በእናንተ ላይ ዝሙት ይሰማል፤ እንደዚህ ያለው ዝሙትም አረማውያን እንኳ የማያደርጉት ነው፤ ያባቱን ሚስት ያገባ አለና። እናንተም ከዚህ ጋር ትዕቢተኞች ናችሁ፤ ይልቁንም ይህን ያደረገው ከእናንተ ይለይ ዘንድ ለምን አላዘናችሁበትም? እኔ በሥጋዬ ከእናንተ ጋር ባልኖር፥ በመንፈሴ ከእናንተ ጋር አለሁ፤ እነሆ፥ ከእናንተ ጋር እንደ አለሁ ሆኜ፥ ይህን ሥራ የሠራውን እፈርድበታለሁ። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተሰብስባችሁ፥ በእኔ ሥልጣን፥ በጌታችን በኢየሱስም ኀይል፥ ሥጋውን ጎድቶ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ቀን ነፍሱ ትድን ዘንድ እንዲህ ያለውን ሰው ለሰይጣን አሳልፋችሁ ስጡት። እንግዲያስ መታበያችሁ መልካም አይደለም፤ ጥቂቱ እርሾ ብዙውን ሊጥ እንደሚያመጥ አታውቁምን? እንግዲህ ለአዲስ ቡሆ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ ከእናንተ አርቁ፤ ገና ቂጣ ናችሁና፤ ፋሲካችን ክርስቶስ ተሠውቶ የለምን?
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 5 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 5
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 5:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች