ​ችው። አንድ ቀንም ወደ​ዚያ በመጣ ጊዜ ወደ ቤቱ ገብቶ በዚያ ተኛ። ሎሌ​ው​ንም ግያ​ዝን፥ “ይህ​ችን ሱማ​ና​ዊት ጥራ” አለው። በጠ​ራ​ትም ጊዜ በፊቱ ቆመች። እር​ሱም፥ “እነሆ፥ ይህን ሁሉ ክብር አከ​በ​ር​ሽኝ ምን ላድ​ር​ግ​ልሽ? ለን​ጉሥ ወይስ ለሠ​ራ​ዊት አለቃ የም​ነ​ግ​ር​ልሽ ጉዳይ እን​ዳ​ለሽ በላት” አለው፤ እር​ስ​ዋም፥ “እኔ በወ​ገኔ መካ​ከል እኖ​ራ​ለሁ” ብላ መለ​ሰች። እር​ሱም ግያ​ዝን፥ “እን​ግ​ዲህ ምን እና​ድ​ር​ግ​ላት?” አለው። ሎሌው ግያ​ዝም፤ “ልጅ የላ​ትም፥ ባል​ዋም ሸም​ግ​ሎ​አል” ብሎ መለሰ። እር​ሱም፥ “ጥራት” አለው። ጠራ​ትም በደ​ጃ​ፉም ቆመች። ኤል​ሳ​ዕም፥ “በሚ​መ​ጣው ዓመት በዚህ ወራት ወንድ ልጅ ትታ​ቀ​ፊ​ያ​ለሽ” አላት፤ እር​ስ​ዋም፥ “አይ​ደ​ለም ጌታዬ ሆይ፥ አገ​ል​ጋ​ይ​ህን አትዋ​ሻት” አለ​ችው። ከዚ​ያም በኋላ ሴቲቱ ፀነ​ሰች፥ በዓ​መ​ቱም ኤል​ሳዕ በነ​ገ​ራት ወራት ወንድ ልጅ ወለ​ደች።

2 ነገሥት 4:8-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደ ሱነም ሄደ። በዚያም አንዲት ሀብታም ሴት ነበረች፤ እርሷም ምግብ እንዲበላ አጥብቃ ለመነችው፤ በዚያም ባለፈ ቍጥር ምግብ ለመብላት ወደ ቤቷ ይገባ ነበር። ሴቲቱም ባልዋን እንዲህ አለችው፤ “ይህ አዘውትሮ በደጃችን የሚያልፍ ሰው፣ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው መሆኑን ዐውቃለሁ፤ ስለዚህ በሰገነቱ ላይ አንዲት ትንሽ ክፍል ቤት ሠርተን ዐልጋና ጠረጴዛ፣ ወንበርና ፋኖስ እናስገባለን፤ ከዚያም ወደ እኛ በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ ማረፊያ ትሆነዋለች።” አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደዚያው መጥቶ ወደ ማረፊያ ክፍሉ በመውጣት ጋደም አለ። አገልጋዩን ግያዝንም፣ “ሱነማዪቱን ጥራት” አለው፤ በጠራትም ጊዜ መጥታ በፊቱ ቆመች። ኤልሳዕም፣ “ ‘ለእኛ ስትይ በጣም ተቸግረሻል፤ ምን እንዲደረግልሽ ትፈልጊአለሽ? ለንጉሡ ወይስ ለሰራዊቱ አዛዥ የምንነግርልሽ ጕዳይ አለን?’ ብለህ ጠይቃት” አለው። ሴቲቱም መልሳ፣ “እኔ እኮ የምኖረው በገዛ ወገኖቼ መካከል ነው” አለችው። ኤልሳዕም፣ “ታዲያ ምን ይደረግላት” ሲል ጠየቀ። ግያዝም፣ “ልጅ እኮ የላትም፤ ባሏም ሸምግሏል” አለ። ኤልሳዕም፣ “በል እንግዲያው ጥራት” አለው፤ እርሱም ጠርቷት መጥታ በራፉ ላይ ቆመች። ኤልሳዕም፣ “የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት፤ እርሷም፣ “አይደለም ጌታዬ፣ አንተ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ ኋላ አገልጋይህን መዋሸት እንዳይሆንብህ!” አለችው። ሴትዮዋም ፀነሰች፤ ኤልሳዕ እንደ ነገራትም በተባለው ጊዜ ወንድ ልጅ ወለደች።

