የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ሳሙኤል 17:20-58

1 ሳሙኤል 17:20-58 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ዳዊ​ትም ማልዶ ተነሣ፤ በጎ​ቹ​ንም ለጠ​ባቂ ተወ፤ እሴ​ይም ያዘ​ዘ​ውን ይዞ ሄደ፤ ጭፍ​ራ​ውም ተሰ​ልፎ ሲወጣ፥ ለሰ​ል​ፍም ሲጮኽ በሰ​ረ​ገ​ሎች ወደ ተከ​በ​በው ሰፈር መጣ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሠራ​ዊ​ትም ፊት ለፊት ተሰ​ላ​ል​ፈው ነበር። ዳዊ​ትም ዕቃ​ውን በዕቃ ጠባ​ቂው እጅ አኖ​ረው፤ ወደ​ሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ሮጦ ሄደ፤ የወ​ን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ደኅ​ን​ነት ጠየቀ። እር​ሱም ሲነ​ጋ​ገ​ራ​ቸው፥ እነሆ፥ ጎል​ያድ የተ​ባለ ያ አር​በኛ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ የጌት ሰው ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍራ መካ​ከል ወጣ፤ ቀድሞ የተ​ና​ገ​ረ​ው​ንም ቃል ተና​ገረ፤ ዳዊ​ትም ሰማ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ሰው​ዬ​ውን ባዩ ጊዜ እጅግ ፈር​ተው ከፊቱ ሸሹ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች፥ “ይህን የወ​ጣ​ውን ሰው አያ​ች​ሁ​ትን? በእ​ው​ነት እስ​ራ​ኤ​ልን ሊገ​ዳ​ደር ወጣ፤ የሚ​ገ​ድ​ለ​ው​ንም ሰው ንጉሡ እጅግ ባለ​ጠጋ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ ልጁ​ንም ይድ​ር​ለ​ታል፤ ያባ​ቱ​ንም ቤተ ሰብ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ከግ​ብር ነጻ ያወ​ጣ​ቸ​ዋል” አሉ። ዳዊ​ትም በአ​ጠ​ገቡ ለቆ​ሙት ሰዎች፦ ይህን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ለሚ​ገ​ድል፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተግ​ዳ​ሮ​ትን ለሚ​ያ​ርቅ ሰው በውኑ ይህ ይደ​ረ​ግ​ለ​ታል? የሕ​ያው አም​ላ​ክን ጭፍ​ሮች የሚ​ገ​ዳ​ደር ይህ ያል​ተ​ገ​ረዘ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ማን ነው?” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው። ሕዝ​ቡም፥ “ለሚ​ገ​ድ​ለው ሰው እን​ዲህ ይደ​ረ​ግ​ለ​ታል” ብለው እንደ ቀድ​ሞው መለ​ሱ​ለት። ታላቅ ወን​ድ​ሙም ኤል​ያብ ከሰ​ዎች ጋር ሲነ​ጋ​ገር ሰማ፤ ኤል​ያ​ብም በዳ​ዊት ላይ እጅግ ተቈጣ፥ “ለምን ወደ​ዚህ ወረ​ድህ? እነ​ዚ​ያ​ንስ ጥቂ​ቶች በጎች በም​ድረ በዳ ለማን ተው​ሃ​ቸው? እኔ ኵራ​ት​ህ​ንና የል​ብ​ህን ክፋት አው​ቃ​ለ​ሁና ሰል​ፉን ለማ​የት መጥ​ተ​ሃል” አለው። ዳዊ​ትም፥ “እኔ ምን አደ​ረ​ግሁ? ይህ ታላቅ ነገር አይ​ደ​ለ​ምን?” አለ። ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ወደ ሌላ ሰው ዘወር አለ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ያለ ነገር ተና​ገረ፤ ሕዝ​ቡም እንደ ቀድ​ሞው ያለ ነገር መለ​ሱ​ለት። ዳዊ​ትም የተ​ና​ገ​ረው ቃል ተሰማ፤ ለሳ​ኦ​ልም ነገ​ሩት፤ ወደ እር​ሱም ወሰ​ደው። ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “ስለ እርሱ የማ​ንም ልብ አይ​ው​ደቅ፤ እኔ ባሪ​ያህ ሄጄ ያን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ እወ​ጋ​ዋ​ለሁ” አለው። ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “አንተ ገና ብላ​ቴና ነህና፥ እር​ሱም ከብ​ላ​ቴ​ን​ነቱ ጀምሮ ጦረኛ ነውና ይህን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ለመ​ው​ጋት ትሄድ ዘንድ አት​ች​ልም” አለው። ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን አለው፥ “እኔ ባሪ​ያህ የአ​ባ​ቴን በጎች ስጠ​ብቅ አን​በሳ ወይም ድብ ይመጣ ነበር፤ ከመ​ን​ጋ​ውም ጠቦት ይወ​ስድ ነበር። በኋ​ላ​ውም እከ​ተ​ለ​ውና እመ​ታው ነበር። ከአ​ፉም አስ​ጥ​ለው ነበር፤ በተ​ነ​ሣ​ብ​ኝም ጊዜ ጕሮ​ሮ​ውን አንቄ እመ​ታ​ውና እገ​ድ​ለው ነበር። እኔ ባሪ​ያህ አን​በ​ሳና ድብ ገደ​ልሁ፤ ይህም ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ ይሆ​ናል። እን​ግ​ዲህ እገ​ድ​ለው ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተግ​ዳ​ሮ​ትን አስ​ወ​ግድ ዘንድ ዛሬ አል​ሄ​ድ​ምን? የሕ​ያው አም​ላክ ጭፍ​ሮ​ችን ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምን​ድን ነው?” ዳዊ​ትም፥ “ከአ​ን​በ​ሳና ከድብ እጅ ያስ​ጣ​ለኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ያል​ተ​ገ​ረዘ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ እጅ ያስ​ጥ​ለ​ኛል” አለ። ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ሂድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሁን” አለው። ሳኦ​ልም ለዳ​ዊት ጥሩር አለ​በ​ሰው፤ በራ​ሱም ላይ የናስ ቍር ደፋ​ለት። ዳዊ​ት​ንም ሰይ​ፉን በል​ብሱ ላይ አስ​ታ​ጠ​ቀው፤ ዳዊ​ትም አን​ድና ሁለት ጊዜ ሲራ​መድ ደከመ። ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “አለ​መ​ድ​ሁ​ምና በዚህ መሄድ አል​ች​ልም” አለው። ከላ​ዩም አወ​ለ​ቁ​ለት። ዳዊ​ትም በት​ሩን በእጁ ያዘ፤ ከወ​ን​ዝም አም​ስት ድብ​ል​ብል ድን​ጋ​ዮ​ችን መረጠ፤ በእ​ረኛ ኮሮ​ጆ​ውም በኪሱ ከተ​ታ​ቸው፤ ወን​ጭ​ፍም በእጁ ነበረ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ቀረበ። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም መጥቶ ወደ ዳዊት ቀረበ፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በፊቱ ይሄድ ነበር። ጎል​ያ​ድም ዳዊ​ትን ትኩር ብሎ አየው፤ ቀይ ብላ​ቴና፥ መል​ኩም ያማረ ነበ​ረና ናቀው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “በት​ርና ድን​ጋይ ይዘህ የም​ት​መ​ጣ​ብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “የለም ከውሻ ትከ​ፋ​ለህ” አለው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን በአ​ም​ላ​ኮቹ ረገ​መው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “ወደ እኔ ና፤ ሥጋ​ህ​ንም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው። ዳዊ​ትም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን አለው፥ “አንተ ሰይ​ፍና ጦር፥ ጋሻም ይዘህ ትመ​ጣ​ብ​ኛ​ለህ፤ እኔ ግን ዛሬ በተ​ገ​ዳ​ደ​ር​ኸው በእ​ስ​ራ​ኤል ጭፍ​ሮች አም​ላክ ስም በሰ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ አን​ተን በእጄ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፤ እመ​ታ​ህ​ማ​ለሁ፤ ራስ​ህ​ንም ከአ​ንተ እቈ​ር​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ሬሳ​ህ​ንና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ሠራ​ዊት ሬሶች ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት ዛሬ እሰ​ጣ​ለሁ። ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር እን​ዳለ ያው​ቃሉ፤ ይህም ጉባኤ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ይ​ፍና በጦር የሚ​ያ​ድን እን​ዳ​ይ​ደለ ያው​ቃል። ሰልፉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እና​ን​ተን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።” ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ተነ​ሥቶ ዳዊ​ትን ሊገ​ና​ኘው በቀ​ረበ ጊዜ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ሊገ​ና​ኘው ወደ ሰልፉ ሮጠ። ዳዊ​ትም እጁን ወደ ኮሮ​ጆው አግ​ብቶ አንድ ድን​ጋይ ወሰደ፤ ወነ​ጨ​ፈ​ውም፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ግን​ባ​ሩን መታው፤ ድን​ጋ​ዩም ጥሩ​ሩን ዘልቆ በግ​ን​ባሩ ተቀ​ረ​ቀረ፤ እር​ሱም በም​ድር ላይ በፊቱ ተደፋ። ዳዊ​ትም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን በወ​ን​ጭ​ፍና በድ​ን​ጋይ አሸ​ነ​ፈው፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም መትቶ ገደለ ፤ በዳ​ዊ​ትም እጅ ሰይፍ አል​ነ​በ​ረም። ዳዊ​ትም ሮጦ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ላይ ቆመ፤ ሰይ​ፉ​ንም ይዞ ከሰ​ገ​ባው መዘ​ዘው፤ ገደ​ለ​ውም፤ ራሱ​ንም ቈረ​ጠው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዋና​ቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ሸሹ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልና የይ​ሁዳ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው እልል አሉ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም እስከ ጌትና እስከ አስ​ቀ​ሎና በር ድረስ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው። የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በድ​ኖ​ቻ​ቸው እስከ ጌትና እስከ አቃ​ሮን በሮች ድረስ በመ​ን​ገድ ላይ ወደቁ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ከማ​ሳ​ደድ ተመ​ል​ሰው ሰፈ​ራ​ቸ​ውን በዘ​በዙ። ዳዊ​ትም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ራስ ይዞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣው፤ ጋሻና ጦሩን ግን በድ​ን​ኳኑ ውስጥ አኖ​ረው። ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ሊዋጋ ሲወጣ ባየ ጊዜ ለሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ለአ​ቤ​ኔር፥ “አቤ​ኔር ሆይ፥ ይህ ብላ​ቴና የማን ልጅ ነው?” አለው። አቤ​ኔ​ርም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ አላ​ው​ቅም” አለ። ንጉ​ሡም፥ “ይህ ብላ​ቴና የማን ልጅ እንደ ሆነ አንተ ጠይ​ቅና ዕወቅ” አለው። ዳዊ​ትም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ገድሎ በተ​መ​ለሰ ጊዜ አቤ​ኔር ወሰ​ደው፤ ወደ ሳኦ​ልም ፊት አመ​ጣው፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ራስ በእጁ ይዞ ነበር። ሳኦ​ልም፥ “አንተ ብላ​ቴና የማን ልጅ ነህ?” አለው ዳዊ​ትም፥ “እኔ የቤተ ልሔሙ የባ​ሪ​ያህ የእ​ሴይ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ።

1 ሳሙኤል 17:20-58 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ዳዊት በማለዳ በጎቹን ለጠባቂ ትቶ፣ እሴይ እንዳዘዘው ዕቃውን ይዞ ጕዞ ጀመረ። ልክ ሰራዊቱ እየፎከረ ለውጊያ ቦታ ቦታውን ለመያዝ በሚወጣበት ጊዜ ከጦሩ ሰፈር ደረሰ። እስራኤልና ፍልስጥኤማውያን ቦታ ቦታቸውን ይዘው ፊት ለፊት ተፋጠው ይጠባበቁ ነበር። ዳዊት ዕቃውን ከስንቅ ጠባቂው ዘንድ አስቀምጦ ወደ ጦሩ ግንባር ሮጠ፤ ወንድሞቹንም አግኝቶ ደኅንነታቸውን ጠየቀ። ከእነርሱም ጋር በሚነጋገርበት ጊዜ፣ ከጌት የመጣው ፍልስጥኤማዊው ጀግና ጎልያድ ከሰልፉ መካከል ወጥቶ እንደ ለመደው ሲደነፋ፤ ዳዊት ሰማ። እስራኤላውያንም ሰውየውን ባዩት ጊዜ ሁሉም በታላቅ ፍርሀት ከፊቱ ሸሹ። እስራኤላውያንም እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው በየቀኑ እየመጣ እስራኤልን እንደሚገዳደር ታያላችሁ? ይህን ሰው ለሚገድል፣ ንጉሡ ብዙ ሀብት ይሰጠዋል፤ ሴት ልጁን ይድርለታል፣ የአባቱንም ቤት በእስራኤል ዘንድ ከግብር ነጻ ያደርገዋል” ይባባሉ ነበር። ዳዊት በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች፣ “ለመሆኑ ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እንዲህ ያለውን ውርደት ከእስራኤል ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? ደግሞስ የሕያው እግዚአብሔርን ሰራዊት ይገዳደር ዘንድ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ እርሱ ማነው?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም፣ “ለሚገድለው ሰው የሚደረግለትማ ይህ ነው” ሲሉ አስቀድመው ያሉትን ደግመው ነገሩት። ታላቅ ወንድሙ ኤልያብ፣ ዳዊት ከሰዎች ጋር ሲነጋገር በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጥቶ፣ “ለምን ወደዚህ ወረድህ? እነዚያንስ ጥቂት በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውሃቸው? ትዕቢትህንና የልብህን ክፋት ዐውቃለሁ፤ የመጣኸው ጦርነቱን ለማየት ብቻ ነው” አለው። ዳዊትም፣ “ታዲያ ምን አደረግሁ? መጠየቅ እንኳ አልችልም?” አለ። ከዚያም ወደ ሌላ ሰው ዘወር ብሎ፣ ያንኑ ጥያቄ ጠየቀ፤ ሰዎቹም እንደ ቀድሞው መለሱለት፤ ዳዊት የተናገረው ነገር ወደ ሳኦል ጆሮ ደረሰ፤ ሳኦልም ልኮ አስጠራው። ዳዊትም ሳኦልን፣ “ከዚህ ፍልስጥኤማዊ የተነሣ የማንም ሰው ልብ አይሸበር፤ ባሪያህ ሄዶ ይዋጋዋል” አለው። ሳኦልም መልሶ “አንተ ገና አንድ ፍሬ ልጅ ነህ፣ ሰውየው ግን ከልጅነቱ ጀምሮ ውጊያ የተለማመደ ስለሆነ፣ ወጥተህ ይህን ፍልስጥኤማዊ ልትገጥመው አትችልም” አለው። ዳዊት ግን ሳኦልን እንዲህ አለው፣ “አገልጋይህ የአባቱን በጎች በሚጠብቅበት ጊዜ፤ አንበሳ ወይም ድብ መጥቶ ከመንጋው አንድ በግ ነጥቆ ሲሄድ፣ ተከትዬ በመሄድ እመታውና ከአፉ አስጥል ነበር፤ ፊቱን ወደ እኔ በሚያዞርበትም ጊዜ ጕረሮውን ይዤ በመምታት እገድለው ነበር። ባሪያህ አንበሳውንም ድቡንም ገድሏል፤ ይህም ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ የሕያው እግዚአብሔርን ሰራዊት ተገዳድሯልና መጨረሻው ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል። ከአንበሳ መዳፍና ከድብ መንጋጋ ያዳነኝ እግዚአብሔር አሁንም ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሳኦልም፣ “ሂድ፤ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን” አለው። ከዚያም ሳኦል ለዳዊት የገዛ ራሱን የጦር ልብስ አለበሰው፤ ጥሩር አጠለቀለት፤ ከናስ የተሠራ ቍርም ደፋለት። ዳዊትም ይህን ዐይነት ልብስ ለብሶ ስለማያውቅ፣ ሰይፉን በጦር ልብሱ ላይ ታጥቆ ለመራመድ ሞከረ፤ እርሱም ሳኦልን፣ “ያልተለማመድሁት ስለሆነ እንደዚህ ሆኜ መራመድ አልችልም” አለው። ስለዚህ ሁሉንም አወለቀው። ከዚያም በትሩን በእጁ ያዘ፤ አምስት ድቡልቡል ድንጋዮች ከወንዝ መርጦ በእረኛ ኮረጆው ከጨመረ በኋላ፣ ወንጭፉን በእጁ ይዞ፣ ወደ ፍልስጥኤማዊው ቀረበ። ፍልስጥኤማዊውም፣ ጋሻ ጃግሬውን እፊት እፊቱ በማስቀደም፣ ወደ ዳዊት እየቀረበ መጣ። እርሱም ዳዊትን ትኵር ብሎ ሲያየው፣ ደም ግባት ያለው፣ መልከ መልካምና አንድ ፍሬ ልጅ ነበር፤ ስለዚህ ናቀው። ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፣ “በትር ይዘህ የምትመጣብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው፤ በአማልክቱም ስም ረገመው። እርሱም፣ “እስቲ ወደኔ ና! ሥጋህን ለሰማይ አሞሮችና፣ ለምድር አራዊት እሰጣለሁ” አለው። ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን እንዲህ አለው፤ “አንተ ሰይፍ፣ ጦርና ጭሬ ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን አንተ በተገዳደርኸው የእስራኤል ሰራዊት አምላክ በሆነው፣ ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ። እግዚአብሔር ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እኔ መትቼ እጥልሃለሁ፤ ራስህንም እቈርጠዋለሁ። በዚህች ዕለት የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ሬሣ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፣ ዓለምም ሁሉ በእስራኤል ዘንድ አምላክ መኖሩን ያውቃል። እዚህ የተሰበሰቡትም ሁሉ፣ እግዚአብሔር የሚያድነው በሰይፍ ወይም በጦር እንዳልሆነ ያውቃሉ፤ ሰልፉ የእግዚአብሔር ስለ ሆነም ሁላችሁን በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል።” ፍልስጥኤማዊው ሊመታው በቀረበ ጊዜ፣ ዳዊትም ሊገጥመው ወደ ውጊያው ሜዳ በፍጥነት ሮጠ። እጁንም ወደ ኮሮጆው በመስደድ አንድ ድንጋይ አውጥቶ ወነጨፈው፤ ፍልስጥኤማዊውንም ግንባሩ ላይ መታው። ድንጋዩም ግንባሩ ውስጥ ገብቶ ተቀረቀረ፤ ፍልስጥኤማዊውም በግምባሩ ተደፋ። በዚህ ሁኔታ ዳዊት በወንጭፍና በድንጋይ ብቻ ፍልስጥኤማዊውን አሸነፈው፤ በእጁም ሰይፍ ሳይዝ ፍልስጥኤማዊውን መታው፤ ገደለውም። ዳዊት ሮጦ በላዩ ላይ ቆመ፤ ከዚያም የፍልስጥኤማዊውን ሰይፍ ከሰገባው መዝዞ አወጣው፤ እርሱንም ከገደለው በኋላ ራሱን በሰይፍ ቈረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ጀግናቸው መሞቱን ባዩ ጊዜ ሸሹ። ከዚህ በኋላ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ተነሥተው እየፎከሩ ፍልስጥኤማውያንን እስከ ጌት መግቢያና እስከ ዔቅሮን በሮች ድረስ አሳደዷቸው። የፍልስጥኤማውያንም ሬሳ ከሸዓይራይም አንሥቶ እስከ ጌት ከዚያም እስከ ዔቅሮን በሮች ባለው መንገድ ላይ ወድቆ ነበር። እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተመለሱ፤ ሰፈራቸውንም በዘበዙ። ዳዊትም የፍልስጥኤማዊውን ራስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ ነገር ግን የፍልስጥኤማዊውን የጦር መሣሪያዎች በራሱ ድንኳን ውስጥ አስቀመጠ። ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ለመግጠም በሚሄድበት ጊዜ ሳኦል ተመልክቶ የሰራዊቱን አዛዥ አበኔርን፣ “አበኔር ሆይ፤ ይህ ልጅ የማን ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም፣ “ንጉሥ ሆይ፤ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ አላውቅም” ብሎ መለሰለት። ንጉሡም፣ “እንግዲህ ወጣቱ የማን ልጅ እንደ ሆነ ተከታትለህ ድረስበት” አለው። ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ እንደ ተመለሰ፣ አበኔር ይዞ ንጉሡ ዘንድ አቀረበው። በዚህ ጊዜ ዳዊት የጎልያድን ራስ በእጁ ይዞ ነበር። ሳኦልም፣ “አንተ ወጣት፣ የማን ልጅ ነህ?” ሲል ጠየቀው። ዳዊትም፣ “እኔ የአገልጋይህ የቤተ ልሔሙ ሰው የእሴይ ልጅ ነኝ” ሲል መለሰ።

1 ሳሙኤል 17:20-58 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ዳዊትም ማልዶ ተነሣ፥ በጎቹንም ለጠባቂ ተወ፥ እሴይም ያዘዘውን ይዞ ሄደ፥ ጭፍራውም ተሰልፎ ሲወጣ ለሰልፍም ሲጮኽ በሰረገሎች ወደ ተከበበው ሰፈር መጣ። እስራኤልና ፍልስጥኤማውያን ፊት ለፊት ተሰላልፈው ነበረ። ዳዊትም ዕቃውን በዕቃ ጠባቂው እጅ አኖረው፥ ወደ ሠራዊቱም ሮጠ፥ የወንድሞቹንም ደኅንነት ጠየቀ። እርሱም ሲነጋገራቸው፥ እነሆ፥ ጎልያድ የተባለው ያ ዋነኛ ጀግና ፍልስጥኤማዊ የጌት ሰው ከፍልስጥኤማውያን ጭፍራ መካከል ወጣ፥ የተናገረውንም ቃል ተናገረ፥ ዳዊትም ሰማ። የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ሰውዮውን ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው ከእርሱ ሸሹ። የእስራኤልም ሰዎች፦ ይህን የወጣውን ሰው አያችሁትን? በእውነት እስራኤልን ሊገዳደር ወጣ፥ የሚገድለውንም ሰው ንጉሡ እጅግ ባለጠጋ ያደርገዋል፥ ልጁንም ይድርለታል፥ ያባቱንም ቤተ ሰብ በእስራኤል ዘንድ ከግብር ነጻ ያወጣቸዋል አሉ። ዳዊትም በአጠገቡ ለቆሙት ሰዎች፦ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለሚገድል፥ ከእስራኤልም ተግዳሮትን ለሚያርቅ ሰው ምን ይደረግለታል? የሕያውን አምላክ ጭፍሮች የሚገዳደር ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ነው? ብሎ ተናገራቸው። ሕዝቡም፦ ለሚገድለው ሰው እንዲህ ይደረግለታል ብለው እንደ ቀድሞው መለሱለት። ታላቅ ወንድሙም ኤልያብ ከሰዎች ጋር ሲነጋገር ሰማ፥ የኤልያብም ቁጣ በዳዊት ላይ ነድዶ፦ ለምን ወደዚህ ወረድህ? እነዚያንስ ጥቂቶች በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውሃቸው? እኔ ኩራትህንና የልብህን ክፋት አውቃለሁና ሰልፉን ለማየት መጥተሃል አለው። ዳዊትም፦ እኔ ምን አደረግሁ? ይህ ታላቅ ነገር አይደለምን? አለ። ዳዊትም ከእርሱ ወደ ሌላ ሰው ዘወር አለ፥ እንደዚህም ያለ ነገር ተናገረ፥ ሕዝቡም እንደ ቀድሞው ያለ ነገር መለሱለት። ዳዊትም የተናገረው ቃል ተሰማ፥ ለሳኦልም ነገሩት፥ ወደ እርሱም አስጠራው። ዳዊትም ሳኦልን፦ ስለ እርሱ የማንም ልብ አይውደቅ፥ እኔ ባሪያህ ሄጄ ያንን ፍልስጥኤማዊ እወጋዋለሁ አለው። ሳኦልም ዳዊትን፦ አንተ ገና ብላቴና ነህና፥ እርሱም ከብላቴንነቱ ጀምሮ ጦረኛ ነውና ይህን ፍልስጥኤማዊ ለመውጋት ትሄድ ዘንድ አትችልም አለው። ዳዊትም ሳኦልን አለው፦ እኔ ባሪያህ የአባቴን በጎች ስጠብቅ አንበሳና ድብ ይመጣ ነበር፥ ከመንጋውም ጠቦት ይወስድ ነበር። በኋላውም እከተለውና እመታው ነበር፥ ከአፉም አስጥለው ነበር፥ በተነሣብኝም ጊዜ ጉሮሮውን ይዤ እመታውና እገድለው ነበር። እኔ ባሪያህ አንበሳና ድብ መታሁ፥ ይህም ያልተገረዘው ፍልስጥኤማዊ የሕያውን አምላክ ጭፍሮች ተገዳድሮአልና ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል። ዳዊትም፦ ከአንበሳና ከድብ እጅ ያስጣለኝ እግዚአብሔር ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያስጥለኛል አለ። ሳኦልም ዳዊትን፦ ሂድ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል አለው። ሳኦልም ዳዊትን የገዛ ራሱን ልብስ አለበሰው፥ በራሱም ላይ የናስ ቁር ደፋለት፥ ጥሩርም አለበሰው። ዳዊትም ሰይፉን በልብሱ ላይ ታጠቀ፥ ገናም አልፈተነውምና መሄድ ሞከረ። ዳዊትም ሳኦልን፦ አልፈተንሁትምና እንዲህ ብዬ መሄድ አልችልም አለው። ዳዊትም አወለቀ። በትሩንም በእጁ ወሰደ፥ ከወንዝም አምስት ድብልብል ድንጋዮችን መረጠ፥ በእረኛ ኮረጆውም በኪሱ ከተታቸው፥ ወንጭፍም በእጁ ነበረ፥ ወደ ፍልስጥኤማዊውም ቀረበ። ፍልስጥኤማዊውም መጥቶ ወደ ዳዊት ቀረበ፥ ጋሻ ጃግሬውም በፊቱ ይሄድ ነበር። ጎልያድም ዳዊትን ትኩር ብሎ አየው፥ ቀይ ብላቴና መልኩም ያማረ ነበረና ናቀው። ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፦ በትር ይዘህ የምትመጣብኝ እኔ ውሻ ነኝን? አለው። ፍልስጥኤማዊውም በአምላኮቹ ስም ዳዊትን ረገመው። ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፦ ወደ እኔ ና፥ ሥጋህንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ አለው። ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን አለው፦ አንተ ሰይፍና ጦር ጭሬም ይዘህ ትመጣብኛለህ፥ እኔ ግን ዛሬ በተገዳደርኸው በእስራኤል ጭፍሮች አምላክ ስም በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ። እግዚአብሔር ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፥ እመታህማለሁ፥ ራስህንም ከአንተ አነሣዋለሁ፥ የፍልስጥኤማውያንንም ሠራዊት ሬሶች ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ዛሬ እሰጣለሁ። ይኸውም ምድር ሁሉ በእስራኤል ዘንድ አምላክ እንዳለ ታውቅ ዘንድ፥ ይህም ጉባኤ ሁሉ እግዚአብሔር በሰይፍና በጦር የሚያድን እንዳይደል ያውቅ ዘንድ ነው። ሰልፉ ለእግዚአብሔር ነውና፥ እናንተንም በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል። ፍልስጥኤማዊውም ተነሥቶ ዳዊትን ሊገናኘው በቀረበ ጊዜ ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ሊገናኘው ወደ ሰልፉ ሮጠ። ዳዊትም እጁን ወደ ኮረጆው አግብቶ አንድ ድንጋይ ወሰደ፥ ወነጨፈውም፥ ፍልስጥኤማዊውንም ግምባሩን መታ፥ ድንጋዩም በግምባሩ ተቀረቀረ፥ እርሱም በምድር ላይ በፊቱ ተደፋ። ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው፥ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለ፥ በዳዊትም እጅ ሰይፍ አልነበረም። ዳዊትም ሮጦ በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፥ ሰይፉንም ይዞ ከሰገባው መዘዘው፥ ገደለውም፥ ራሱንም ቆረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ዋናቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ሸሹ። የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ተነሥተው እልል አሉ፥ ፍልስጥኤማውያንንም እስከ ጌትና እስከ አስቀሎና በር ድረስ አሳደዱአቸው። ፍልስጥኤማውያንም ከሸዓራይም ጀምሮ እስከ ጌትና እስከ አቃሮን ድረስ በመንገድ ላይ የተመቱት ወደቁ። የእስራኤልም ልጆች ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተመልሰው ሰፈራችውን በዘበዙ። ዳዊትም የፍልስጥኤማዊውን ራስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፥ ጋሻ ጦሩን ግን በድንኳኑ ውስጥ አኖረው። ሳኦልም ዳዊትን ወደ ፍልስጥኤማዊው ሲወጣ ባየው ጊዜ ለሠራዊቱ አለቃ ለአበኔር፦ አበኔር ሆይ፥ ይህ ብላቴና የማን ልጅ ነው? አለው። አበኔርም፦ ንጉሥ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፥ አላውቅም አለ። ንጉሡም፦ ይህ ብላቴና የማን ልጅ እንደ ሆነ አንተ ጠይቅ አለ። ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ አበኔር ወሰደው፥ ወደ ሳኦልም ፊት አመጣው፥ የፍልስጥኤማዊውንም ራስ በእጁ ይዞ ነበር። ሳኦልም፦ አንተ ብላቴና፥ የማን ልጅ ነህ? አለው። ዳዊትም፦ እኔ የቤተ ልሔሙ የባሪያህ የእሴይ ልጅ ነኝ ብሎ መለሰ።

