የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ሳሙኤል 5:1-5

1 ሳሙኤል 5:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወሰ​ዱ​አት፤ ከአ​ቤ​ኔ​ዜ​ርም ወደ አዛ​ጦን ይዘ​ዋት መጡ። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወስ​ደው ወደ ዳጎን ቤት አገ​ቡ​አት፤ በዳ​ጎ​ንም አጠ​ገብ አኖ​ሩ​አት። በነ​ጋ​ውም የአ​ዛ​ጦን ሰዎች ማለዱ፤ ወደ ዳጎ​ንም ቤት ገቡ፤ እነ​ሆም፥ ዳጎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ አገ​ኙት፤ ዳጎ​ን​ንም አን​ሥ​ተው በስ​ፍ​ራው አቆ​ሙት። በነ​ጋ​ውም ማለዱ፤ እነ​ሆም፥ ዳጎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ነበር፤ የዳ​ጎ​ንም ራስ፥ ሁለቱ እጆ​ቹም ተቈ​ር​ጠው እየ​ራ​ሳ​ቸው በመ​ድ​ረኩ ላይ ወድ​ቀው ነበር፤ ሁለቱ መሀል እጆ​ቹም በወ​ለሉ ላይ ወድ​ቀው ነበር። የዳ​ጎ​ንም ደረት ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር። ስለ​ዚ​ህም የዳ​ጎን ካህ​ናት፥ ወደ ዳጎን ቤት የሚ​ገ​ቡ​ትም ሁሉ በአ​ዛ​ጦን ያለ​ውን የዳ​ጎ​ንን መድ​ረክ እስከ ዛሬ ድረስ አይ​ረ​ግ​ጡም፤ ይራ​መ​ዱት ነበር እንጂ።