2 ነገሥት 4:8-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

አንድ ቀንም እንዲህ ሆነ፤ ኤልሳዕ ወደ ሱነም አለፈ፤ በዚያም ታላቅ ሴት ነበረች፤ እንጀራ ይበላ ዘንድ የግድ አለችው፤ በዚያም ባለፈ ቍጥር እንጀራ ሊበላ ወደዚያ ይገባ ነበር። ለባልዋም “ይህ በእኛ ዘንድ ሁልጊዜ የሚያልፈው ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆነ አውቃለሁ። ትንሽ ቤት በሰገነቱ ላይ እንሥራ፤ በዚያም አልጋ፥ ጠረጴዛ፥ ወንበርና መቅረዝ እናኑርለት፤ ወደ እኛም ሲመጣ ወደዚያ ይገባል፤” አለችው። አንድ ቀንም ወደዚያ በመጣ ጊዜ ወደ ቤቱ ገብቶ በዚያ ዐረፈ። ሎሌውንም ግያዝን “ይህችን ሱነማዊት ጥራ፤” አለው። በጠራትም ጊዜ በፊቱ ቆመች። እርሱም “እነሆ፥ ይህን ሁሉ አሳብ አሰብሽልኝ፤ አሁንስ ምን ላድርግልሽ? ለንጉሥ ወይስ ለሠራዊት አለቃ ልንገርልሽን? በላት፤” አለው፤ እርስዋም “እኔ በወገኔ መካከል ተቀምጫለሁ፤” ብላ መለሰች። እርሱም “እንግዲህ ምን እናድርግላት?” አለ። ግያዝም “ልጅ የላትም፤ ባልዋም ሸምግሎአል፤” ብሎ መለሰ። እርሱም “ጥራት” አለ። በጠራትም ጊዜ በደጃፉ ቆመች። እርሱም “በሚመጣው ዓመት በዚህ ወራት ወንድ ልጅ ትታቀፊአለሽ፤” አለ፤ እርስዋም “አይደለም፤ ጌታዬ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ባሪያህን እንዳትዋሻት እለምንሃለሁ፤” አለች። ሴቲቱም ፀነሰች፤ በዚያም ወራት በአዲሱ ዓመት ኤልሳዕ እንዳላት ወንድ ልጅ ወለደች።