1 ሳሙኤል 17:20-58 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ዳዊትም በማግስቱ ማልዶ ተነሣ፤ በጎቹን ለሌላ እረኛ በመተው እሴይ ባዘዘው መሠረት የተዘጋጀውን ምግብ ይዞ ሄደ፤ እስራኤላውያን ጦርነት ለመግጠም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሚደነፉበት ጊዜ ዳዊት ወደ ጦሩ ሰፈር ደረሰ። የፍልስጥኤማውያን ሠራዊትና የእስራኤላውያን ሠራዊት ቦታ ቦታቸውን ይዘው በጦሩ ግንባር ፊት ለፊት በመተያየት ላይ ነበሩ። ዳዊትም የያዘውን ምግብ ለስንቅ ጠባቂው ትቶ ወደ ጦሩ ግንባር እየሮጠ ወደ ወንድሞቹ ሄደ፤ ስለ ደኅንነታቸውም ጠየቃቸው። ዳዊትም ከወንድሞቹ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ እነሆ፥ ጎልያድ የተባለው ግዙፍ ፍልስጥኤማዊ የጋት ሰው ከዚያ በፊት ያደርገው እንደ ነበር ወደፊት በማምራት በእስራኤላውያን ላይ መፎከሩን ቀጠለ፤ ዳዊትም የእርሱን ድንፋታ ሰማ። እስራኤላውያንም ጎልያድን ባዩ ጊዜ በታላቅ ፍርሀት ሸሹ። እስራኤላውያንም እርስ በርሳቸውም እንዲህ ይባባሉ ነበር፤ “ይህ በየቀኑ እስራኤልን ለመፈታተን የሚወጣውን ሰው ታያላችሁን? ንጉሥ ሳኦል እርሱን ለሚገድልለት ሰው ብዙ ሀብት ለመስጠት ቃል ገብቶአል፤ ሴት ልጁንም እንደሚድርለትና የአባቱም ቤተሰብ ከግብር ነጻ እንደሚያደርግለት ተናግሮአል።” ዳዊትም በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች “ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እስራኤልን ከዚህ አሳፋሪ ውርደት ለሚያድን ሰው ምን ይደረግለታል? ኧረ ለመሆኑ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት የሚፈታተን ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ነው?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም ጎልያድን ለሚገድል ሰው ምን እንደሚደረግለት ነገሩት። የዳዊት ታላቅ ወንድም ኤሊአብም ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር ሰማ፤ እርሱም በዳዊት ላይ በጣም ተቈጥቶ “እዚህ ምን ትሠራለህ? በበረሓ ያሉትንስ እነዚያን ጥቂቶች በጎችህን ለማን ተውካቸው? እኔ ትዕቢተኛነትህንና የልብህን ክፋት ዐውቃለሁ! አሁን የመጣኸው እኮ የጦርነቱን ሁኔታ ለመመልከት ነው!” አለው። ዳዊትም “አሁን እኔ ምን አደረግሁ? ለመጠየቅ እንኳ አልችልምን?” ሲል መለሰለት፤ ከዚያም ወደ ሌላው ሰው መለስ ብሎ ያንኑ ጥያቄ አቀረበለት፤ በጠየቀ ቊጥር የሚያገኘው መልስ ተመሳሳይ ነበር። አንዳንድ ሰዎች ዳዊት የተናገረውን ቃል ሰምተው ስለ ነበር፥ ሄደው ለሳኦል ነገሩት፤ ሳኦልም ልኮ ዳዊትን አስጠራው። ዳዊትም ሳኦልን “ንጉሥ ሆይ! ከዚህ ፍልስጥኤማዊ የተነሣ ማንም ሰው መፍራት የለበትም! እኔ ያንተ አሽከር ሄጄ እርሱን እዋጋዋለሁ” አለው። ሳኦልም ዳዊትን፦ “አንተ ገና ልጅ ነህ፤ እርሱም ከልጅነቱ ጀምሮ ጦረኛ ስለ ሆነ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለመውጋት ትሄድ ዘንድ አትችልም” አለው። ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ ሆይ! እኔ ያንተ አሽከር የአባቴን በጎች የምጠብቅ እረኛ ነኝ፤ አንበሳም ሆነ ድብ መጥቶ ጠቦት በሚነጥቅበት ጊዜ፥ ተከትዬው ሄጄ አደጋ በመጣል የወሰደውን ጠቦት አስጥለው ነበር፤ አንበሳው ወይም ድቡ ወደ እኔ ተመልሶ በሚመጣበትም ጊዜ ጉሮሮውን አንቄ በመምታት እገድለው ነበር። እኔ ያንተ አሽከር አንበሳና ድብ ገድያለሁ፤ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ስለ ተፈታተነ ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል። ከአንበሳና ድብ ያዳነኝ እግዚአብሔር ከዚህም ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሳኦልም “መልካም ነው! እንግዲህ ሂድ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን!” ሲል መለሰለት። ሳኦልም የገዛ ራሱን የጦር ልብስ ለዳዊት አለበሰው፤ ከነሐስ የተሠራውን የራስ ቊር በዳዊት ራስ ላይ ደፍቶ ጥሩርም አለበሰው፤ ዳዊትም ይህን ዐይነት ልብስ ለብሶ ስለማያውቅ ሰይፉን በጦር ልብሱ ላይ ታጥቆ ለመሄድ ሲነሣ መራመድ አልቻለም፤ ስለዚህ ዳዊት ሳኦልን፦ “ያልተለማመድኩት ነገር ስለ ሆነ ይህን ሁሉ ልብስ ለብሼ መዋጋት አልችልም፤” አለ፤ ስለዚህም ያንን ሁሉ አወለቀ፤ በትሩን አንሥቶ፥ ከወንዝ ዳር አምስት ድቡልቡል ድንጋዮች መርጦ በመልቀም በእረኝነት ኮረጆው ከተተ፤ ወንጭፉንም ይዞ ወደ ፍልስጥኤማዊው ቀረበ። ፍልስጥኤማዊው ጎልያድ ወደ ዳዊት ለመቅረብ መራመድ ጀመረ፤ ጋሻጃግሬውም በፊት በፊቱ ይሄድ ነበር፤ ዳዊት ቀይ፥ መልከ መልካም፥ ትንሽ ልጅ ስለ ነበረ ዳዊትን ጎልያድ ትኲር ብሎ ባየው ጊዜ በንቀት ዐይን ተመለከተው፤ ስለዚህም ጎልያድ ዳዊትን “በትር ይዘህ የምትመጣው እኔ ውሻ ነኝን” ካለው በኋላ በአማልክቱ ስም ረገመው። ቀጥሎም “ወዲህ ና! ሥጋህን ለሰማይ አሞራዎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ” አለው። ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰ “አንተ ሰይፍ፥ ጦርና ሾተል ይዘህ መጥተህብኛል፤ እኔ ደግሞ አንተ በምትፈታተነውና በእስራኤል ሠራዊት አምላክ ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ፤ በዚህች ቀን እግዚአብሔር በአንተ ላይ ድልን ያጐናጽፈኛል፤ እኔም ራስህን እቈርጣለሁ፤ የፍልስጥኤማውያንንም ወታደሮች ሥጋ ለአሞራዎችና ለአራዊት ምግብ አድርጌ እሰጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ መላው ዓለም በእስራኤል ዘንድ አምላክ እንዳለ ያውቃል። እዚህ የተሰበሰቡት ሁሉ እግዚአብሔር የሚያድነው በሰይፍና በጦር አለመሆኑን ያውቃሉ፤ ጦርነቱ የእግዚአብሔር ነውና፤ በእናንተም ላይ ድልን እንድንጐናጸፍ ያደርገናል።” ፍልስጥኤማዊው አደጋ ሊጥልበት ወደ ዳዊት በቀረበ ጊዜ ዳዊት ጎልያድን ለመግጠም ወደ ጦሩ ግንባር እየሮጠ ሄደ። እጁንም ወደ ኮረጆው ከቶ አንዲት ድንጋይ በማውጣት በጎልያድ ላይ ወነጨፈ፤ ድንጋዩም ግንባሩን በጥርቆ ወደ ራስ ቅሉ ገባ፤ ጎልያድም በምድር ላይ በግንባሩ ተደፋ። በዚህም ዐይነት ዳዊት በወንጭፍና በድንጋይ ጎልያድን መትቶ በመግደል ድል አደረገ! በእጁም ሰይፍ አልነበረም። ወደ እርሱም ሮጦ በመሄድ በላዩ ላይ ቆመ፤ የጎልያድንም ሰይፍ ከሰገባው በመምዘዝ ራሱን ቈረጠው። ፍልስጥኤማውያንም የእነርሱ ዝነኛ ተዋጊ ጎልያድ መገደሉን ባዩ ጊዜ ሸሹ። ከዚህ በኋላ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እየፎከሩ እነርሱን በመከተል እስከ ጋትና እስከ ዔቅሮን የቅጽር በሮች ድረስ አሳደዱአቸው፤ የፍልስጥኤማውያን ሬሳ እስከ ጋትና እስከ ዔቅሮን ድረስ ወደ ሻዕራይም በሚያደርሰው መንገድ ሁሉ ወደቀ። እስራኤላውያንም እነርሱን አሳደው ከተመለሱ በኋላ ፍልስጥኤማውያን የነበሩበትን ሰፈር ዘረፉ። ዳዊት የጎልያድን ራስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ የጎልያድን የጦር መሣሪያዎች ግን በራሱ ድንኳን አስቀመጠ። ዳዊት ጎልያድን ለመውጋት በሚሄድበት ጊዜ ሳኦል ተመልክቶ የጦሩን አዛዥ አበኔርን “ይህ የማን ልጅ ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም “ንጉሥ ሆይ! በሕይወትህ እምላለሁ፤ የማን ልጅ እንደ ሆነ ገና አላወቅሁም” አለው። ሳኦልም “ሄደህ ይህ ወጣት የማን ልጅ እንደ ሆነ አጥንተህ ዕወቅ” ሲል አዘዘው። ስለዚህ ዳዊት ጎልያድን ገድሎ ወደ ጦር ሰፈር በተመለሰ ጊዜ አበኔር ተቀብሎ ወደ ሳኦል አቀረበው፤ በዚህን ጊዜ ዳዊት የጎልያድን ራስ እንደ ያዘ ነበር፤ ሳኦልም “አንተ ወጣት የማን ልጅ ነህ?” ብሎ ጠየቀው። ዳዊትም “የቤተልሔም ነዋሪ የሆነው የአገልጋይህ የእሴይ ልጅ ነኝ” ሲል መለሰለት።

1 ሳሙኤል 17:20-58 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ዳዊት በማለዳ በጎቹን ለጠባቂ ትቶ፥ እሴይ እንዳዘዘው ዕቃውን ይዞ ጉዞ ጀመረ። ልክ ሠራዊቱ እየፎከረ ለውጊያ ቦታ ቦታውን ለመያዝ በሚወጣበት ጊዜ ከጦሩ ሰፈር ደረሰ። እስራኤልና ፍልስጥኤማውያን ቦታ ቦታቸውን ይዘው ፊት ለፊት ተፋጠው ይጠባበቁ ነበር። ዳዊት ዕቃውን ከስንቅ ጠባቂው ዘንድ አስቀምጦ ወደ ጦሩ ግንባር ሮጠ፤ ወንድሞቹንም አግኝቶ ደኅንነታቸውን ጠየቀ። ከእነርሱም ጋር በሚነጋገርበት ጊዜ፥ እነሆ፥ ከጌት የመጣው ፍልስጥኤማዊው ጀግና ጎልያድ ከሰልፉ መካከል ወጥቶ እንደ ለመደው ሲደነፋ ዳዊት ሰማ። እስራኤላውያንም ሰውየውን ባዩት ጊዜ ሁሉም በታላቅ ፍርሃት ከፊቱ ሸሹ። እስራኤላውያንም እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው በየቀኑ እየመጣ እስራኤልን እንደሚገዳደር ታያላችሁ? ይህን ሰው ለሚገድል፥ ንጉሡ ብዙ ሀብት ይሰጠዋል፤ ሴት ልጁን ይድርለታል፥ የአባቱንም ቤት በእስራኤል ዘንድ ከግብር ነጻ ያደርገዋል” ይባባሉ ነበር። ዳዊት በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች፥ “ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እንዲህ ያለውን ውርደት ከእስራኤል ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? ደግሞስ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ይገዳደር ዘንድ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ እርሱ ማነው?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም፥ “ለሚገድለው ሰው የሚደረግለትማ ይህ ነው” ሲሉ አስቀድመው ያሉትን ደግመው ነገሩት። ታላቅ ወንድሙ ኤሊአብ፥ ዳዊት ከሰዎች ጋር ሲነጋገር በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ፥ “ለምን ወደዚህ ወረድህ? እነዚያንስ ጥቂት በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውካቸው? ዕብሪትህንና የልብህን ክፋት ዐውቃለሁ፤ የመጣኸው ጦርነቱን ለማየት ብቻ ነው” አለው። ዳዊትም፥ “እኔ ምን አደረግሁ? መጠየቅ እንኳ አልችልምን?” አለ። ከዚያም ወደ ሌላ ሰው ዘወር ብሎ፥ ያንኑ ጥያቄ ጠየቀ፤ ሰዎቹም እንደ ቀድሞው መለሱለት፤ ዳዊት የተናገረው ነገር ወደ ሳኦል ጆሮ ደረሰ፤ ሳኦልም ልኮ አስጠራው። ዳዊትም ሳኦልን፥ “ከዚህ ፍልስጥኤማዊ የተነሣ የማንም ሰው ልብ አይሸበር፤ እኔ አገልጋይህ ሄጄ እዋጋዋለሁ” አለው። ሳኦልም መልሶ “አንተ ገና ልጅ ነህ፥ ሰውየው ግን ከልጅነቱ ጀምሮ ውጊያ የተለማመደ ስለሆነ፥ ወጥተህ ይህን ፍልስጥኤማዊ ልትገጥመው አትችልም” አለው። ዳዊት ግን ሳኦልን እንዲህ አለው፥ “አገልጋይህ የአባቱን በጎች በሚጠብቅበት ጊዜ፤ አንበሳ ወይም ድብ መጥቶ ከመንጋው አንድ በግ ነጥቆ ሲሄድ፥ ተከትዬ በመሄድ እመታውና ከአፉ አስጥል ነበር፤ ፊቱን ወደ እኔ በሚያዞርበትም ጊዜ ጉሮሮውን ይዤ በመምታት እገድለው ነበር። ባርያህ አንበሳውንም ድቡንም ገድሏል፤ ይህም ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ተገዳድሯልና መጨረሻው ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል። ከአንበሳ መዳፍና ከድብ መንጋጋ ያዳነኝ ጌታ አሁንም ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሲል ዳዊት ተናገረ። ሳኦልም ዳዊትን፥ “ሂድ፤ ጌታ ካንተ ጋር ይሁን!” አለው። ከዚያም ሳኦል ለዳዊት የገዛ ራሱን የጦር ልብስ አለበሰው፤ ከናሐስ የተሠራ ቁር ደፋለት፤ ጥሩርም አለበሰው። ዳዊትም ይህን ዓይነት ልብስ ለብሶ ስለማያውቅ፥ ሰይፉን በጦር ልብሱ ላይ ታጥቆ ለመራመድ ሞከረ፤ እርሱም ሳኦልን፥ “ያልተለማመድሁት ስለሆነ እንደዚህ ሆኜ መራመድ አልችልም” አለው። ስለዚህ ያንን አወለቀው። ከዚያም በትሩን በእጁ ያዘ፤ አምስት ድቡልቡል ድንጋዮች ከወንዝ መርጦ በእረኛ ኮረጆው ከጨመረ በኋላ፥ ወንጭፉን በእጁ ይዞ ወደ ፍልስጥኤማዊው ቀረበ። ፍልስጥኤማዊውም፥ ጋሻ ጃግሬውን ከፊት ከፊቱ በማስቀደም፥ ወደ ዳዊት እየቀረበ መጣ። እርሱም ዳዊትን ትኩር ብሎ ሲያየው፥ ደም ግባት ያለው፥ መልከ መልካምና ልጅ ነበር፤ ስለዚህ በንቀት ዐይን ተመለከተው። ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፥ “በትር ይዘህ የምትመጣብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው፤ በአማልክቱም ስም ረገመው። እርሱም ዳዊትን፥ “እስቲ ወደኔ ና! ሥጋህን ለሰማይ አሞሮችና፥ ለምድር አራዊት እሰጣለሁ” አለው። ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን እንዲህ አለው፤ “አንተ ሰይፍ፥ ጦርና ጭሬ ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን አንተ በተገዳደርኸው የእስራኤል ሠራዊት አምላክ በሆነው፥ ሁሉን በሚችል በሠራዊት ጌታ ስም እመጣብሃለሁ። ጌታ ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እኔ መትቼ እጥልሃለሁ፤ ራስህንም እቆርጠዋለሁ። በዚህች ዕለት የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ሬሣ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፤ ዓለምም ሁሉ በእስራኤል ዘንድ እግዚአብሔር መኖሩን ያውቃል። እዚህ የተሰበሰቡትም ሁሉ ጌታ ያለ ሰይፍ ወይም ያለ ጦር እንደሚያድን ያውቃሉ፤ ሰልፉ የጌታ ስለ ሆነም ሁላችሁን በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል።” ፍልስጥኤማዊው ሊመታው በቀረበ ጊዜ፥ ዳዊትም ሊገጥመው ወደ ውጊያው ሜዳ በፍጥነት ሮጠ። እጁንም ወደ ኮሮጆው በመስደድ አንድ ድንጋይ አውጥቶ ወነጨፈው፤ ፍልስጥኤማዊውንም ግንባሩ ላይ መታው። ድንጋዩም ግንባሩ ውስጥ ገብቶ ተቀረቀረ፤ በግምባሩም ምድር ላይ ተደፋ። በዚህ ሁኔታ ዳዊት በወንጭፍና በድንጋይ ብቻ ፍልስጥኤማዊውን አሸነፈው፤ በእጁም ሰይፍ ሳይዝ ፍልስጥኤማዊውን መታው፤ ገደለውም። ዳዊት ሮጦ በላዩ ላይ ቆመ፤ ከዚያም የፍልስጥኤማዊውን ሰይፍ ከሰገባው መዞ አወጣው፤ እርሱንም ከገደለው በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ጀግናቸው መሞቱን ባዩ ጊዜ ሸሹ። ከዚህ በኋላ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ተነሥተው እየፎከሩ ፍልስጥኤማውያንን እስከ ጋት መግቢያና እስከ ዔቅሮን በሮች ድረስ አሳደዷቸው። የፍልስጥኤማውያንም ሬሳ ከሸዓራይም አንሥቶ እስከ ጋትና ከዚያም እስከ ዔቅሮን በሮች ባለው መንገድ ላይ ወደቀ። እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን አሳደው ተመለሱ፤ ሰፈራቸውንም በዘበዙ። ዳዊትም የፍልስጥኤማዊውን ራስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ የጦር መሣሪያዎቹን ግን በራሱ ድንኳን ውስጥ አስቀመጠ። ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ለመግጠም ሲሄድ ሳኦል ተመልክቶ የሠራዊቱን አዛዥ አበኔርን፥ “አበኔር ሆይ፤ ይህ ልጅ የማን ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም፥ “ንጉሥ ሆይ፤ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ አላውቅም” ብሎ መለሰለት። ንጉሡም፥ “እንግዲህ ወጣቱ የማን ልጅ እንደሆነ ተከታትለህ ድረስበት” አለው። ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ እንደ ተመለሰ፥ አበኔር ይዞ ንጉሡ ዘንድ አቀረበው። በዚህ ጊዜ ዳዊት የጎልያድን ራስ በእጁ ይዞ ነበር። ሳኦልም “አንተ ወጣት የማን ልጅ ነህ?” ብሎ ጠየቀው። ዳዊትም “የቤተልሔም ነዋሪ የሆነው የአገልጋይህ የእሴይ ልጅ ነኝ” ሲል መለሰለት።