1 ቆሮንቶስ 5:1-7

1 ቆሮንቶስ 5:1-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በመካከላችሁ አሳፋሪ የዝሙት ሥራ መኖሩ ይወራል፤ እንዲህ ዐይነቱ የዝሙት ሥራ በአሕዛብ ዘንድ እንኳ የማይደረግ ነው፤ ይኸውም የእንጀራ እናቱን እንደ ሚስት አድርጎ የሚኖር አለ ተብሎአል። ታዲያ፥ እንዲህ ያለ አሳፋሪ ነገር በመካከላችሁ እያለ ለምን ትታበያላችሁ? ይልቅስ በዚህ ነገር ማዘን አይገባችሁምን? እንዲህ ዐይነቱን ሥራ የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱ። ምንም እንኳ እኔ በሥጋ አብሬአችሁ ባልሆን በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ልክ አብሬአችሁ እንዳለሁ ሆኜ እንዲህ ዐይነቱን ሥራ በፈጸመው ሰው ላይ በጌታ በኢየሱስ ስም ፈርጄበታለሁ፤ በምትሰበሰቡበት ጊዜ እኔም በጌታችን በኢየሱስ ኀይል በመካከላችሁ በመንፈስ ስለምገኝ፥ በኃጢአት የተሞላው የዚህ ሰው ሥጋ ይፈርስ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፋችሁ ልትሰጡት ይገባል። ይህንንም የምታደርጉት ጌታ ኢየሱስ ለፍርድ በሚመጣበት ቀን የዚህ ሰው ነፍስ እንድትድን ነው። እንግዲህ መመካታችሁ መልካም አይደለም፤ ትንሽ እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው ታውቁ የለምን? አሁን እንደ ሆናችሁት ሁሉ እርሾ እንደሌለበት እንደ አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፤ የፋሲካችን በግ የሆነው ክርስቶስ ተሠውቶአል፤

1 ቆሮንቶስ 5:1-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በእ​ና​ንተ ላይ ዝሙት ይሰ​ማል፤ እን​ደ​ዚህ ያለው ዝሙ​ትም አረ​ማ​ው​ያን እንኳ የማ​ያ​ደ​ር​ጉት ነው፤ ያባ​ቱን ሚስት ያገባ አለና። እና​ን​ተም ከዚህ ጋር ትዕ​ቢ​ተ​ኞች ናችሁ፤ ይል​ቁ​ንም ይህን ያደ​ረ​ገው ከእ​ና​ንተ ይለይ ዘንድ ለምን አላ​ዘ​ና​ች​ሁ​በ​ትም? እኔ በሥ​ጋዬ ከእ​ና​ንተ ጋር ባል​ኖር፥ በመ​ን​ፈሴ ከእ​ና​ንተ ጋር አለሁ፤ እነሆ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር እንደ አለሁ ሆኜ፥ ይህን ሥራ የሠ​ራ​ውን እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ። በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ፥ በእኔ ሥል​ጣን፥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱ​ስም ኀይል፥ ሥጋ​ውን ጎድቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን ነፍሱ ትድን ዘንድ እን​ዲህ ያለ​ውን ሰው ለሰ​ይ​ጣን አሳ​ል​ፋ​ችሁ ስጡት። እን​ግ​ዲ​ያስ መታ​በ​ያ​ችሁ መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ጥቂቱ እርሾ ብዙ​ውን ሊጥ እን​ደ​ሚ​ያ​መጥ አታ​ው​ቁ​ምን? እን​ግ​ዲህ ለአ​ዲስ ቡሆ ትሆኑ ዘንድ አሮ​ጌ​ውን እርሾ ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ ገና ቂጣ ናች​ሁና፤ ፋሲ​ካ​ችን ክር​ስ​ቶስ ተሠ​ውቶ የለ​ምን?

1 ቆሮንቶስ 5:1-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በመካከላችሁ የዝሙት ርኩሰት እንዳለ በርግጥ ይወራል፤ እንዲህ ያለው ርኩሰት በአረማውያን ዘንድ እንኳ ታይቶ የማይታወቅ ነው፤ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው አለና። ደግሞም ታብያችኋል! ይልቅስ ሐዘን ተሰምቷችሁ፣ ይህን ድርጊት የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ ልታስወግዱት አይገባምን? ምንም እንኳ እኔ በአካል አብሬያችሁ ባልሆንም፣ በመንፈስ ግን ከእናንተ ጋራ ነኝ፤ ልክ አብሬያችሁ እንዳለሁ ሆኜ፣ ይህን ባደረገው ሰው ላይ አሁኑኑ ፈርጄበታለሁ። በምትሰበሰቡበት ጊዜ እኔም በመንፈስ ከእናንተ ጋራ ስለምሆን፣ በጌታችን በኢየሱስ ስምና በመካከላችሁ በሚገኘው በጌታችን በኢየሱስ ኀይል፣ ሥጋው ጠፍቶ መንፈሱ በጌታ ቀን ትድን ዘንድ፣ እንደዚህ ዐይነቱ ለሰይጣን ይሰጥ። መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው አታውቁምን? አሁን ያለ እርሾ እንደ ሆናችሁ ሁሉ አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፤ የፋሲካ በጋችን የሆነው ክርስቶስ ተሠውቷልና።