2 ነገሥት 1:12
2 ነገሥት 1:12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኤልያስም “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ!” አለው፤ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር እሳት መኰንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ።
2 ነገሥት 1:12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኤልያስም፥ “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፤ አንተንም፥ አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ” አለው። እሳትም ከሰማይ ወርዳ እርሱንና አምሳውን ሰዎች በላች።
2 ነገሥት 1:12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኤልያስም መልሶ፣ “እኔ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንሁ እሳት ከሰማይ ወርዳ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ትብላ!” አለው፤ ከዚያም እሳት ከሰማይ ወርዳ እርሱንና ሰዎቹን ፈጽማ በላች።
2 ነገሥት 1:12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኤልያስም “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፤ አንተንም፥ አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ፤” አለው። የእግዚአብሔርም እሳት ከሰማይ ወርዳ እርሱንና አምሳ ሰዎቹን በላች።