1 ቆሮንቶስ 4:15-16
1 ቆሮንቶስ 4:15-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በክርስቶስ ብዙ መምህራን ቢኖሩአችሁም አባቶቻችሁ ብዙዎች አይደሉም፤ እኔ በኢየሱስ ክርስቶስ በትምህርት ወልጄአችኋለሁና። ወንድሞቻችን ሆይ! እኔን እንድትመስሉ እማልዳችኋለሁ፤
1 ቆሮንቶስ 4:15-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ምንም እንኳ በዐሥር ሺሕ የሚቈጠሩ ሞግዚቶች በክርስቶስ ቢኖሯችሁም፣ ብዙ አባቶች ግን የሏችሁም፤ በወንጌል አማካይነት በክርስቶስ ኢየሱስ ወልጄአችኋለሁና። ስለዚህ እኔን እንድትመስሉ እለምናችኋለሁ።
1 ቆሮንቶስ 4:15-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በክርስቶስ አእላፍ ሞግዚቶች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌል ወልጄአችኋለሁና። እንግዲህ እኔን የምትመስሉ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።