1 ሳሙኤል 1:15-19

1 ሳሙኤል 1:15-19 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሐናም መልሳ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አይ​ደ​ለም፤ እኔስ ወራት የባ​ሳት ሴት ነኝ፤ ጠጅና ሌላ የሚ​ያ​ሰ​ክር ነገር አል​ጠ​ጣ​ሁም፤ ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነፍ​ሴን አፈ​ሰ​ስሁ፤ ኀዘ​ኔና ጭን​ቀቴ ስለ በዛ እስከ አሁን ድረስ እደ​ክ​ማ​ለ​ሁና ባር​ያ​ህን እንደ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ሴቶች ልጆች አት​ቍ​ጠ​ራት።” ዔሊም፥ “በሰ​ላም ሂጂ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ከአ​ንቺ ጋር ይሁን የለ​መ​ን​ሽ​ው​ንም ልመና ሁሉ ይስ​ጥሽ” ብሎ መለ​ሰ​ላት። እር​ስ​ዋም፥ “ባር​ያህ በፊ​ትህ ሞገ​ስን አገ​ኘች” አለ​ችው። ሴቲ​ቱም መን​ገ​ድ​ዋን ሄደች፤ ወደ ቤት​ዋም ገባች፤ ከባ​ሏም ጋር በላች፤ ጠጣ​ችም ፤ ፊቷም ከዚያ በኋላ አዘ​ን​ተኛ መስሎ አል​ታ​የም። ማል​ደ​ውም ተነ​ሥ​ተው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰግ​ደው ሄዱ፤ ወደ ቤታ​ቸ​ውም ወደ አር​ማ​ቴም ደረሱ፤ ሕል​ቃ​ናም ሚስ​ቱን ሐናን ዐወ​ቃት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሰ​ባት፤ ፀነ​ሰ​ችም።