1 ቆሮንቶስ 4:18-21
1 ቆሮንቶስ 4:18-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እነሆ፥ ወደ እናንተ ስላልመጣሁ ከእናንተ ወገን የታበዩ ሰዎች አሉ። እንኪያስ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ፈጥኜ እመጣለሁ፤ ነገር ግን የትዕቢተኞችን ነገር አልሻም፤ ኀይላቸውን እሻለሁ እንጂ። የእግዚአብሔር መንግሥት በኀይል እንጂ በቃል አይደለምና። እንዴት ሆኜ ወደ እናንተ ልመጣ ትወዳላችሁ? በበትር ነውን? ወይስ በፍቅርና በቅንነት መንፈስ?
1 ቆሮንቶስ 4:18-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከእናንተ አንዳንዶቹ ወደ እናንተ የማልመጣ መስሏቸው ታብየዋል፤ ይሁን እንጂ የጌታ ፈቃድ ቢሆን ፈጥኜ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ ከዚያም እነዚህ ትዕቢተኞች የሚናገሩትን ብቻ ሳይሆን፣ ምን ኀይል እንዳላቸውም ማየት እሻለሁ። ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት የወሬ ጕዳይ ሳይሆን የኀይል ጕዳይ ነው። ለመሆኑ የምትፈልጉት የቱን ነው? በትር ይዤ ልምጣ ወይስ በፍቅርና በገርነት መንፈስ?
1 ቆሮንቶስ 4:18-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አንዳንዱ ግን ወደ እናንተ የማልመጣ እየመሰላቸው የታበዩ አሉ፤ ነገር ግን ጌታ ቢፈቅድ ፈጥኜ ወደ እናንተ እመጣለሁ፥ የትዕቢተኞችንም ኃይል አውቃለሁ እንጂ ቃላቸውን አይደለም፤ የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ነው እንጂ በቃል አይደለምና። ምን ትወዳላችሁ? በበትር ወይስ በፍቅርና በየውሃት መንፈስ ልምጣባችሁን?
1 ቆሮንቶስ 4:18-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ነገር ግን ከእናንተ አንዳንዶቹ እኔ እናንተን ለመጐብኘት የማልመጣ መስሎአቸው በትዕቢት ተሞልተዋል። ይሁን እንጂ የጌታ ፈቃድ ቢሆን በቅርብ ጊዜ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ የእነዚህን ትዕቢተኞች ንግግራቸውን ብቻ ሳይሆን ኀይላቸውንም ማወቅ እፈልጋለሁ። የእግዚአብሔር መንግሥት የንግግር ጉዳይ ሳይሆን የእግዚአብሔር ኀይል ነው። የምትፈልጉት ምንድን ነው? የመቅጫ በትር ይዤ ወደ እናንተ እንድመጣ ትፈልጋላችሁን? ወይስ በፍቅርና በትሕትና መንፈስ እንድመጣ ትፈልጋላችሁ?