2 ነገሥት 4:8-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርስዋም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፤ እርስዋም ባልዋን እንዲህ አለችው፤ “ብዙ ጊዜ ወደ ቤታችን የሚመጣው ይህ ሰው የተቀደሰ የእግዚአብሔር ሰው ስለ መሆኑ እርግጠኛ ነኝ፤ ስለዚህም በሰገነቱ ላይ አንድ ትንሽ ክፍል ሠርተን በዚያች ውስጥ አንድ አልጋ፥ አንድ ጠረጴዛ፥ አንድ ወንበርና አንድ የፋኖስ መብራት እናኑርለት፤ እርሱም እኛን ለመጐብኘት በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ ማረፊያ ትሆነዋለች።” አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደ ሱነም ተመልሶ ሄደ፤ ዕረፍት ለማድረግም ወደ ተሠራለት ክፍል ገብቶ ዐረፈ፤ ግያዝ ተብሎ የሚጠራውንም አገልጋዩን፥ “ሄደህ ሱነማዊትን ጥራ” አለው፤ እርስዋም መጥታ በፊቱ ቆመች። ግያዝ “ለእኛ ስላደረገችው መልካም ነገር ሁሉ ምን አደርግላት ዘንድ እንደምትፈልግ ጠይቃት፤ ምናልባት ወደ ንጉሡ ወይም ወደ ጦር አዛዡ ዘንድ ሄጄ የምነግርላት ጉዳይ ሊኖር ይችላል” አለው። እርስዋም “በዘመዶች መካከል በምኖርበት በዚህ ስፍራ ምንም የሚቸግረኝ ነገር የለም” ስትል መለሰችለት። ኤልሳዕም ግያዝም “ታዲያ ምን ላደርግላት እችላለሁ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም “እነሆ፥ ልጅ የላትም፤ ባልዋም ሽማግሌ ነው” ሲል መለሰ። ኤልሳዕም “እንድትመጣ ንገራት” ብሎ አዘዘው። እርስዋም መጥታ በበሩ አጠገብ ቆመች፤ ኤልሳዕም “በመጪው ዓመት ልክ ይህን ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት። እርስዋም፦ “አይደለም! ጌታዬ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! እባክህ የማይፈጸም የተስፋ ቃል አትንገረኝ!” አለችው። ነገር ግን ሴቲቱ ፀነሰች፤ ልክ ኤልሳዕ የተናገረው ጊዜ ሲደርስ በተከታዩ ዓመት ወንድ ልጅ ወለደች።

2 ነገሥት 4:8-17 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርሷም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፤ እርሷም ባሏን እንዲህ አለችው፤ “ብዙ ጊዜ ወደ ቤታችን የሚመጣው ይህ ሰው የተቀደሰ የእግዚአብሔር ሰው ስለ መሆኑ እርግጠኛ ነኝ፤ ስለዚህም በሰገነቱ ላይ አንድ ትንሽ ክፍል ሠርተን በዚያች ውስጥ አንድ አልጋ፥ አንድ ጠረጴዛ፥ አንድ ወንበርና አንድ የፋኖስ መብራት እናኑርለት፤ እርሱም እኛን ለመጐብኘት በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ ማረፊያ ትሆነዋለች።” አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደ ሱነም ተመልሶ ሄደ፤ ዕረፍት ለማድረግም ወደ ተሠራለት ክፍል ገብቶ ዐረፈ፤ ግያዝ ተብሎ የሚጠራውንም አገልጋዩን፥ “ሄደህ ሱነማዊትን ጥራ” አለው፤ እርሷም መጥታ በፊቱ ቆመች። ግያዝ “ለእኛ ስላደረገችው መልካም ነገር ሁሉ ምን አደርግላት ዘንድ እንደምትፈልግ ጠይቃት፤ ምናልባት ወደ ንጉሡ ወይም ወደ ጦር አዛዡ ዘንድ ሄጄ የምነግርላት ጉዳይ ሊኖር ይችላል” አለው። እርሷም “በዘመዶች መካከል በምኖርበት በዚህ ስፍራ ምንም የሚቸግረኝ ነገር የለም” ስትል መለሰችለት። ኤልሳዕም ግያዝም “ታዲያ ምን ላደርግላት እችላለሁ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም “እነሆ፥ ልጅ የላትም፤ ባሏም ሽማግሌ ነው” ሲል መለሰ። ኤልሳዕም “እንድትመጣ ንገራት” ብሎ አዘዘው። እርሷም መጥታ በበሩ አጠገብ ቆመች፤ ኤልሳዕም “በመጪው ዓመት ልክ ይህን ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት። እርሷም፦ “አይደለም! ጌታዬ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! እባክህ የማይፈጸም የተስፋ ቃል አትንገረኝ!” አለችው። ነገር ግን ሴቲቱ ፀነሰች፤ ልክ ኤልሳዕ የተናገረው ጊዜ ሲደርስ በተከታዩ ዓመት ወንድ ልጅ ወለደች።