1 ተሰሎንቄ 5:16-22
1 ተሰሎንቄ 5:16-22 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። መንፈስን አታጥፉ፤ ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤ ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።
Share
1 ተሰሎንቄ 5 ያንብቡ1 ተሰሎንቄ 5:16-22 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በማናቸውም ሁኔታ አመስግኑ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ይህ ነውና። የመንፈስን እሳት አታዳፍኑ፤ ትንቢትን አትናቁ። ነገር ግን ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ፤ ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።
Share
1 ተሰሎንቄ 5 ያንብቡ1 ተሰሎንቄ 5:16-22 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። መንፈስን አታጥፉ፤ ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤ ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ።
Share
1 ተሰሎንቄ 5 ያንብቡ1 ተሰሎንቄ 5:16-22 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ባለማቋረጥ ጸልዩ፤ በሁሉ ነገር እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ሕይወት እግዚአብሔር ከእናንተ የሚፈልገው ይህን ነው። የመንፈስ ቅዱስን ሥራ አታዳፍኑ፤ የትንቢትን ስጦታ አትናቁ፤ ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ። ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።
Share
1 ተሰሎንቄ 5 ያንብቡ