1 ጢሞቴዎስ 4:11-16
1 ጢሞቴዎስ 4:11-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው። እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም ተጠንቀቅ። በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል። ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አስብ፤ ይህንም አዘውትር። ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።
1 ጢሞቴዎስ 4:11-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እነዚህን ነገሮች እዘዝ፤ አስተምርም። ወጣትነትህን ማንም አይናቅ፤ ነገር ግን ለሚያምኑት በንግግርና በኑሮ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርኣያ ሁንላቸው። እኔ እስክመጣ ድረስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለሕዝብ ለማንበብ፣ ለመምከርና ለማስተማር ትጋ። ሽማግሌዎች እጃቸውን በአንተ ላይ ሲጭኑ በትንቢት የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል። ሰው ሁሉ ማደግህን ያይ ዘንድ በእነዚህ ነገሮች ላይ አትኵር፤ በትጋትም ፈጽማቸው። ለሕይወትህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፣ ራስህንና የሚሰሙህንም ታድናለህና።
1 ጢሞቴዎስ 4:11-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው። እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም ተጠንቀቅ። በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን፥ በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል። ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አስብ፥ ይህንም አዘውትር። ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።
1 ጢሞቴዎስ 4:11-16 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እነዚህን ነገሮች እዘዝ፤ አስተምርም፤ ወጣት በመሆንህ ማንም አይናቅህ፤ ይልቅስ በንግግር፥ በኑሮ፥ በፍቅር፥ በእምነትና በንጽሕና ለአማኞች መልካም ምሳሌ ሁን። እኔ እስክመጣ ድረስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለሕዝብ በማንበብ፥ በመስበክና በማስተማር ትጋ። ትንቢት በተነገረልህ ጊዜና የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችም እጃቸውን በጫኑብህ ጊዜ የተሰጠህን በአንተ ያለውን መንፈሳዊ ስጦታ አትዘንጋ። መሻሻልህን ሰዎች ሁሉ እንዲያዩ በእነዚህ ነገሮች ትጋ፤ እነዚህንም ነገሮች በሥራ ላይ በማዋል ሁለንተናህን ለእነርሱ ስጥ። ለራስህና ለማስተማር ሥራህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ነገሮች ጽና፤ ይህን በማድረግም ራስህንና የሚሰሙህን ታድናለህ።
1 ጢሞቴዎስ 4:11-16 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እነዚህን ነገሮች እዘዝ፤ አስተምርም፤ ማንም ወጣትነትህን አይናቀው፤ ይልቅስ በንግግር፥ በኑሮ፥ በፍቅር፥ በእምነት፥ በንጽሕና፥ ለሚያምኑት ምሳሌ ሁን። እስክመጣ ድረስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለሕዝቡ በማንበብ፥ በመምከርና በማስተማር ትጋ። ሽማግሌዎች እጃቸውን በአንተ ላይ የጫኑ ጊዜ በትንቢት የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል። እድገትህ በሁሉ ሰው ፊት እንዲገለጥ እነዚህን ነገሮች በጥንቃቄ በሥራ ላይ አውል፤ ለእነርሱም ራስህን ሙሉ በሙሉ በመስጠት ትጋ። ለራስህና ለምታስተምረው ትምህርት ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ነገሮች ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንና የሚሰሙህን ታድናለህ።