1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 1:15-19

1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 1:15-19 መቅካእኤ

ሐናም እንዲህ ብላ መለሰችለት፥ “ጌታዬ ሆይ፤ አይደለም፤ እኔስ ልቧ ክፉኛ ያዘነባት ሴት ነኝ፤ የልቤን ኀዘን በጌታ ፊት አፈሰስሁ እንጂ፥ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም። ይህን ያህል ጊዜ የጸለይኩት ከባድ ከሆነው ጭንቀቴና መከራዬ የተነሣ ስለሆነ፥ አገልጋይህን እንደማትረባ ሴት አትቁጠረኝ።” ከዚያም ዔሊ፥ “በሰላም ሂጂ! የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ይስጥሽ!” አላት። እርሷም፥ “አገልጋይህ በፊትህ ሞገስ ታግኝ” አለች፤ ከዚያም ተነሥታ መንገዷን ቀጠለች፤ ምግብም በላች፤ በፊቷም ገጽ ኀዘን መታየቱ ቆመ። በማግስቱ ጠዋት ተነሥተው በጌታ ፊት ሰገዱ፤ ከዚያም በራማ ወደሚገኘው ቤታቸው ተመለሱ። ሕልቃናም ሚስቱን ሐናን ዐወቃት፤ ጌታም አሰባት፤

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}